የማይሻር ቁስል
ክፍል ስድስት
“ በሞትኩት!” አለች በመሀል ገና ጀመር ያደረገችውን ሻይ እያስቀመጠችው።
“ ምን ነው?”
“ የመፅሀፌን የወረቀት ህትመት ቦርሳዬ ውስጥ ሳልይዘው አልቀርም። የመጨረሻ ገፆቹን ከዛ ላይ አንስተህ ማንበብ ትችላለህ።” ብላ አጠገቧን ዞር ዞር ብላ ስትመለከት ቦርሳዋን አጣችው። ሳሎን ሶፋ ላይ እንዳስቀመጠችው ትዝ ሲላት ልታመጣ ስትነሳ አብርሀም ቀድሟት ብድግ አለ። “ ሶፋ ላይ አስቀምጠሽዋል አይደል! ቆይ ይዤልሽ ልምጣ።” ብሎ ወደ ሳሎኑ አመራ። ጠረጴዛ ፊት ለፊት የተቀመጠውን ቦርሳዋን ይዞላት ተመለሰ።
“ይኸው!” አለ ቦርሳዋን እያቀበላት። ማክሪና ቦርሳዋን ከከፈተችው በኋላ በአንድ የተጠረዙ ወረቀቶችን አወጣች እና “ እንደያዝኩት አውቄ ነበር።” አለች ።
“ በየሄድሽበት ፅሁፍሽን ይዘሽው ትንቀሳቀሻለሽ?” አላት አብርሀም ያን ሁሉ ወረቀቶች በቦራሳዋ ይዛ መንቀሳቀሷ አስገርሞት። “የእድል ነገር አይታወቅም። ምናልባት ከአንድ አሳታሚ ድርጅት ሰራተኛ ጋር ታክሲ ላይ ብንገናኝ አሊያም ከአንድ እውቅ ፀሀፊ ጋር ካፌ ውስጥ ብንገጣጠም ዝግጁ መሆኑ አይከፋም።” አለች ማክሪና ቦርሳዋን አስቀምጣ ድርሰቷን ለአብርሀም እያቀበለችው። ወደግንባሯ ድፍት ያደረገችው ፀጉር ለመጀመሪያ ጊዜ ንፋስ ወደኋላ ሲገልበው ግንባሯ ላይ ረጅም ስፍ የሚመስል ጠባሳዋን ገለጠው። ቦርሳዋ ውስጥ ያደረገችው ሻሽ ትዝ ያላት ማክሪና ቶሎ ብላ አወጣችና አደረገችው።
“ ግንባርሽን ምን ሆነሽ ነው?” አላት አብርሀም ድርሰቱን ተቀብሎ በእጁ ከያዘ በኋላ።
“ ከአመታት በፊት የተፈጠረ ነገር ነው። በለሊት አንድ አደጋ አጋጥሞኝ ክፉኛ ተጎድቼ ነበር። ” አለች በሻሿ ላይ ጠባሳዋን በእጆቿ እየዳበሰችው።
“ እንኳን ተረፍሽ መጥፎ ቦታ ነበር።” አለ እና አብርሀም ያቆመበትን ፍለጋ ገፆቹን ያገላብጥ ጀመር።
“ ሻይህ ቀዘቀዘ!” አለች ማክሪና። አብርሀም ከመፅሀፉ ላይ አይኖቹን ሳይነቅል የቀዘቀዝው ሻዩን አነሳና በአንድ ትንፋሽ ጭልጥ አደረገው። ሻይ ቅጠሉ አብዝቶ እንደሆን ያሰበው የጠጣው ሻይ ሲጎመዝዘው ነበር። ፊቱን ጭምድድ ካደረገው በኋላ አንድ ገፅ ገለጠና “ አገኘሁት” አለ በደስታ።
“ ለኔም አብረህ ታነብልኛለህ! ” አለች ማክሪና ካለችበት በተመስጦ እያየችው።
“ ደስ ይለኛል። ” አለ እና አብርሀም ጎሮሮውን ጠረግ ጠረግ ካደረገ በኋላ ቀጥሎ የተፈጠረውን ለማወቅ እየጓጓ ድርሰቱን ማንበቡን ጀመረ።
“... በሳቅ የታጀበው እንባዋን ንፋሱ እየተሻማት በሩጫ ወደቤቷ አመራች። ያደረገችው ጫማ እንደልቧ አላስሮጥ ሲላት አውልቃ በእጆቿ ያዘችውና ዋናውን የመኪና መንገድ ሳይታወቃት ጨረሰችው። ሰፈሯ እንደደረሰች የገባት የቤታቸውን መግቢያ መንገድ ስትመለከተው ነበር። መንገዱ ከዋናው መንገድ በራቀ ቁጥር ጭለማ የዋጠው ድቅድቅ ፅልመት ቢሆንም ያሳለፈችውን ጨለማ የለመዱ አይኖቿ ያለምንም ድካም የምትሄድበትን ያሳዩአት ነበር። የኮሮኮንቹ መንገድ ድንጋይ እዚም እዛም ቢያደናቅፋትም ስንቱን እንቅፋት የተሻገሩ እግሮቿ በዛ መንገድ ላይ እያፍትለከለኩ መውሰድ አልከበዳቸውም። በቀረበች ቁጥር የቀራት መንገድ እየረዘመ ያለ መሰላት። በስተመጨረሻ ቤታቸውን ፊትለፊት የሚያሳይ መታጠፊያ ጋር ልትደርስ ስትል አንድ ድምፅ ከኋላ ሰማች።"
“ ቆንጂት በዚህ ምሽት ወዴት ነው!” አለ አንድ ሰው በጭለማው ውስጥ ሆኖ ፊቱ ባይታይም ድምፁ እንደሰከረ ያስታውቃል። “ መልስ አልሰጠችውም! ድምፁን ለመስማት ቆም ካለች በኋላ ወደቤቷ ለመሄድ ስትሞክር ከኋላዋ አንዳች ነገር ሲያርፍባት በደረቷ መሬት ላይ ተደፋች። ጀርባዋ ላይ እንዳች የሚወጋ ነገር እየተሰማት ግራ በመጋባት ምን እንደተፈጠረ ለማየት ዞራ ስትቀመጥ አጠገቧ የቆመ አንድ ወጣት ተመለከተች። አይኖቹ እና ጥርሶቹ በለሊት አድፍጦ ሟችን እንደሚጠብቅ አውሬ ያበራሉ። "
ዮሀንስ...🤌🤍 @Jo_21_19
🥀ᴊᴏɪɴ & ꜱʜᴀʀᴇ🥀
🔔@Kurach_Kalat💭
📣@Kurach_Kalat💬