አብሬሽ ሞቼ ባይሆን.....
ለምን የሚወዱሽ ሲያለቅሱ ደረታቸውን ሲደቁ
ፀጉራቸውን ሲነጩ ዝም ብዬ ፈዝዤ ተመለከትኳቸው...?
አቅፈውኝ አዝነውልኝ እያለቀሱ ሲያባብሉኝ ለምን ደነዘዝኩ...?
አብሬሽ ሞቼ ባይሆን....?
ድንኳን ውስጥ ወዳጅ አዝማድ ተሰብስቦ ሲጨዋወት ሲያፅናና እኔ ለምን ብቻዬን ዲዳ ሆንኩኝ....?
አብሬሽ ሞቼ ባይሆን...?
ሚቀርበኝ ጉድህ ፈላ እያለ ሲመለከተኝ በርታ እያለ ማፅናኛ የቃላት ጋጋታ ሲያንጋጋ እንዴት በዚህ ሁሉ መሀል የእንባ ቋቴ አልተረታም...🥺
ከእሩቅ ከቅርብ ቀዬ ሃዘኔን በአካል ሊያጋሩኝ መጥተው አይኔን እያዩ ሲያጫውቱኝ ሊያበረቱኝ ሲታገሉ እንዴት ሆድ አይብሰኝም...?
አብሬሽ ሞቼ ባይሆን....?
ቆሌ ቅስሜ ደመነፍሴ ትውስታዬ መጓጓቴ ህልሜ አብሮ ከአንቺ ጋር ባይቀበር እንዲሁ መች እሆን ነበር....?
ከዚህ በኋላ አለመኖርሽ እንዴት አያባባኝም...?
አንቺ ሞተሽ እኔ አብሬሽ ሞቼ ባይሆን አንድ ዘለላ እንባ እንዴት አይወጣኝም ...?
ይሁን ሁሉም....አብሬሽ ሞቼ ባይሆን ለምን ምሳዬ አይርበኝም...? እንደ ሁሌም ለምን ውሀ ጥሜ አይታወቀኝም...? ቆይ እሺ ለምን አትናፍቂኝም....?
ዮሀንስ...🤌🤍 @Jo_21_19
🥀ᴊᴏɪɴ & ꜱʜᴀʀᴇ🥀
🔔@Kurach_kalat💭
📣@Kurach_kalat💬