#ኻሊድ ኢስላማዊ ማዕከል


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


#ኻሊድ ኢስላማዊ ማዕከል
☞ ዓሊም
ወይም ዑስታዝ አይደለሁም፤ ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ/እውቀትን ፈላጊ ነኝ።
ነገር ግን «አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ!» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ ለማድረስ ብዬ ነው። እናንተም አንዲትም ቃል ብቶን ከማድረስ አትስነፉ
አሏህ ይቀበለን!!!

👇𝐉𝐨𝐢𝐧 & 👇𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞
https://t.me/Khalid_Islamawi_Studio

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


✅ ኢብኑል ቀይም የተባለው ታላቁ ዓሊም – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላል : –

" ፆም አላህን ለሚፈሩ ሉጋም ነው ። ( ፍላጎትን) ለሚዋጉ ጋሻ ነው ። ለደጋጎችናወደ አላህ ለቀረቡት ( የእርካታ) እንቅስቃሴ ነው ። እሱ ከሌላው ስራ በተለየ ለአላህ ነው ። "

https://t.me/bahruteka


Forward from: Bahiru Teka
🔷 ረመዳንን ለመቀበል የሚረዱ 10 ነጥቦች

               ካለፈው የቀጠለ

ያለፈውን ለማግኘት የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/bahruteka/4636

      ረመዳንን ለመቀበል ከሚረዱ ነጥቦች አምስተኛውን ( ተውበት አደርጎ መቀበል ) የሚለውን አይተን ነበር ።

   – ስድስተኛው – ከመሀበራዊ መገናኛ ዘዴዎች
                   በተለይ እንደ ፌስቡክ ፣ ቲክ – ቶክና ፣ ዩ – ቲዩብ የመሳሰሉት መራቅ ።
    እንደነዚህ አይነት ሚዲያዎች ምእራባዊያን የሰውን ልጅ ባጠቃላይ ሙስሊሞችን በተለይ ከስነምግባር ውጪና የስሜት አምላኪዎች ለማድረግ የዘረጉዋቸው መረቦች ናቸው ። በእነዚህ ድህረገፆች አማካይነት የሚለቋችው ፀያፍ ፊልምና ምስሎች ሰዎችን በቀላሉ ከስነምግባር ውጪ አድርገው የስሜት አምላኪ ያደርጉታል ።
   የሚያሳዝነው በእነዚህ ሚዲያዎች ዋናው ተጠቃሚ ሙስሊሙ መሆኑ ነው ። ከረመዳን ፆም ቱሩፋት ተጠቃሚ ለመሆንና ያለችውን የኢማን ጭላንጭል ለመጠበቅ የፈለገ ሰው ከእነዚህ ሚዲያዎች ይራቅ ። የረመዳንን ወር ለመቀበል ከዚህ ወደ አዘቅት ይዞ ከሚጓዝ የስሜት ፈረስ ወርዶ በተውበት ፈረስ ወደ አላህ መገስገስ ይነርበታል ።
– ሰባተኛ – ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ማድረስ
              አላህ ባሪያው አንድ ፀጋ ሲውልለት ካመሰገነ ሌላ ፀጋ ይጨምርለታል ። ከፀጋዎች ሁሉ ትልቁ ፀጋ በላኢላሀ ኢልለላህ ኑሮ ለረመዳን ወር መድረስ ነው ። ለዚህ ፀጋው አላህን ማመስገን በጣም አስፈላጊ ነው ። ባሪያው ለረመዳን ወር ስላደረሰው ካመሰገነው በቱሩፋቱ ተጠቃሚ ያደርገዋል ። ወንጀሉንም ሊምርለት ሰበብ ይሆነዋልና አላህን ማመስገን ባህሪያችን እንዲያደርግልን እንለምነዋለን ።
– ስምንተኛ  – ይቅር ማለት
                  ረመዳንን ለመቀበል ልብን ንፁህ አድርጎ የአእምሯችንን ገፆች ነጭ አድርገን ከዘመድ ከጓደኛ ከማንኛውም ሰው ያለን ዲናዊ ያልሆኑ ቅያሜዎችን አስወግደን ለበደለን ይቅር ብለን መቀበል ይኖርብናል ። በዱንያዊ ጉዳይ ቂም ይዞ ፆም ትርፉ ረሀብና ጥም ነው ። የሁለት የተጣሉ ሰዎች ስራ እስኪታረቁ ድረስ ወደ አላህ ዘንድ አይወጣምና ።
– ዘጠነኛ – ፆመኞችን ለማስፈጠር መዘጋጀት
              ረመዳን ሲመጣ አብዛኛው ሰው በአቅሙ ልክ የተለያዩ ማፍጠሪያዎችን ያዘጋጃል ። ይህ ውስጣዊ ዝግጅት ከቀደመውና ማባከን ከሌለበት ጥሩ ነው ።  ከዚሁ ጎን ለጎን ረመዳን የመተዛዘን የመረዳዳት ወር እንደመሆኑ ምስኪኖችን ፣ አቅመደካሞችን ሰው ፊት ቆመው የማይለምኑ ችግራቸው አላህና ራሳቸው እንጂ ማንም የማያውቅላቸው ወንድምና እህቶችን በማስታወስ የምንችለውን በማድረግ በረመዳን እንዲደሰቱ ለማድረግ መዘጋጀት ያስፈልጋል ።
– አስረኛ – ቁርኣን ለመቅራት መነየት
              ረመዳን ቁርኣን የወረደበትና የቁርኣን ወር ስለሆነ ይህ አላህ ለአማኞች የሰጠው የህይወት መመሪያ የሆነውን ገፀበረከት በውስጡ የሁለት ሀገር ስኬት የያዘው ከጌታችን ለየአንዳንዳችን የተላከው ደብዳቤ አንብበን በውስጡ ያለውን ማእድን ሳንጠቀምበት አላህ ፊት እንዳንቀርብ ቁርጥ ባለ ንያ ቁርኣን መቅራት እጀምራለሁ ብለን ልንዘጋጅ ይገባል ። ቀጥሎ ባወጣነው ፕሮግራም መሰረት በቀኑ ወይም በማታው ክ/ጊዜ ጀምረን ለማክተም እንዲወፍቀን አላህን መለመን አለብን ።

       አላህ ካገራላቸው ባሮቹ ያድርገን ።

ጠቃሚ ስለሆነ በድጋሚ የተለቀቀ ።

https://t.me/bahruteka


Forward from: [ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
ነሺዳ የሱፊዮች እና የኢኽዋኖች ዘፈን እንጂ ኢስላማዊ አይደለም!!

""""""""""""""የመፅሃፉ መቅድም""""""""""""""
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህና አዛኝ በሆነው፣ በእርሱም እታገዛለሁ!።
ምስጋና በጠቅላላ ለዓለማቱ ብቸኛ ለሆነውና በሀይማኖቱ ደንጋጊ (ህግ አውጪ) ለሆነው፤ የሰው ልጆችን እውቀቱ በሌላቸው ነገር ላይ መከተልን የከለከለ ለሆነው፤ ብቸኛ ተመላኪ ለሆነው አምላካችን አላህ የተገባ ነው!!፡፡

የሰው ልጆችን እውቀቱ የሌላቸውን ነገር እንዳይከተሉ እንዲህ በማለት ከልክሏል፡-

﴿وَلَا تَقْفُ مَا لَيْسَ لَكَ بِهِ عِلْمٌ  إِنَّ السَّمْعَ وَالْبَصَرَ وَالْفُؤَادَ كُلُّ أُولَئِكَ كَانَ عَنْهُ مَسْئُولًا ﴾ [الإسراء:٣٦]

ለአንተ በርሱ እውቀት የሌለህን ነገር አትከተል፡፡ መስሚያ፤ ማያም፤ ልብም እነዚህ ሁሉ ‹ባለቤታቸው› ከእነሱ ተጠያቂ ነውና፡፡” አል ኢስራእ 36

ከነፍሳችን ተንኮልና ከብልሹ ስራችን በአላህ እንጠበቃለን፤ አላህ የመራውን የሚያጠመው የለም፤ አላህ ያጠመመውንም የሚያቃናው የለም! ከአንድ አላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ (በልቤ ያመንኩ ስሆን) የምስክርነት ቃሌን እሰጣለሁ፤ እርሱም ብቸኛና ምንም ተጋሪ የለውም! ነቢዩ ሙሐመድምﷺ የእርሱ ባሪያና መልእክተኛው መሆናቸውን (በልቤ ያመንኩ ስሆን) የምስክርነት ቃሌን እሰጣለሁ፡፡
ከንግግር ሁሉ እውነተኛው ንግግር የአላህ ቃል የሆነው ቁርኣን ነው! ከመንገዶች ሁሉ ትክክለኛው መንገድ (እምነት) የመልዕክተኛው የነቢዩ ሙሐመድ መንገድ (እምነት) ነው፡፡
የነገሮች ሁሉ አደገኛ በሀይማኖት ላይ አዲስ ፈጠራ (ቢድዓ) ማምጣት ነው! በሀይማኖት ላይ ፈጠራ (ቢድዓ) ሁሉ “ከነቢዩ ያልተለመደ” መጤ ነው፤ መጤ የተባለ በሙሉ ጥመት ነው፤ የጥመት ጎዳና በሙሉ የእሳት ነው።

ከዚህ በመቀጠል
በዚህን ጊዜ እንደሚታወቀው በብዛት በተጨባጭ እንደሚታየውም በአላህና በመልክተኛው ክልክል የተደረገው እንደተፈቀደ ነገር፤ የተፈቀደው ደግሞ እንደተወገዘ ነገር የሚታይበት ተጨባጭ ነው የሚታውየው። ለዚህም ያለ በቂ እውቀት ዝና እና ተወዳጅነትን ፍለጋ ብይን (ፈትዋ) የሚሰጡ አላዋቂ መሀይማን (ጃሂሎች) ዘንድ ሙፍቲ ተደርገው የተቀመጡ በስሜትና በመሀይማን ጭፍን ድጋፍ ሀቅን ላለመቀበል በትቢት የተወጠሩ፤ ያለ ደረጃቸው በመሀይማን ሸይኽና ኡስታዝ ተብለው የተሰቀሉ ብልሽትን የሚያስፋፉ (የፈሳድ) ሙፍቲዎች አሉ፡፡

ታዲያ እንዲህ ያሉ የጥመት ብይን (ፈትዋ) የሚሰጡ ሰዎችን ሀቅ ፈላጊውን ሚስኪኑን ህዝብ፤ በእንዲህ ያለ ፈትዋቸው ሲያስቱ ዝም ብሎ ማየት የአላህን ሀቅን ግልፅ የማድረግ አማና በአግባቡ አለመወጣት ከመሆኑም ባሻገር፤ የተወገዘን ንግግር የሚናገሩና በተወገዘ ነገር ላይ ይፈቀዳል ብለው ያለ እውቀት በድፍረት ፈትዋ የሚሰጡ ሰዎችን ባለማውገዛችን ከአይሁዶች እንዳንመሳሰል ያሰጋል፡፡ አላህ እነዚያ ከበኒ ኢስራኢል ከሀዲ የሆኑት የተረገሙበትን ምክንያት እንዲህ በማለት ገልፆልናል፡-

﴿لُعِنَ الَّذِينَ كَفَرُوا مِنْ بَنِي إِسْرَائِيلَ عَلَى لِسَانِ دَاوُودَ وَعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ  ذَلِكَ بِمَا عَصَوْا وَكَانُوا يَعْتَدُونَ٧٨كَانُوا لَا يَتَنَاهَوْنَ عَنْ مُنْكَرٍ فَعَلُوهُ ﴾ [المائدة: 78-79]

ከኢስራኢል ልጆች እነዚያ የካዱት በዳውድና በመርያም ልጅ በዒሳ ምላስ ተረገሙ፡፡ ይህ ትእዛዝን በመጣሳቸውና ወሰንን የሚያልፉ በመሆናቸው ነው፡፡ ከሰሩት መጥፎ ነገር አይከላከሉም ነበር፡፡” አልማኢዳ 78-79

ይህ በመሆኑም አንዱ ሲሳሳት ሌላኛው ተው! ማለት ግድ ይለዋል!፡፡ በመሆኑም ነሺዳን በተመለከተ የተሰጠውን የተሳሳተ ፈትዋ በቁርኣንና በሶሂህ ሀዲስ፤ በኢስላም ሊቃውንቶች የጋራ ስምምነት (ኢጅማዕ) ስህተት መሆኑን ለህዝበ ሙስሊሙ በተቻለ መጠን ግልፅ የተደረገ ሲሆን፤ ነሺዳን ሀላል ለማስመሰል የተነሱ ብዥታዎች ላይም አንድ በአንድ መልስ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

ይህን ሶፍት ኮፒ/PDF አንብበው ለሌሎች በማሰራጨት ሌሎችንም ከነሺዳ ብዥታ ይታደጉ!!
ለአስተያየትና ለጥቆማ የሚከተለውን የኢሜይል አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡-
Ibn.shifa11@gmail.com
PDFን በዚህ ሊንክም 👇👇 ያገኙታል
https://t.me/IbnShifa/933
https://t.me/IbnShifa/1383

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa


✅  ረመዳንን ለመቀበል የሚረዱ 10 ነጥቦች

     ባለፈው ለማስታወስ እንደተሞከረው ረመዳንን ለመቀበል መጀመሪያ አላህን በመፍራት ውስጥን ማጥራት በጣም አስፈላጊ ነው ። አሁን ደግሞ አላህ ካለ ረመዳንን ለመቀበል የሚያዘጋጁ 10 ነጥቦችን እናያለን ። እነዚህ ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው : –

አንደኛ – አላህ በጤና በሰላም እንዲያደርሰን ዱዓእ ማድረግ
       ከነብዩ በዚህ ዙሪያ የተወራ ሐዲስ ቢኖርም የሐዲስ ሊቃውንቶች ደዒፍ ነው ያሉት ስለሆነ ትቼዋለሁ ። ነገር ግን ሰለፎች አላህ እንዲያደርሳቸውና እንዲቀበላቸው ዱዓእ ያደርጉ እንደነበር ተረጋግጧል ።

ሁለተኛ – ረመዳን በመምጣቱ መደሰት
           የአላህ መልእክተኛ ሶሓቦቻቸውን ረመዳን በመምጣቱ እንዲህ በማለት ያበስሩ ነበር : –
       " የተባረከው የረመዳን ወር መጣላችሁ,  መፆሙን አላህ ፅፎባችኋል ( ግዴታ አድርጎባችኋል ) በርሱ ውስጥ የጀነት በሮች ይከፈታሉ የጀሀነም በሮች ይዘጋሉ ………" ።
        ኢማሙ አሕመድ ዘግበውት ሸይኽ አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል ።

ሶስተኛ – ከረመዳን ለመጠቀም መቁረጥና ፕሮግራም ማውጣት
          አብዛኛው ሰው ለዱንያዊ ጉዳዩ ፕሮግራም ያወጣል ነገር ግን የአኼራውን ጉዳይ በዘፈቀደ ይሰራል ያውም ዲን አለው ከተባለ ። ብልጥ ማለት ለሚቀጥለው ሀገር የተዘጋጀ ማለት ነው ። በዝግጅቱ ውጤታማ ለመሆን በፕሮግራም መመራት ግድ ነው ። ከዚህ ውስጥ አንዱና ዋነኛው የረመዳንን ወር ቀኑና ማታውን ለመጠቀም ፕሮግራም ማውጣትና ወስኖ መቀበል ብልጠት ነው ።

አራተኛ – ስለረመዳን ህግጋቶች መማር
           ሙስሊም የሆነ ሰው አላህን በእውቀት ላይ ሆኖ ሊገዛው ግድ ይላል ። ለዚህ ነው አላህ መልእክተኛውን መጀመሪያ እወቅ ያላቸው ። በመሆኑም አንድ ሙስሊም አላህ በሱ ላይ ግዴታ ያደረገበትን ዒባዳ በእውቀት ላይ ሆኖ መፈፀም ግዴታው ነው ። በጅህልና በሚሰራው ስራ ዑዝር የለውም ። ምናልባት ከአቅሙ በላይ ሆኖበት ካልሆነ በስተቀር ። ዐሊም ባለበት በራሱ ስንፍና ያለእውቀት አበላሽቶ ቢሰራ ከመጠየቅ አይድንም ።
      የትኛውንም ዒባዳ ስንሰራ ጠይቀን ተምረን አውቀን መሆን አለበት ። የረመዳን ፆም ህግጋቶችን መማር ለምሳሌ የሚያበላሹትን ፣ አጅሩን የሚቀንሱትን ፣ ቀዳእ የሚያስፈርዱና እንዲሁም ለማፍጠር የሚፈቀድባቸው ሁኔታዎችና የመሳሰሉትን ማወቅ ግዴታ ነው ።

አምስተኛ – ተውበት አድርጎ መዘጋጀት
             ረመዳንን ለመቀበል ከማንኛውም ወንጀል ተውበት አድርጎ መመለስና መፀፀት ዳግም ላለመመለስ ቁርጥ ያለ አቋም መያዝ ያስፈልጋል ። አላህ ዘንድ ያለን ፀጋና ቱሩፋት እሱን በማመፅ ለማግኘነት ማሰብ ሞኝነት ነው ። አንድ ሙስሊም በረመዳን ወንጀሉ ተምሮ ምህረት ለማግኘት ወደ አላህ በሁለመናው መመለስ ይኖርበታል ። አላህ ወደርሱ የተመለሰን ይቀበላል እጥፍ ድርብ ምንዳም ይሰጣል ።

     አላህ ካለ ይቀጥላል : –
https://t.me/Khalid_Islamawi_Studio
https://t.me/Khalid_Islamawi_Studio
https://t.me/Khalid_Islamawi_Studio
https://t.me/Khalid_Islamawi_Studio


Forward from: Bahiru Teka
🔷  ተውበት ከማድረግ ምን እስከሚሆን ነው የምጠብቀው ?

አላህ በተለያየ ዘመን የተለያዩ መልእክተኞችን ልኮ ህዝቦችን አስጠንቅቋል ። እንቢተኝነታቸው ሲበዛ በአመፃቸው ሲዋልሉ ማናለብኝነታቸው ሲያይል አቅማቸውን ሊያሳያቸው የውርደት ካባ ሊያከናንባቸው የሱን ሀያልነት ሳይወዱ በግዳቸው እንዲቀበሉ ሊያደርጋቸው አይናቸው እያየ ምድር እንዲውጣቸው አውሎ ንፋስ እንዲያነሳቸው ከሰማይ የእሳት ዝናብ እንዲዘንብባቸው ከምድር የፈላ ውሃ እንዲፈልቅባቸው በማድረግ በዱንያ ላይ አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ለሌላ መማሪያ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል ። ነገር ግን የሰው ልጅ ቀልቡ ከድንጋይ የበለጠ የጠነከረ በመሆኑ ካለፈው ከመማር ይልቅ ይበልጥ በማመፅ የአላህን ህግ በመጣስ ለሌላ ጥፋት እራሱን በማዘጋጀት አሻፈኝ በማለት ከዘመን ዘመን ጥፋቱ እየባሰ ቅጣቱም ፉጡራንን እያመሰ ለእንሰሳትና አእዋፍት ተርፎ ምድር በሰው ልጅ አመፅ ሰላሟን አጥታ እያለቀሰች ነው ።
ማንኛውም የተፈጥሮ አደጋ መንስኤው የሰው ልጅ የመጥፎ ስራ ውጤት ነው ። ይህን አስመልክቶ አላህ በተከበረው ቃሉ በተለያዩ አንቀፆች ነግሮናል ።
ቀጥሎ ጥቂቶቹን እንመልከት :–
وَمَا أَصَابَكُم مِّن مُّصِيبَةٍ فَبِمَا كَسَبَتْ أَيْدِيكُمْ وَيَعْفُو عَن كَثِيرٍ
الشورى ( 30 )

" ከመከራም ማንኛውም ያገኛችሁ ነገር እጆቻችሁ በሠሩት (ኃጢኣት) ምክንያት ነው ፡፡ ከብዙውም ይቅር ይላል " ፡፡

አሁንም በሌላ አንቀፅ እንዲህ ይላል :-
« ظَهَرَ الْفَسَادُ فِي الْبَرِّ وَالْبَحْرِ بِمَا كَسَبَتْ أَيْدِي النَّاسِ لِيُذِيقَهُم بَعْضَ الَّذِي عَمِلُوا لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ»
الروم ( 41 )
" የሰዎች እጆች በሠሩት ኃጢኣት ምክንያት የዚያን የሠሩትን ከፊሉን ያቀምሳቸው ዘንድ መከራው በየብስና በባሕር ተገለጠ፤ (ተሰራጨ) ፡፡ እነርሱ ሊመለሱ ይከጀላልና "፡፡

የሰው ልጅ የአላህ ፀጋ ከምድርም ከሰማይም እየመጣለት አሻፈረኝ ሲል ወደ ቅጣት የሚቀይረው መሆኑን ሲነግረን እንዲህ ይለናል :-

« وَضَرَبَ اللَّهُ مَثَلًا قَرْيَةً كَانَتْ آمِنَةً مُّطْمَئِنَّةً يَأْتِيهَا رِزْقُهَا رَغَدًا مِّن كُلِّ مَكَانٍ فَكَفَرَتْ بِأَنْعُمِ اللَّهِ فَأَذَاقَهَا اللَّهُ لِبَاسَ الْجُوعِ وَالْخَوْفِ بِمَا كَانُوا يَصْنَعُونَ »
النحل ( 112)
" አላህ ጸጥተኛ፣ የረካች፣ ሲሳይዋ ሰፊ ኾኖ ከየስፍራው ይመጣላት የነበረችውንና በአላህ ጸጋዎች የካደችውን አላህም ይሠሩት በነበሩት ኃጢኣት የረኃብንና የፍርሃትን ቅጣቶች ያቀመሳትን ከተማ (መካን) ምሳሌ አደረገ " ፡፡

እነዚህ ሙሲባዎች አላህ ሰዎች ሲያምፁ ከሱ አምልኮት ሲርቁ ማናለብኝ ሲሉ የሚያመጣቸው የሱ ቅጣቶች ናቸው ። ወደርሱ ካልተመለሱ በቅጣት አለንጋ መገረፍ አይቀርም ።
ሙሲባ ሲመጣ አመፀኛውን ብቻ ለይቶ አይመታም ሁሉንም ይነካል ። ለዚህ ነው አላህ ለይቶ የማይነካውን ፈተና ተጠንቀቁ የሚለን ። ይህንንም በሚቀጥለው አንቀፅ እንመልከት: –

« وَاتَّقُوا فِتْنَةً لَّا تُصِيبَنَّ الَّذِينَ ظَلَمُوا مِنكُمْ خَاصَّةً وَاعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ »
الأنفال ( 25 )
" ከናንተም ውስጥ እነዚያን የበደሉትን ብቻ ለይታ የማትነካን ፈተና ተጠንቀቁ ፡፡ አላህም ቅጣቱ ብርቱ መኾኑን እወቁ "፡፡
ተመልከቱ አላህ በዐለም ላይ ያመጣው ሁሉንም ያዳረሰው በሽታ ፣ በየሀገሩ በጎርፍ የሚያልቀው ፣ በመሬት መንቀጥቀጥ የሚወድምው ከተማና መኖሪያው የነበረው ቤት ቀብሩ የሚሆነው ኸልቅ ፣ ለዘመናት በጆሯችን ስንሰማው የነበረውና አሁን በሀገራችን ላይ እየተከሰተ ያለው ርእደ መሬት ( የመሬት መንቀጥቀጥ ) መንስኤው የኛ ወንጀል ነው ሩቅ ማሰብ አያስፈልግም ። በጣም የሚያሳዝነው ሶሞኑን በጋሞ ከ300 በላህ ሰዎች በዚሁ መቅሰፍት አልቀዋል ። ሌሎች የመሬት መንሸራተት በሚል ሬሳቸው ጠፍቶ ቀርቷል ። አልቆመም አሁንም የማንቂያ ደወሉ እየተዛመተ ወደ ደሴ ከተማ ደርሶ ንብረት አውድሟል ። ታዲያ አሁን ከሰማይ የቅጣት እሳት እንዳይዘንብ ያልተፈራ መቼ ሊፈራ ነው ? ሁላችንም ተውበት አድርገን ወደ አላህ ተመልሰን ልንለምነው ይገባል ። በተቻለን አቅም ከጥፋቱ ሜዳ ርቀን ሰዎች እሱን በብቸኝነት እንዲያመልኩ ወደ ነብዩ ሱና እንዲመለሱ ዳዕዋ ልናደርግ ይገባል ። ከተለያዩ ወንጀሎች ርቀው ተውበት አድርገው ወደ አላህ እንዲመለሱ ማስታወስ የግድ ነው ። ይህ ሀላፊነት በነዋይ የሰከሩት ፣ እውቅና ፍለጋ ከአቋማቸው የተንሸራተቱት ይወጡታል ማለት ቂልነት ነው ። በመሆኑም ሀላፊነቱ በተውሒድ ተጣሪዎች ጫንቃ ላይ የወደቀ እውነታ ነውና የነብያት ወራሾች ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሀላፊነታቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል ።

ካልሆነ መጠበቅ ያለብን የባሰ ነገር ነው ።‼

http://t.me/bahruteka


Forward from: Bahiru Teka
✅ አስተማሪና አስገራሚ ገጠመኝ

አንድ አላህ ሪዝቁን ያሰፋለት አባት ልጁን ይዞ ለማዝናናት በመኪና ይወጣል ። የሚፈልገው ቦታ ወስዶ እያዝናናው እያለ የሶላት ሳአት እየደረሰ መሆኑን ሲያይ ልጁን ይበቃል የሶላት ሳአት ደርሷል ብሎት ይወጣሉ ። በቅርብ ወደ ሚገኝ መስጂድ እየሄደ እያለ ከእግረኛ መንገድ ወጣ ብሎ አንድ የ9ኝ አመት አካባቢ የሚሆን ፀጉረ ሉጫ በጣም የሚያምር ልጅ ፊት ለፊቱ ትንሽ ቆስጣ ፣ ካሮትና ጎመን በትንሽ የሱፍራ አይነት ላስቲክ ተቀምጦ ልጁ ግራ እጁን አጥፎ በጉልበቱ ላይ አድርጉ አንገቱን ደፍቶ በቀኝ እጁ ጠጠር እየወረወረ ያያል ።
መኪናውን አቁሞ ቀስ ብሎ ጠጋ ብሎ ይሄ ምንድነው ብሎ ይጠይቀዋል ? ልጁም የሚሸጥ ነው ይለዋል ። እንደ መደንገጥ ብሎ ዋጋውን ይጠይቀዋል ። ልጁም የየአንዳንዱን ዋጋ ይነግረዋል ። ሰውየው ከተጠየቀው በላይ ለየአንዳንዱ መቶ መቶ ብር ሰጥቶት በፌስታል ያስገባቸዋል ። ልጁም ይሄ ሁሉ አያስፈልግም ዋጋው ትንሽ ነው ይላል ። ችግር የለም ጎበዝ የኔ ልጅ በጣም ጎበዝ ነህ እናትህ በደንብ እንድታመጣ ንገራት ሌላ ጊዜም እገዛሀለሁ ብሎት ሊሄድ ሲል ልጁ ተነስቶ ይቆምና እጁን ዘርግቶ አላህ ይስጥልኝ ብሎ ወደ እናቱ ሊሮጥ ሲል እጁን ያዝ አድርጎ ቆየኝ ብሎት ወደ መኪናው ሄደ ።
ሰውዬው ልጁ ሲነሳ ያደረገው ጃኬትና ሱሪ እንዲሁም ጫማ የተቀዳደዱ መሆናቸውን አይቶ ነበር ። መኪናው ጋር ሄዶ እቃውን መኪና ውስጥ አድርጎ ልጁን ከሚኪና አውርዶ ይዞት መጣ ። ለልጁ በመኪና ሄደው ልብስ እንደሚገዙ ነግሮት የለበሳቸው ልብሶች ለዚህ ልጅ አውልቆ እንደሚያለብሰው ነገረው ልጁም ሌላ ከገዛህልኝ እሺ አለ ። ይዞት መጣ የልጁን ጫማና ሱሪ አውልቆ አለበሰው ከዛም የልጁን ጃኬት አውልቆ ፊቱን አዙሮ ከኪሱ በዛ ያለ ብር አውጥቶ ኪሱ ውስጥ አደረገና አልብሶት አሮጌዎቹን በፌስታል አድርጎ እዛው አስቀምጦለት ባዶ እግሩን የሆነውን ልጁን አቅፎ ወደ መኪናው አቀና ።
ምስኪኑ ልጅ የተደበላለቀ ስሜት እየተሰማው ልብሶቹን አያቸው ። ልጅነቱ መጥቶበት እጆቹን በኪሱ ከቶ ራመድ ሊል ሲል ብሮቹ እጁ ውስጥ ገቡ አውጥቶ ሲያየው ብዙ ብር ነው ። ጊዜ አልወሰደም ሮጦ ሰውየው ጋር ሄደ አባባ ጃኬቱ ኪስ ውስጥ ብዙ ብር ነበር እንካ አለው ። ሰውየውም ችግር የለም ረስቼው አይደለም አውቄ ነው ለእናትህ ስጣት አለው ። ልጁም አስደንጋጭና አስገራሚ መልስ ሰጠው ።
ቅድም እንድሰራ አበረታተኸኝ አሁን ግን እንድለምን እያደረግኸኝ ስለሆነ አልፈልግም እንካ ብሎት ብሮቹን ጥሎበት ሄደ ። ሰውየውም በሰማውና ባየው ነገር ተገርሞ ልጁን ይዞ ወደ ሱቅ ሄደ ። !!!
ሱብሓነላህ ለልጁ ብሩህ አእምሮና ለሰውዬው ቅን ልቦና የሰጠ ጌታ ጥራት ይገባው ። ለመሆኑ ምን ተሰማችሁ ?
አላህ በተሰጠን ፀጋ ወደርሱ የሚያቃርብ ስራ የምንሰራ ያድርገን ።

https://t.me/bahruteka


🏝 ተሰምቶ የማይጠገብ ህፃን
❴ይህ የአላህና የመልካም ተርቢያ ውጤት ነው። ትኩረት ለልጆች ይደረግ!❵

🏖 ላጤዎች ሆይ! ጥሩ አጋር በመምረጥ የልጆቻችሁን ሀቅ ከማግባታችሁ በፊት ጀምራችሁ ተጠባበቁ! ዱዓ አድርጉ!

🏝 አዲስ ሙሽሮች ሆይ! ከመውለዳችሁ በፊት ከዱዓ ጀምሮ ልምድ በመቅሰምም የምትወልዱትን ልጅ የተሻለ አድርጉ!

🏖 እናት እና አባት ሆይ! የወለዳችኋቸውን ልጆች በአግባቡ በማሳደግ የቁርኣን ሀፊዞች፣ ኡስታዞች፣ መሻይኾች፣ ኡለሞች... በአጠቃላይ የኢስላም ወታደሮች ለማድረግ ሰበብ አድርሱ!

💡 እስኪ አስቡት ልጃችሁ የአላህን ቃል በደንብ ሀፍዞ ከዛ ማታ ስትሰበሰቡ ወይም ጧት ስትነሱ ከቁርኣን እየመረጠ እንዲህ ለዛ ባለው ቆንጆ ድምፅ ቢያሰማችሁ ምን ያክል ያስደስታል።

🤲 አላህ ጥሩ ልጆችን በማፍራት ያበርታን!

▵▮▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰▯▴
⚙ 📝 أَبُـــو عِـمْــرَان ❨𝕒𝕓𝕦 𝕚𝕞𝕣𝕒𝕟❩

🏝 ••⇣⇣.  🏖   ••⇣⇣ 
╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞

🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy

ሀሳብ  ካለዎ 
⤵️⤵️⤵️⤵️
https://t.me/AbuImranAselefybot


Forward from: Ethio-Universities Salafi Community(EUSaCo)
🎆 አዲስ የተጀመረ የትምህርት ፕሮግራም🎇

✍ እነሆ በአላህ ፈቃድ በመላው ሀገሪቱ የሚገኝ ሰለፊይ የዩንቨርስቲ፣ኮሌጅ እና ሌሎች የትምህርት ተቋማት ኮሚኒቲን በአንድ አስተሳስሮ ትክክለኛውን እስላማዊ አስተምህሮ ለዑማው የማድረስ ዓላማን ሰንቆ የተነሳው የናንተው  " ኢዩሰኮ-EUSaCo" "እውቀት ከንግግርም ሆነ ከተግባር በፊት ነው" የሚለውን እስላማዊ መርህ ከግምት በማስገባት ማህበረሰቡን በእውቀት የማነጽ ስራ መጀመሩንና የመጀመሪያውን የኪታብ ደርስ በተሳካ ሁኔታ በ Online ማጠናቀቁን ልብ ይሏል‼️  አሁንም በአረህማኑ እገዛ "ኢዩሰኮ-EUSaCo" አዲስ የደርስ ፕሮግራም ወደናንተ እያደረሰ መሆኑን ሲያበስራችሁ በታላቅ ደስታ ነው!!

🎯 የሚሰጡት ትምህርቶች

📚 صفة صلاة النبي صلى الله عَلَيْهِ وَآلِهِ وَسَلَّم
✍ تأليف : محمد ناصر الدين الألباني(رحمه الله)
📖  የኪታቡ pdf 👇👇
t.me/EUSaCochannel/176

📚حائية الإِمَامِ ابْنِ أَبِي دَاوُدَ فِي السُّنَّةِ
📖የኪታቡ pdf 👇👇
t.me/EUSaCochannel/177

🎤 በአቡ ሀመዊያህ ሸምሱ
ጉልታ(ሀፊዘሁሏህ)

📅 ዘወትር ጁምዓና ቅዳሜ
⏰  ከምሽቱ 3:30 ጀምሮ(በኢትዮ.)
🕌 በ online የሚሰጥ ይሆናል‼️

♻️ ከዚህ በፊት በ"ኢዩሰኮ-EUSaCo" የተሰጠን ደርስ ለማግኘት👇👇
t.me/EUSaCochannel/123

👌 በተቃና ኒያ ትምህርቱን በመታደምንና መልዕክቱን በማሰራጨት የምንዳው ተቋዳሽ እንሁን‼️

🏝 •⇣⇣.  🏖   •⇣⇣ 
╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞

🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️

t.me/EUSaCochannel
t.me/EUSaCoGroup

#Share    #ሼር   #EUSaCo #ኢዩሰኮ


🚥 ሸሪዓዊ መስተፋቅር
🌷🌺🌷🌹🌷💐🌷


➜ ከሽርክ ተግባራት ውስጥ አትቲወላ (መስተፋቅር) የሚለው የሚገኝበት ሲሆን ይህ በድግምተኛች በጂኒ አማካይነት የሚሰራ ነው።

🏝 አላህ ባልና ሚስቶች እንዲዋደዱ ኒካሕን ሚስጢሩ አድርጓል። የአላህ መልእክተኛ በተግባር አሳይተውናል እንኑርበት ይህ ሸሪዓዊ መስተፋቅር ነው

🎙 آلأُسْتَاذ بَحْرُو تَكَا أَبُو عٌبَيْدَة «حَفِظَهُ اللَّهُ»
🎙 በኡስታዝ ባህሩ ተካ አቡ ዑበይዳህ አላህ ይጠብቀው!


⎛አደራ! ሳያዳምጡ እንዳያልፉ ከኡስታዛችን ጋር ፈገግ እያልን እንከታተል!!!⎫

📚ከአል’ኢርሻድ ደርስ ተቀንጭቦ የተወሰደ

ለተጨማሪ ⬇️ ያንብቡ ↙️

htt.me/AbuImranAselefy/8919' rel='nofollow'>u>tps://t.me/AbuImranAselefy/8919


Forward from: [ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
ዱዳ ሸይጧን እና ተናጋሪ ሸይጧን?!

قال شيخ الإسلام ابن تيمية "…سكت وكتم الحق والساكت عن الحق شيطان أخرس" اهـ مجموع الفتاوى

ኢብኑ ተየሚያ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል፦
"… ዝም አለ። ሀቅንም ደበቀ። ሀቅን ከመናገር የለገመ ዱዳ ሸይጧን ነው።"

وقال العلامة ابن القيم "وأي دين وأي خير فيمن يرى محارم الله تنتهك وحدوده تضاع ودينه يترك! وسنة رسول الله صلى الله عليه وسلم يرغب عنها وهو بارد القلب ساكت اللسان شيطان أخرس كما أن من تكلم بالباطل شيطان ناطق" اهـ إعلام الموقعين


ኢብኑል ቀዪም አላህ ይዘንላቸው እንዲህ ብለዋል፦
"ምን አይነት ዲን ነው?! ምን አይነት ጥሩነት ነው?! የአላህ ክልክሎች ሲደፈሩ፣ ድንበሮቹ ሲበላሹ፣ ዲኑ ወደ ሃሊት ሲተው፣ የመልእክተኛው (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሱና ሰዎች ችላ እያስባሏት፣ እያየ ልቡ ቀዝቃዛ (የማይናደድ)፣ ምላሱ ዝም ያለ (መጥፎን የማይቃወም)፣ ዱዳ ሸይጧን (ሀቅን የሚደብቅ) ይሆናል። ባጢልን የሚያስተምርም ተናጋሪ ሸይጧን እንደሆነው ሁላ።"

ስለዚህ ወንድሜ በዚህ ዘመን የሰው ሰይጣኖች በዝተዋል። ዝም የሚሉት ሰይጣናት ስራቸውን በዝምታ ነው የሚሰሩት። መጥፎ ሲሰራ አይተው አይቃወሙም። ከጥሩ ነገር ወደኋላ ሲባል አይተው አይናገሩም። ወደ ተውሒድ እና ወደ ሱና አይጣሩም።

ተናጋሪ የሰው ሰይጣናት ደግሞ አጭበርባሪዎቹ ናቸው። በዲን የሚነግዱ። የቁርአንን እና የሀዲስ መልእክት የሚያንሻፍፉ እና በሰዎች መካከል ብዥታን የሚነዙ።

t.me/abuzekeryamuhamed


Forward from: " ዓብዱረህማን ዑመር"
በውስጥህ የሚመላለስ ማንኛውንም የቸገረህ ነገር ሸይኽ ዑሰይሚን አንጀት አርስ መፍትሔ ይሰጡታል።

قال تعالى :
{ ۞ أَتَأۡمُرُونَ ٱلنَّاسَ بِٱلۡبِرِّ وَتَنسَوۡنَ أَنفُسَكُمۡ }
البقرة 44
አላህ እንዲህ ብሏል፦
« ሰዎችን በበጎ ሥራ ታዛላችሁ ነፍሶቻችሁንም ትረሳላችሁን? »
አል በቀራ - 44
✅ يقول الشيخ ابن العثيمين في تفسير لهذه الآية
▫️ أينا الذي لم يسلم من المنكر!

لو قلنا: لا ينهى عن المنكر إلا من لم يأت منكراً لم يَنهَ أحد عن منكر؛
ولو قلنا: لا يأمر أحد بمعروف إلا من أتى المعروف لم يأمر أحد بمعروف؛
ሸይኽ ዑሰይሚን (ረሒመሁላህ) ይሄን አንቀፅ ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ፦
❝ ማንኛችን ነው ከመጥፎ ነገር ሙሉ በሙሉ ንፁህ የሚሆነው??
- በመጥፎ ነገር ምንም ተሳስቶ የማያውቅ ካልሆነ ከመጥፎ ነገር መከልከል የለበትም ከተባለ አንድም ከመጥፎ የሚከለክል አይኖርም።
- መልካምን ሁሉ የሰራ ብቻ ነው በመልካም የሚያዘው ካልን በመልካም የሚያዝ አይኖርም።

ولهذا نقول: مُرْ بالمعروف، وجاهد نفسك على فعله،
وانْهَ عن المنكر، وجاهد نفسك على تركه..
انتهى
❝ ስለዚህም ፦ በመልካም እዘዝ እሱን በመስራት ነፍስህን ታገል። ከመጥፎ ከልክል እሱን በመተው ነፍስህን ታገል እንላለን! ❞ ይላሉ።
📚المصدر : تفسير سورة البقرة
الشريط السادس الوجه الثاني
/ الدقيقة 17:47
للشيخ محمد صالح العثيمين - رحمه الله】

http://t.me/Abdurhman_oumer


Forward from: Wolkite University yeselefiyah channel
👉  ሺዓዎችና ዓሹራእ

    ዓሹራእ ሲታወስ በዋነኝነት የሚታወሰው የሑሰይን ኢብኑ ዐልይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ ከርበላእ ላይ መገደል ነው ። ሑሰይን ከርበላእ ላይ የተገደለው ሙሐረም 10/61ኛው አመተ ሂጅሪያ ላይ ነበር ።
    የሑሴይን መገደል መንስኤ የነበረው ለየዚድ ኢብኑ ሙዓዊያ ኢብኑ አቡ ሱፍያን ሙባየዓ አላደርግም ማለቱ ነበር ። በኢስላም ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለው የሐሰን ኢብኑ ዐልይ ለሙዓዊያ የመሪነቱን ቦታ መልቀቁ ( ተናዙል )  ማድረጉ ነው ። ዑስማን ኢብኑ ዐፋን በዐብዱላሂ ኢብኑ ሰበእ አል የሁዲይ የተንኮል መረብ ከተገደለ በኋላ ዐልይ የኸሊፋነቱን ቦታ በሶሓቦች ግፊትና ውትወታ ተረክቦ ሁኔታዎችን ለማረጋጋት እየሰራ ባለበት ወቅት ሙዓዊያ የሻም ዋሊ ( አስተዳደር ) ነበርና ለዐልይ የዑስማን ገዳዮች ለፍርድ እንዲቀርቡ ጥያቄ ያቀርባል ። ዐልይም መጀመሪያ ሙባየዓ ማድረግ እንዳለበትና ሁኔታዎች ከተረጋጉና ገዳዮቹ በህዝብ ውስጥ ተደብቀው ስላሉ መለየት በሚቻልበት ወቅት ለፍርድ እንደሚቀርቡ ይገልፅለታል ። ሙዓዊያም ምናልባት መዲና ያለው ሁኔታ ካልተረጋጋና አቅም ከሌለው ሀላፊነቱን ለሱ እንዲሰጠውና እሱ ገዳዮቹን ለፍርድ ሊያቀርብ በሚችልበት አቅምና አቋም ላይ መሆኑን በመግለፅ ይህ ሳይሆን ሙባየዓ እንደማያደርግ ለዐልይ ያሳውቃል ። ይህ አለመግባባት ሳይፈታ ዐልይ ኢብኑ አቢጧሊብ ዐብዱራሕማን ኢብኑ ሙልጂም በሚባል ኻሪጂ ይገደላል ። በቦታው ሐሰን ኢብኑ ዐልይ ሙባየዓ ተደረገለት ኸሊፋም ሆነ ።  ነገር ግን ከሙዓዊያ ጋር የነበረው አለመግባባት በቀላሉ የሚፈታ አልነበረምና ሐሰን ለሙዓዊያ መሪነቱን አስረከበ ።
     ይህ የሐሰን ተግባር ለሑሰይን አላስደሰተውም ። ነገር ግን ታላቁ ነውና ምንም ማድረግ አልቻለም ለሙዓዊያ ሙባየዓ አደረግ ። በዚህም ሀገር ሰላም ሆነ ሙስሊሞች ኡፈይ አሉ ። በዚህ ሁኔታ ነገሮች እየሄዱ እያሉ ሙዓዊያ መሪነቱን ለልጁ የዚድ አሳልፎ ሰጠ ። የዊላያት መሪዎችና የጦር አዛዦች እንዲሁም ታዋቂ ሶሓባዎች ለልጁ ሙባየዓ እንዲያደርጉ ጠየቀ ። ሑሰይን ኢብኑ ዐልይ ለየዚድ ሙባየዓ እንደማያደርግ ግልፅ አደረገ ። በዚህን ጊዜ የዚድ ለመዲናው አስተዳዳሪ ከሑሰይን ሙባየዓ እንዲቀበልለት ትእዛዝ አስተላለፈ ። ሑሰይንም ሁኔታው ስላላማረው መዲናን ትቶ ወደ መካ ተሰደደ ። የዚህን ጊዜ ኢራቅ ያሉ የሙዓዊያ ተቋዋሚ ፋርሳዊያን ( ሺዓዎች ) ሑሰይንን ወደ እነርሱ እንዲመጣና መሪያቸው እንዲሆን መወትወት ጀመሩ ። ሑሰይንም ለመውጣት አሰበ የኩፋ ሰዎች በየቀኑ ወደ ሑሰይን ይልካሉ ። ይህ ሁኔታ ያላማረው የዚድ የሑሰይንን እንቅስቃሴ መከታተል ጀመረ ።
    ሑሰይንም የአጎቱን ልጅ ሙስሊም ኢብኑ ዓቂልን ወደ ኩፋ ሄዶ ነገሮችን እንዲያጣራ ላከው ። ሙስሊም ኩፋ እንደደረሰ በጣም ጥሩ አቀባበል ተደረገለት ለሑሰይን ሙባየዓ አደረጉ ። የዚህን ጊዜ ለሑሰይን መምጣት እንዳለበትና ሙባየዓ እንደተደረገለት ገልፆ ላከለት ።
     የዚድ የሙስሊም ኢብኑ ዐቂል ኩፋ መግባትና ሰዎች ( ሺዓዎች ) ለሑሰይን ሙባየዓ እያደረጉ መሆኑን በሰማ ጊዜ ዑበይዱላህ ኢብኑ ዚያድን የበስራና የኩፋ መሪ አድርጎ በመሾም ወደ ኩፋ እንዲሄድና የሆነውን ነገር አጣርቶ እርምጃ እንዲወስድ ላከው ። ወደ መዲናና መካ የሚገኙ ትላልቅ ሶሓቦችም ሑሰይንን ወደ ኩፋ እንዳይወጣ እንዲመክሩትና ሙባየዓ እንዲያደርግ እንዲነግሩት መልእክት ላከ ።
    ዑበይዱላህ ኢብኑ ዚያድ ወደ ኩፋ እንደመጣ ለወታደሮች በጣም ከፍተኛ ስጦታ ሰጠ ። ታዋቂ ሰዎችን አስጠርቶ ከሱ ጋር እንዲሆኑ የፈለጉት ነገር እንደሚያደርግላቸው ካልሆነ ግን አይቀጡ ቅጣት እንደሚቀጣቸው ገለፀላቸው ። ማንኛውም ሰው አዲስ ሰው እንዳያስጠጋ አስጠግቶ የተገኘ እርምጃ እንደሚወስድበት ተናገረ ። ቀጥሎ በስራና ኩፋ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ አዘዘ ። ማንኛውም አዲስ ሰው ከተገኘ ወደርሱ እንዲቀርብ ትእዛዝ ሰጠ ። ቀጥሎ አሉ የተባሉ ታዋቂ ሰዎችን በተለያየ ጥቅማጥቅም በመያዝ ሙስሊም ኢብኑ ዐቂል ያለበት እንዲያደርሱትና ከሱ ጎን የቆሙ ሰዎችን እንዲለዩለት አደረገ ።
   ወዲያውኑ ሙስሊም ኢብኑ ዐቂል ያለበት ቦታ ጦቀሙት ። ወደ ሙስሊም ኢብኑ ዐቂል ጉዞ ቀጠለ ደረሰበትም ። ሙስሊም ኢብኑ ዐቂል የተከሰተው ነገር ሲያይ ማመን አቃተው እነዚያ ቃል የገቡና ሑሰይንን እንዲያስመጣ ያዘዙት ሺዓዎች ክደውታል ። ዑበይዱላህ እጅ እንዲሰጥ ጠየቀው አላደረገውም ተገደለ ። የሚቀጥለው ስራ የሑሰይንን መምጣት መጠበቅ ነው ። በተለያዩ መንገዶች ጠባቂ አደረገ ። ስለሙስሊም መገደል እንዳይደርሰው አደረገ ።
    ሑሰይን ከመካ ወደ ኩፋ እንቅስቃሴ ጀመረ ። ትላልቅ ሶሓቦች እንዳይሄድ ከለከሉት ። ከእነዚህ ውስጥ : –
– ዐብዱላሂ ኢብኑ ዐባስ
– ዐብዱላሂ ኢብኑ ዑመር
– ጃቢር ኢብኑ ዐብዱላሂ
– ዐብዱላሂ ኢብኑ ዙበይር
– አቡ ሰዒድ አል ኹድርይ
    እና ሌሎችም ግን አልተሳካም ።
    የሑሰይን መንቀሳቀስ ተሰማ ዑበይዱላህ ኢብኑ ዚያድ 1000 ፈረሰኛ እሱን ለመጠባበቅ ላከ ። ሌላ ጦር ደግሞ ዑመር ኢብኑ ሰዕድን መሪ አድርጎ ላከ ። ለዚህ ጦር እጅ ከሰጠ ይዘው እንዲያቀርቡት ካልሆነ እንዲገሉት ትእዛዝ ሰጠ ። ሑሰይን ወደ ኩፋ በቀረበ ጊዜ የአጎቱ ልጅ መገደል ፣ የኩፋ ሰዎች ከዑበይዱላህ ኢብኑ የዚድ ጎን መቆማቸውንና የአጎቱን ልጅና እሱንም እንደካዱዋቸው የሙስሊም ኢብኑ ዑቅባ ደጋፊዎች ሀኒእ ኢብኑ ዑርዋን ጨምሮ ሁሉም መገደላቸውን ሰማ ። ብዙም ሳይቆይ ከዑመር ኢብኑ ሰዕድ ጦር ጋር ተገናኘ ። እነዚያ ወትውተው ከመካ ያስወጡት ሺዓዎች አዘጋጅተው ለጅብ ሰጥተውታል ።
     የዚህን ጊዜ ከሱ ጋር ያሉትን ማስጨረስ አልፈለገም ሙሉ በሙሉ ሀሳቡን ቀይሮ ሶስት አማራጭ ለዑመር ኢብኑ ሰዕድ አቀረበለት ። አማራጮቹ የሚከተሉት ነበሩ : –
– እንዲተውትና ወደ መካ እንዲመለስ
– ወደ ድንበር ሄዶ እንደማንኛውም ሙስሊም ድንበር እንዲጠብቅ ( ሀገር ጠባቂ ወታደር እንዲሆን )
– ወደ ሻም ሄዶ ከየዚድ ጋር ተነጋግሮ እንዲግባባ የሚል ነበር ። 
    ዑመር ይህን ሲሰማ በጣም ደስ ብሎት ለዑበይዱላህ ኢብኑ ዚያድ ላከለት ። ይሁን እንጂ በሙስሊሞች ደም የሚታጠበው ዑበይዱላህ ኢብኑ ዚያድ እጅ ካልሰጠ እንዲገድለው አዘዘ ። ዑመር ለሑሰይን እጅ እንዲሰጥ ጠየቀው ሑሰይንም አይደረግም አለ ። በሙሐረም 10 ኛ ቀን በ61ኛው አመተ ሂጅሪያ ሺዓዎች ከመካ መሪያችን ሁን ብለው አውጥተው ከርበላእ ላይ እንዲገደል አደረጉት ።
    ይህን ቀን ነው ሺዓዎች ከርበላእ ላይ ራቁታቸውን ሆነው ራሳቸው እየገረፉ ለሑሰይን ሞት ሐዘን እያሉ  ያ ሑሰይን ብለው የሚጮኹት ።

      https://t.me/bahruteka


👉👂 "አላህ ከዐርሽ በላይ ስለመሆኑ በግራመር (በነህው)"


[Clip:5:20 Mins]

🎙🎙በሸይኽ ዐብዱል-ሐሚድ አል-ለተሚይ (ሀፊዘሁሏህ)
https://t.me/abdulham/2307


/


እየሩሳሌም ሶስተኛው የሙስሊሞች ቅዱስ ስፍራ

አንብበው ሲጨርሱ  ሼር በማድረግ  ለሌሎችም ያዳርሱ
እየሩሳሌም በሙስሊሞች ዘንድ ከመካ እና ከመዲና ቀጥላ ሶስተኛዋ ቅድስት ስፍራ ናት፡፡ ሙስሊሞች ለእየሩሳሌም የሚሰጡት ትልቅ ቦታን ባለመረዳት ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖች ሙስሊሞች የእየሩሳሌም ጠላት እንደሆኑ አድርገው ያስባሉ፡፡ እውነታ ግን እየሩሳሌም ለሙስሊሞች የተከበረውን መስጂደል አቅሳን ይዛ የምትገኝ የተከበረች ስፍራ ናት፡፡
ሙስሊሞች ወደ መካ እና መዲና እንደሚጓዙት ሁሉ ወደ እየሩሳሌም በመጓዝም መስጂደል አቅሳን ማየትን ይሻሉ፡፡በወራሪዋ እስራኤል አማካኝነት ይህ የተከበረ ቦታ በህፃናት፣በአዛውንቶች እና በሴቶች ደም ሁሌም እንዲጨቀኝ ቢደረግም አንድ ቀን ከወራሪዋ እስራኤል ነፃ የሚወጣበት ቀን መምጣቱ አይቀርም፡፡
  አለም ላይ የሚገኙ ሙስሊሞች ለእየሩሳሌም የሚሰጡትን ቦታ ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖችም ጠንቅቀው ሊረዱት ይገባል ስለ ፍልስጤማውያን ስንጮህ በግፍ መሬታቸውን በወራሪዋ እስራኤል ስለተነጠቁ ብቻ ሳይሆን  ወይም ሙስሊም ስለሆኑ ብቻ ሳይሆን ወይንም አረብ ስለሆኑ ሳይሆን በወራሪዋ እስራኤል  በጉልበት የተያዘብን በእየሩሳሌም ምድር የሚገኘው መስጂደል አቅሳም የፍልስጤማውያን ብቻ ሳይሆን   የመላው ሙስሊም ቅዱስ ስፍራ በመሆኑ ነው

እያንዳንዱ ሙስሊም ስለ እየሩሳሌም ፤ስለ መስጂደል አቅሳ  ዘወትር ፀሎት ያደርጋል፡፡ ከግፈኞቹ ፂዬናውያን ነፃ ወጥታ ሁሉም ወደ እየሩሳሌም ተጉዞ በመስጂደል አቅሳ ሰላቱን ሊሰግድ ይናፍቃል፡፡

የሙስሊሞችን እና የእየሩሳሌምን  ጥብቅ ትስስር ለመረዳት  የተወሰኑ ነጥቦችን በመጥቀስ እንመልከት

1. መስጂድ አል-አቅሷ  የቦታና የመስጂድ ሥም ብቻ ሳይሆን ከእስልምና ሃይማኖት ጋር የሚያገናኙት በርካታ ቁምነገሮች አሉ፡፡ አምላካችን አላህ (ሱ.ወ.) መስጂድ አል-አቅሷን እና  ዙሪያውን በሱ የተባረከና የተቀደሰ አካበቢ መሆኑን በቁርአን ላይ ገልፆልናል፡፡

سُبْحَانَ الَّذِي أَسْرَىٰ بِعَبْدِهِ لَيْلًا مِّنَ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ إِلَى الْمَسْجِدِ الْأَقْصَى الَّذِي بَارَكْنَا حَوْلَهُ لِنُرِيَهُ مِنْ آيَاتِنَا ۚ إِنَّهُ هُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ ﴿١

ያ ባሪያውን ከተከበረው መስጊድ ወደዚያ ዙሪያውን ወደ ባረክነው ወደ ሩቁ መስጊድ በሌሊት ውስጥ ያስኼደው (ጌታ) ጥራት ይገባው፡፡ ከተዓምራቶቻችን ልናሳየው (አስኼድነው)፡፡ እነሆ እርሱ (አላህ) ሰሚው ተመልካቺው ነው፡፡((አል-ኢስራእ ፡1)

2. ሌላው አል-አቅሷን ከሙስሊሞች የሚያስተሳስረው የኢስራእና ሚዕራጅ ምድር መሆኑ ነው፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ወደ ሰማዩ ዓለም ጉዞ ባደረጉ ጊዜ ከመካው መስጂድ ወደ  እየሩሳሌም መስጂድ አልአቅሷ  ተጉዘዋል፡፡ ከዚያም በመነሳት ነበር ወደ ሰማዩ ዓለም የተጓዙት፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከመካ ወደ በይት አልመቅዲስ መጓዛቸው የቦታውን ታላቅነትና ቅድስና ያመለክታል፡፡ 

ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ወደ  እየሩሳሌም ወደሚገኘው አል-አቅሷ መስጂድ  በተጓዙበትም ወቅት ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.)  ከአላህ የተላኩትን ታላላቅ ነቢያቶችን  መሪ ሆነው አሰግደዋል፡፡ከነዚህም መካከል  ከነብዩላህ አደም ጀምሮ እስከ እየሱስ ክርስቶስ(አ.ሰ) ያሉት ነብያት ይገኙበታል፡፡

3.  የእየሩሳሌም ምድር በርካታ ታላላቅ የአላህ ነብያት የተላኩበት ምድርም ነው፡፡ አባታችን ኢብራሂምን (አብረሃም) (ዐ.ሰ) ጨምሮ ዳውድ(ዳዊት)፣ ሱለይማን(ሰለሞን)፣ ሙሳ(ሙሴ)፣ ኢሳ( እየሱስ ክርስቶስ ) (አ.ሰ) እና ሌሎችም ህዝቦች አላህን በብቸኝነት አንድ አድርገው እንዲገዙ ጥሪ እንዲያደርጉ ከአላህ የተላኩበት ምድር ነው፡፡

4 . እንደ አብዛኞቹ ዑለማኦች(የእስልምና ሊቃውንት)  ስምምነት በእየሩሳሌም  የሚገኘውን አል-አቅሷ መስጂድን ለመጀመሪያ ጊዜ የገነቡት አባታችን አደም (ዐ.ሰ.) ሲሆኑ ኋላ ላይ ግን ነብዩላህ ኢብራሂም (አ.ሠ) ካዕባን በድጋሚ እንደገነቡት ይህንንም መስጂድ (የፀሎት ቦታ) አስፍተውታል፡፡ በመቀጠልም የነብዩላህ ዳውድ(ዳዊት) ልጅ የሆኑት  ነቢዩ ሱለይማን(ሰለሞን) ሙሉ ግንባታውን በማደስ እንዳጠናከሩት  እና እንደገነቡት  በታሪክ ላይ ሰፍሮ ይገኛል፡፡

በምድር ላይ አላህን ለማምለክ ታስቦ በነብዩላህ ኢብራሂም) (አ.ሰ)የተገነባው የመጀመሪያው መስጂድ (የፀሎት ስፍራ)   መካ የሚገኘው አልሐራም (ከዕባ) መሆኑ ይታወቃል፡፡ አል-አቅሷ ደግሞ  በምድር ላይ የተገነባ ሁለተኛው መስጂድ (የፀሎት ስፍራ) ሲሆን በሱ እና በከዕባ መካከል የአርባ አመት ዕድሜ ብቻ ነው ያለው፡፡ ነብዩላህ ኢብራሂም ከልጃቸው እስማኤል ጋር በመካ ካዕባን ከገነቡ ቡኋላ ከ 40 አመታት ቡኋላ በእየሩሳሌምም ይህን መስጂደል አቅሳን (የፀሎት ስፍራ) አስፍተውታል፡፡ ከነብዩላህ ኢብራሂም ቀጥሎ ልጃቸው ይስሓቅ ቀጥሎም የልጅ ልጃቸው ያቆብ (ዐ.ሰ)  ወደ ግብፅ እስከሄዱበት ጊዜ ድረስ አላህን በብቸኝነት የሚያመልኩበትቦታ ሆኖ ቆይቷል፡፡

5.  እየሩሳሌም የሚገኘው አል-አቅሷ የመጀመሪያው የሙስሊሞች ቂብላ(የሰላት አቅጣጫ)  ነው፡፡ ነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ለአለም ህዝብ በነብይነት ሲላኩ የሙስሊሞች ቂብላ/የሶላት መቀጣጫ/ ወደ ከዕባ/መካ/ እንዲሆን ከመደረጉ በፊት ለአሥራ ስድስት ወይም ለአሥራ ሰባት ወራት ወደእየሩሳሌም ወደ መስጂደል አቅሳ  ዞረው ሰግደዋል፡፡ ካዕባ የሰላት አቅጣጫ ከመደረጉ በፊት ሙስሊሞች ወደ እየሩሳሌም በመዞር ነበር ሰላታቸውን የሚሰግዱት፡፡ ዛሬ ላይ ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖች ሙስሊሞች  ወደ መካ ካዕባ ዞራችሁ የምትሰግዱት ለጥቁሩ ድንጋይ ነው ብለው ባለማወቅ ውንጀላ ሲያቀርቡ  ሙስሊሞች በመጀመሪያ ፊታቸውን  ወደ እየሩሳሌም በማዞር ይሰግዱ እንደነበር ቢያውቁ ወደ አንድ አቅጣጫ መዞር የምንሰግድለት አምላክ አንድ ቦታ በመገኘቱ ሳይሆን  የአንድነት ተምሳሌት መሆኑን ይረዱ ነበር፡፡

6.  ጓዝ ተጭኖና ስንቅ ተቋጥሮ ለጉብኝትም ሆነ ለሶላት ከሚኬድባቸው ሶስት መስጂዶች ውስጥ   እየሩሳሌም የሚገኘው  አል-አቅሷ  መስጂድ አንዱ ነው፡፡ በዚህ በእየሩሳሌም በሚገኘው  በአልአቅሷ ውስጥ የሚሰገድ ሶላት በሌላው መስጂድ ውስጥ ከሚሰገደው በደረጃ በአምስት መቶ እጥፍ ይበልጣል፡፡  በአል-አቅሷ መስጂድ ውስጥ የሚሰገደውን ሶላት ሊበልጥ የሚችለው በመካ (መስጂድ አልሐራም) እና በመዲና የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) መስጂድ ውስጥ የሚሰገደው ሶላት ብቻ ነው፡፡ለዚህም ነው ሁሉም ሙስሊም ከመሞቱ በፊት ከመካ እና ከመዲና መስጂዶች ቀጥሎ ወደ እየሩሳሌም ተጉዞ በመስጂደል አቅሳ ለመስገድ የሚመኘው፡፡

7. በርካታ የነብዩ መሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ባልደረቦች እና  ትላልቅ ደጋግ ሰዎች የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) እየሩሳሌም ስለሚገኘው ስለ አል-አቅሷ ደረጃና ቅድስና ያስተማሩትን በመከተል ወደዚያ ሄደዋል፡፡ ጎብኝተውታል፡፡ ሰግደውበታል፡፡ አል-አቅሷ በታሪክ በተለያዩ ገዥዎች ሥር በቅብብሎሽ ከቆየ በኋላ በሙስሊሞች ቁጥጥር ስር የሆነው  በኸሊፋ ዑመር ኢብኑ አልኸጣብ (ረ.ዐ.) ዘመን ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ በርካታ ሶሓቦች በበይት አልመቅዲስ በመገኘት ተምረዋል፣ አስተምረዋል፡፡ እዚያው ቆይተው ከሞቱት ታላላቅ ሶሓቦች መካከል ዑባዳ ኢብኑ አስሷሚት እና ሸዳድ ኢብኑ አውስ (ረ.ዐ.) ይገኙበታል፡፡ የተቀበሩትም ከመስጂዱ ቅጥር ግቢ ውጭ በሚገኘው ባብ አር-ረሕመህ በሚሰኘው ቦታ ላይ ነው
Join and Share
👇👇
😍@khalid_islamawi_studio


0ረፋን መፆም ለማይችሉ
~
ዛሬ ዐረፋ ነው፣ ዙልሒጃ ዘጠኝ። ይህንን ቀን መፆም ትልቅ ዋጋ እንዳለው የሚታወቅ ነው። በተቻለ መጠን ሊያልፈን አይገባም።
በወር አበባ፣ በወሊድ፣ በህመም ሰበብ መፆም የማትችሉ ደግሞ ለመፆም ቁርጠኛ ውሳኔ ከነበራችሁ አትቆጩ። የምታመልኩት የልባችሁን የሚያውቅ ጌታ ነው። በኒያችሁ የሚፈፅሙ ሰዎችን አምሳያ ይመነዳችኋል። ይህንን የሚጠቁሙ መረጃዎች ብዙ ናቸው። ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦
"وهذه قاعدة الشريعة: أن من كان عازماً على الفعل عزما جازما، وفعل ما يقدر عليه منه، كان بمنزلة الفاعل".
"ይሄ የሸሪዐ ህግ ነው። አንድን ተግባር ለመፈፀም ቁርጠኛ ውሳኔን የወሰነና የሚችለውን ያደረገ ሰው በፈፃሚ ደረጃ ነው የሚሆነው።" [አልፈታዋ፡ 23/236]
=
@Khalid_islamawi_studio
@Khalid_islamawi_studio
@Khalid_islamawi_studio
@Khalid_islamawi_studio


ኡዱሒያ ጋር የሚያያዙ ተጨማሪ ነጥቦች
~
1ኛ፦ የሚታረደው እንስሳ ወንድ ብቻ አይደለም የሚሆነው፣ ሴትም ማረድ ይቻላል። ይሄ የዑለማእ ወጥ ስምምነት (ኢጅማዕ) ያለበት ጉዳይ ነው።

የታረደችው እንስሳ ሆዷ ውስጥ ፅንስ ካለ፣ ካልከበዳቸው መመገብ ይችላሉ። ነብዩ ﷺ ስለዚህ ጉዳይ ሲጠየቁ እንዲህ ብለዋል፦
كُلوه إنْ شِئتُم؛ فإنَّ ذَكاتَه ذَكاةُ أمِّه
"ከፈለጋችሁ ብሉት። የእሱ (የሽሉ) እርድ የእናቱ እርድ ነው።" [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 2827]
ማለትም የሷ ክፍል እንደመሆኑ እሷን ሐላል ያደረጋት እርድ እሱንም ሐላል አድርጎታል ማለታቸው ነው። "ከፈለጋችሁ" ነው ያሉት። ያልፈለገ ለሚፈልግ ሊሰጠው ካልሆነም ሊተወው ይችላል።

2ኛ፦ የሚታረደው እንስሳ ቀንድ ያለው መሆኑ ግዴታ አይደለም። በተፈጥሮው ቀንድ የሌለው ከሆነ ምንም ችግር የለውም።
3ኛ፦ ግልፅ ያልሆኑ ትንንሽ ነውሮች ያሉበትን ማረድ ይቻላል። በጣም አጥብቀን ራሳችንን ልናስቸግር ወይም የተሻለ እንስሳ ልናስመልጥ አይገባም።

4ኛ:- ውጭ ሃገር ለሚኖር ሰው በውክልና የምናርድ ከሆነ ባለ ኡዱሒያው አካል ዒድ ሳይሰግድ ቀድመን ማረድ የለብንም። ይቺን ፈትዋ ማየት ትችላላችሁ። https://t.me/ibnhezam/14606
ስለዚህ ባለ ኡዱሒያዎቹ አውሮፓና አሜሪካ የሚኖሩ ከሆኑ ከኛ ጋር በተመሳሳይ ሰዓት ስለማይሰግዱ እናቆየው። እስከ ዙልሂጃ 13ኛ ቀን ድረስ ማረድ ስለሚቻል ስጋት እንዳይገባን።

5ኛ፦ ስጋውን ከፊሉን ቤት ውስጥ ለእለት ምግብ ማዋል፣ ከፊሉን ማስቀመጥ፣ ከፊሉን ደግሞ ሶደቃ አድርጎ ለሰው መስጠት ይቻላል። 1/3ኛ ለእለት ምግብ፣ 1/3ኛ ለሚቆይ፣ 1/3ኛ ደግሞ ለሶደቃ የሚለው መረጃ የለውም። በዚህም ይሁን በሌላ በፈለገው መልኩ ማከፋፈል ይችላል።
ከፊል ዓሊሞች ትንሽም ቢሆን ሶደቃ መስጠቱ ግዴታ ነው ይላሉ። ነገር ግን አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው ሙሉውን መጠቀምም ይቻላል።
ስለዚህ ለምሳሌ ቤተሰብ የሚበዛበት ሰው እዚያው ሊጠቀመው ይቻላል ማለት ነው።
=
@Khalid_islamawi_studio
@Khalid_islamawi_studio
@Khalid_islamawi_studio
@Khalid_islamawi_studio


የኡዱሒያን እርድ የሚመለከቱ ጥቂት ወሳኝ ነጥቦች
~
ኡዱሒያ ማለት በዒደል አድሓ ቀን ወደ አላህ ለመቃረብ ታስቦ የሚታረድ እርድ ነው፡፡ ነብዩ ﷺ በተግባር ፈፅመውታል፡፡ መዲና ላይ አስር አመት ሲኖሩም ኡዱሒያን ያርዱ ነበር፡፡ [ሚሽካት፡ 1475] እንዲፈፀምም አዘዋል፡፡ ስለዚህ አቅም ያለው ሰው ሊፈፅመው ይገባል ማለት ነው፡፡ ነብዩ ﷺ “አቅሙ እያለው ኡዱሒያን ያላረደ ሰው መስገጃችንን እንዳይቀርብ” ብለዋል፡፡
ኡዱሒያ ብዙሃን ዑለማኦች ዘንድ የጠነከረች ሱና ነች። ከፊል ምሁራን ዘንድ ደግሞ ግዴታ ነች። ኢብኑ ተይሚያ - ረሒመሁላህ - ከሁለቱ ሃሳቦች የሚጎላው ግዴታ ነው የሚለው ነው ይላሉ። ግዴታም ቢሆን ታዲያ ያልቻለ ሰው ኡዱሒያ ለማረድ ብሎ እዳ እንዲገባ / እንዲበደር አይገደድም።

ለኡሑዲያ የሚታረደው እንስሳ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለበት

1. የሚታረደው እንስሳ ከበግ፣ ፍየል፣ ከብት እና ግመል ውስጥ ብቻ መሆን አለበት።
2. ከብትና ግመልን በጋራ ማረድ የፈለገ አንዱ ቢበዛ ለ7 ሰው ነው መሆን ያለበት፡፡ ከዚያ መብለጥ የለበትም። አንዱ ለ 7 ሰው ከተቻለ ቁጥራቸው ከ 7 ያነሰ ሆነው ቢያርዱ የበለጠ ያብቃቃል። ፍየልና በግ ለጋራ ማረድ አይቻልም፡፡
3. የሚታረደው እንስሳ እድሜው የደረሰ መሆን አለበት፡፡ በግ 6 ወር፣ ፍየል 1 አመት፣ ከብት 2 አመት፣ ግመል ከሆነ 5 አመት የሞላው መሆን አለበት፡፡
4. የሚታረደው እንስሳ መታወሩ ግልፅ የሆነ፤ ህመሙ ግልፅ የሆነ በሽተኛ፤ ግልፅ የሆነ አንካሳ፤ በጣም ያረጀ፣ አብዛሃኛው ወይም ግማሽና ከዚያ በላይ የሆነ ጆሮው፣ ጅራቱ፣ ላቱ፣ ቀንዱ፣ የተቆረጠ ወይም የተሰበረ መሆን የለበትም፡፡ ትንንሽ እንከኖች ችግር አይሆኑም። የተኮላሸ መጠቀም ይቻላል። ነብዩ ﷺ ሁለት የተኮላሹ በጎችን አርደዋል። [ሱነኑል በይሃቂይ]
5. የሚታረደው የግድ በተገደበው ጊዜ መሆን አለበት፡፡ እሱም ከዒድ ሶላት በኋላ እስከ ዙልሒጃ 13 ባለው ነው፡፡ ነብዩ ﷺ (ዒድ) ከመሰገዱ በፊት ያረደ በሷ ቦታ (እርዱን) ይድገም፡፡ ያላረደ ይረድ” ብለዋል፡፡ [ቡኻሪ]
6. ያለ ምንም ልዩነት ከሁለቱም ፆታ ከወንድም #ከሴትም ለኡዱሒያ ማረድ ይፈቀዳል፡፡ [ኢብኑ ባዝ፣ ፈታዋ ኑሩን ዐለ ደርብ፡ ካሴት ቁ. 72]
7. ቆዳውንም ይሁን የትኛውንም ክፍሉን መሸጥ አይፈቀድም፡፡ ለአራጁ የሚከፈለውም ከኡዱሒያው ቆዳ ወይም ሌላ ክፍሉ መሆን የለበትም፡፡ ነብዩ ﷺ “የኡዱሒያውን ቆዳ የሸጠ ኡዱሒያ የለውም!” ብለዋል፡፡ [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 2/1055] ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “ከኡዱሒያው ስጋ፣ ሞራ፣ ቆዳ፣ ወይም ሌላ ነገር መሸረጥ ክልክል ነው፡፡ ምክንያቱም ለአላህ ያወጣው ገንዘብ ስለሆነ ልክ እንደ ሶደቃ መመለስ አይቻልም፡፡ [ፈታዋ ኢብኒ ዑሠይሚን፡ 25/162] ባይሆን ስጦታ የተሰጠው ሰው ቢሸጥ ምንም ችግር የለበትም፡፡
8. ስጋው ምን ይደረጋል? በእለቱ ከቤት ይበላል። ለዘመድ፣ ለጓደኛ፣ ለምስኪን ይሰድቃል ወይም ስጦታ ይሰጣል። ቀሪ ከኖረ ያስቀምጣል፡፡ ስጦታ የተሰጠው ሰው ግን መሸጥን ጨምሮ ሐላል በሆነ መልኩ ለፈለገው አገልግሎት ማዋል ይችላል፡፡
9. ኡዱሒያውን እራሱ ባለቤቱ ቢያርድ በላጭ ነው፡፡ ካልቻለ ወይም ካልተመቸው ግን ሰው መወከል ይችላል፡፡
ከተለያዩ ፈትዋዎች የተሰበሰበ ነው፡፡
=
ሸይኽ ሷሊሕ አል ሉሃይዳን አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል፡-

«በወላጆች ላይ ፅድቅን ማድረግ አላህን በኢኽላስ ከማምለክ  ጋር የተያያዘ ሲሆን ወላጅን አለመታዘዝ በአላህ ላይ ከማሻረክ ጋር የተያያዘ ነው። ለዚህም ነው ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ለባልደረቦቻቸው ‹‹ ከከባባድ ወንጀሎች ይበልጥ ከባዱን አልነግራችሁምን?» አሉ። ሰሃቦችም፦ «አዎን ይንገሩን» አሏቸው።
እሳቸውም፦ “በአላህ ላይ ሽርክን መፈፀም ነው፣  ከዛም  ወላጆችን አለመታዘዝ ነው።» በማለት መለሱ። ምስጋናን በተመለከተ አላህ በቁርኣኑ ፦ « እኔን እና ወላጆችህን አመስግን።» ይላል።

@Khalid_islamawi_studio
@Khalid_islamawi_studio
@Khalid_islamawi_studio
@Khalid_islamawi_studio


ሸይኽ ሷሊሕ አል ሉሃይዳን አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል፡-

«በወላጆች ላይ ፅድቅን ማድረግ አላህን በኢኽላስ ከማምለክ  ጋር የተያያዘ ሲሆን ወላጅን አለመታዘዝ በአላህ ላይ ከማሻረክ ጋር የተያያዘ ነው። ለዚህም ነው ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ለባልደረቦቻቸው ‹‹ ከከባባድ ወንጀሎች ይበልጥ ከባዱን አልነግራችሁምን?» አሉ። ሰሃቦችም፦ «አዎን ይንገሩን» አሏቸው።
እሳቸውም፦ “በአላህ ላይ ሽርክን መፈፀም ነው፣  ከዛም  ወላጆችን አለመታዘዝ ነው።» በማለት መለሱ። ምስጋናን በተመለከተ አላህ በቁርኣኑ ፦ « እኔን እና ወላጆችህን አመስግን።» ይላል።

@Khalid_islamawi_studio
@Khalid_islamawi_studio
@Khalid_islamawi_studio
@Khalid_islamawi_studio


ቡራዩ ሰላም መስጅድ ከፈረሰም በኋላ የአካባቢው ሙስሊም ነዋሪዎች በቦታው ላይ መስገድ አላቆሙም ነበር ።
ሁሉንም ወቅት ሰላቶች ተሰብስበው በጀመአ በፈረሰው መስጅድ ሜዳ ላይ ሲሰግዱ ቆይተዋል ።ይሁን እና ትላት ቅዳሜ መግሪብ ለመስገድ ጀምአው ሲሰበሰብ ግን የአካባቢው ታጣቂዎች እና ፖሊስ በሁለት ፓትሮል መጥተው ሰላቱን ከልክለዋል። 

ከዚህ በኋላ በዚህ ቦታ ላይ የሚሰግዱ ከሆነ እንደሚያስሯቸው ዝተውባቸዋል።

የሸገር ሲቲ ከንቲባ ስለመስጅዱ ፈረሳ አላውቅም ብለዋል የሸገር ሲቲ ፀጥታም መረጃው የለኝም እያለ ነው ይሁን እና ዛሬስ በፓትሮል መጥቶ ሰላቱን ያስቆመው ማን ነው?
ለዚህ አካል የፖሊስ ልብስ እና መኪና ማን ሰጠው?
ይህ አካል የራሱ እስር ቤት አለው ወይ?
ሸገር ሲቲ ስንት መንግስት ነው ያለው?

ስለመስጅድ ፈረሳ የተነሳውን ጥያቄ አለመመለስ ብሎም ስለቀጣይ የሚፈርሱ መስጅዶች ፕሮግራም ማውጣት ህዝበ ሙስሊሙን መናቅ ነው።

አዲሲቷን ከተማ ሙስሊም አልባ ለማድረግ የሚሰራው ሴራ በአላህ ፈቃድ አይሳካም።

https://t.me/khalid_islamawi_studio

20 last posts shown.