የማይሻር ቁስል
ክፍል ሶስት
“ ስለፅሁፍ ስናወራ ትዝ አለኝ!” አለ አብርሀም የሚጨንቀውን ዝምታ እየሰበረ። ከተቀመጠበት ሶፋ በጥግ የወሸቃቸውን የወረቀት ጥቅሎችን አወጣ እና አቧራውን መታ መታ አድርጎ አራገፈው። “ የንፅህና ችግር እንጂ ሳላነባቸው ቀርቼ እንዳይመስልሽ!” አላት ፈገግ እያለ።
“ የኔ መፅሀፍ እንዳይሆን?! ”
“ አዎና! በፌስቡክ ላይ ማውራት ከጀመርንበት ጊዜ አንስቶ የላክሽልኝን ፅሁፎት በጠቅላላ በወረቀት እያሳተምኩ አንብቤያቸዋለሁ። በስልክ ሳነብ ደስ አይለኝም! የድሮ ሰው በይኝ!”
“ ምን ማለት እንዳለብኝ አላውቅም!”
“ ምንም አትበይ ፤ እንደውም የምለው ማጣት ካለብኝ እኔው ነኝ። እንደዚህ አይነት ድርሰት ከማንም ቀድሜ ማንበብ መቻሌ በጣም ደስ ይላል። የቃላት አጠቃቀምሽ እጅግ ማራኪ ነው። በተለይ በተከታታይ እየላክሽልኝ የነበረው ረጅም ልብወለድ! እያንዳንዱን ገፀባህሪ ስትገልጪ ከማስተዋወቅም በላይ በብዕርሽ አዲስ ሰው እየፈጠርሽ እንደሆነ ይታያል። በደስታቸው የምትደሰቺላቸው በሀዘናቸው የምታዝኚላቸው ስሜታቸው የሚጋቡ ገፀባህሪያት ናቸው። ከሁሉም በላይ ደግሞ ዋናዋ ገፀባህሪ በታሪኳ የምታዝኚላት እንዲሳካላት የምትፈልጊላት አይነት ማንነት አላት። አንድ ያስተዋልኩት ነገር ደግሞ ፤ ስለራስሽ ከነገርሽን በመነሳት ከአንቺ ጋር በጣም ትመሳሰላላችሁ! አንቺም የመወደድ ለዛ አለሽ!” አላት ፤ ማክሪና ፊቷን በእጇ ደገፍ አድርጋ ከምታዳምጥባት ፈገግ አለች።
አብርሀም ንግግሩን ቀጠለ ፤ “ ታሪኩ የሚፈፀሙበት ቦታዎች ፤ የገፀባህሪያቶቹ ስሜት እና ድርጊት ፤ ሲልም የድርጊቶቹ እና የክስተቶቹ አገላለፅ ገፀባህሪያቱን በአካል እየተከታተልሽ የፃፍሻቸው እንጂ በህሊና የፈጠርሻቸው አይመስሉም። ”
“ እኔንጃ! ተሳስቼ የሌላ ደራሲ መፅሀፍ ልኬልህ እንዳይሆን!” አለች ማክሪና ግንባሯ ላይ የደፋችውን ፀጉር እያስተካከለች።
“ የምልሽ ነገር ሁሉ ከልቤ የተሰማኝን ነው። እዚሁ ቁጭ ብዬ በመፅሀፍሽ ሀገሪቷን ሳካልል ነው የከረምኩት። ግን ስለስህተት ካወራሽ አይቀር አንድ ስህተት አግኝቼብሻለሁ። ”
“ አንድ ብቻ?”
“ አዎ! ልቤን በታሪክሽ ሰርቀሽ አንጠልጥለሽው ስታበቂ የመጨረሻ ምዕራፍ ብለሽ የላክሽልኝ ክፍል የመጨረሻ ገፆቹን ቆርጠሽ አስቀርጠሻቸዋል!” አላት የመጨረሻውን ገፅ በእጆቹ እያውለበለበው።
“አይደረግም! የእውነትህን ነው?”
“አዎን! ምን ላይ እንዳቆመ ላንብብልሽ!”
“ አምራን የደረሳትን መልዕክት እንዳነበበችው ካለችበት ተነስታ በደስታ ጮኸች። እድሜ ልኳን ከቤተሰቧ ጋር ያሳለፈችው ስቃይ በስተመጨረሻ ሊካስ እንደሆነም ስታስብ የደስታ እንባ ዘለላዎች ፊቷን አጠቡት። ቀን ከለሊት ስትፀልይ ፤ በጨለመ መንገድ ነገዋን እያሰበች በጉልበቷ ስትንፏቀቅ ቆይታ ዛሬ ገና በእግሯ ቆማ ልትሄድ እንደሆነ ታሰባት። ለደቂቃዎች በተቀመጠችበት የደስታ እንባ ስታለቅስ ከቆየች በኋላ ረገብ ሲልላት ነበር ቤተ መፅሀፍት እንደነበረች ያስታወሰችው። ሰው ሁሉ ስሜቷን አይቶ መናገር አልፈለገም እንጂ ትኩረቱ ሁሉ ወደ እሷ እንደነበር ዙሪያዋን አይታ አወቀችው። እንባዋን ጠረግ አድርጋ በድጋሜ ከላይ እስከታች የገባላትን መልዕክት አነበበች። ውድ አምራን ለስታንፎርድ ዩንቨርስቲ ያስገባሽው የነፃ ትምህርት እድል ተቀባይነት ስላገኘ በተጠቀሰው ቀን ትምህርትሽን መጀመር ትችያለሽ! ብሎ የሚጀምረውን ፅሁፍ ደጋግማ ካነበበችው በኋላ ከተቀመጠችበት በጥድፊያ እቃዎቹን ቦርሳዋ ውስጥ ከታ እየተጣደፈች ከቤተመፅሀፍት ወጣች።"
" ሰዓቱ ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ቢሆንም ምሽቱን እዛው ዩንቨርስቲ አድራ በነጋታው ወደቤት ለመሄድ የሚሆን ትዕግስት አልነበራትም። ይህን የመሰለ ዜና በስልክ ለእናት እና አባቷ መናገርም አልፈለገችም። ውስጧ እየተንቀለቀለ ያለውን የደስታ ስሜት ከእናት እና አባቷ ጋር ተቃቅፋ ማሳለፍን ፤ ምሽቱን ያሳለፉትን ነገሮች ሁሉ እያስታወሱ ለበጎ መሆኑን እየሳሉ የወደፊት ነገዋን በደስታ ማሰብን ፈልጋለች። በታመመችበት እና የሞት አፋፍ ደርሳ በመጣችበት ጊዜያት ሁሉ ሲያነባ የነበረው የእናቷን አይን እያየች ህይወት በእሷ ሲክሳት ማየትን ፈልጋለች። ከሀኪም ቤት ሀኪም ቤት በእግሮቹ እየኳተነ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ወጣትነቱን የገበረላትን የአባቷን ሰውነት እቅፍ አድርጋ ልታሳርፈው ፈልጋለች። የምትኖርበት ሰፈር በእግር ሲኬድ አድካሚ መሆኑ አላሳሰባትም። በሳቅ የታጀበው እንባዋን ንፋሱ እየተሻማት በሩጫ ወደቤቷ አመራች። ” ብለሽ አቆምሽው። አላት አብርሀም አንገቱን አቀርቅሮ ሲያነብ ከነበረበት።
ዮሀንስ...🤌🤍 @Jo_21_19
🥀ᴊᴏɪɴ & ꜱʜᴀʀᴇ🥀
🔔@Kurach_Kalat💭
📣@Kurach_Kalat💬