💙 ምኞቴ 🔸
#ክፍል_ 9️⃣
✍.... ኤዲ ለቢኒ ካላት ፍቅር የተነሳ ስታከብረዉ ወደር የላትም፡፡ ሁሌም ቢሆን ለሱ ንግግር
ቦታ ትሰጣለች፡፡
በእያንዳንዷ ክንዋኔም ላይ የቢኒ ቃል ተቀዳሚ ነዉ፡፡
... ሁለቱም በእኩል ቅጽበት "እ..." ሲሉ... ኤዲ ቀደም ብላ "ወይዬ ቢኒ ምን ልትለኝ ነበር?"
አለችዉ፡፡
ቢኒም "ኤዲዬ የኔ ቆንጆ አንቺ ሁሌም እኔን ታስቀድሚያለሽ፡፡ "የኔ ፍቅር ታዉቃለሃ?"
..... "ምኑን ነዉ የማዉቀዉ ኤዲዬ?"
..... "እኔና አንተ ከተጋባን አራተኛ አመታችን ነዉ፡፡"
..... " እ... በፍቅር ክንፍ አድርገሽኝ ያበድኩልሽ ቀን! ያ ቀን እንዴት ይጠፋኛል ዉዴ!?"
..... "እሱ አይደለም ፍቅሬ"
..... "እና ምንድን ነዉ ....?"
..... "ከተጋባን ቆይተናል ግን እስካሁን...."
... "ማሬ አታስጨንቂኛ ፕሊስ ንገሪኝ?"
..... "ቢኒ የኔ ዉድ...."
.... "ወይዬ ኤዲ የኔ ቆንጆ! ... ንገሪኛ!"
..... "ልጅ ልወልድልህ አልቻልኩም ቢኒ"
ቢኒ በዉስጡ ያለዉን ስሜት ኤዲ አወጣችዉ፡፡ "ሁለታችንም አንድ አይነት ነገር ነበር
የምናስበዉ ማለት ነዉ?" አለ በሆዱ፡፡ ትክክለኛ ባልና ሚስት ከአንድ ምንጭ ነዉ የሚቀዱት
ማለት ይሄኔ ነዉ፡፡
ቢኒ ኤዲን ሊጎዳት አልፈለገም....
..... "ኤዲዬ ይሄኮ ታዲያ የፈጣሪ ዉሳኔ ነዉ፡፡ ፈጣሪ ባለ ጊዜ ትወልጂ ይሆናል፡፡" አላት፡፡
..... " አዎ የኔ ፍቅር ፈጣሪ ካለ እወልድ ይሆናል፡፡ ግን ደግሞ አንተ ከኔ በይበልጥ ልጅ
ማግኘት፤ ዘርህን መተካት ይኖርብሃልኮ ዉዴ!"
..... "እና ምን ላርግ ዉዴ? ልጅ ከመዉለድ በላይ አንቺ ለኔ እንደምታስፈልጊኝ ታዉቂያለሽ፡፡
ስለዚህ ማሬ...."
፡
፡
፡
ረዲኤት ስለ ቢኒ ስታብሰለስል ቆይታ ሲጨንቃት ጋደም ባለችበት እንቅልፍ ሸለብ አድርጓታል፡፡
እማማ በለጡም የረዲ የሰሞኑን ቅብዥር አላምራቸዉ ቢል ወደ ረዲ የመኝታ ክፍል ገብተዉ
ከጎኗ ቁጭ ከማለታቸዉ ነበር ... ረዲ እንደ ቅብዥር ነገር ጀምሯት "ቢኒ እወድሃለሁ"
የምትለዉ፡፡
እማማ በለጡ በቆሙበት ደርቀዉ ቀሩ፡፡እስከዛሬ ልጃቸውን ምን እዲህ እንፈሚያደርጋት ገባቸው ቢኒ የኤዲ ባል...እንዴት?... እያሉ ብቻቸውን ያወሩ ጀመር፡፡ ምን ይበሉ? ሊቀሰቅሷት አቃታቸዉና
እንደገና መለስ አሉ፡፡ "በአካል ባታገኘዉ እንኳ በህልሟ እስኪ የሷ ይሁን!" እያሉ ይመስላሉ፡፡
እማማ በለጡ በጣም ጥሩ ሴት ናቸዉ፡፡ ልጃቸዉ አንድ ከመሆኗ የተነሳ እንደ እናት ብቻ
ሳይሆን እንደ እህትም፣ እንደ ጓደኛም ሆነዉ ነዉ ያሳደጓት፡፡ ረዲን ዛሬ ጫን ያለዉ ይዟት
እንጂ አንድም ነገር ከእናቷ ደብቃ አታዉቅም፡፡ አሁን ግን ... የሰዉ ባል አፈቀርኩ ብትል
እንኳን ለእናት ለጓደኛም ለመንገር ያሸማቅቃል፡፡
እማማ በለጡ ጉዳቸዉን ሰምተዉ በእጃቸዉ መዳፋ አገጫቸዉን ይዘዉ "ጉድ... ጉድ" እያሉ
ከረዲኤት ክፍል ወጡ፡፡
እማማ በለጡ ከመዉጣታቸዉ ረዲኤት ብርግግ ብላ ስትነሳ ፊቷ በላብ ተዉጧል፡፡ በቅብዥሯ
"እወድሃለሁ" ስትለዉ የነበረዉ ቢኒያም ከአጠገቧ የለም፡፡ የሞባይሏን ሰአት ስታይ ቢኒ
ለስራ የሚወጣበት ሰዓት ደርሷል፡፡ በፍጥነት ተነሳችና ወደ መታጠቢያ ክፍል ሂዳ እጇ ላይ
ዉሀ በማድረግ ፊቷት ውሃ ረጨት ረጨት አደረገች፡፡ በሷ ሃሳብ መታጠቧ ነበር፡፡ እየሮጠች
ወጣችና በሯ ላይ ቁጭ ብላ እየተቁለጨለጨች የነ ቢኒን ቤት በር በር ታይ ጀመር፡፡
.
....ቢኒ፡ ኤዲ መረበሿን ሲያይ አብሯት እንኳ ባይዉል ቁርስ አብሯት ለመብላት ወስኖ ነበር
ማርፈዱ፡፡ ኤዲ ግን... አዳሯን ሙሉ እንቅልፍ በአይኗ ሳይዞር ስላደረች ንጋቱ ላይ ለብዙ ቀን
እንቅልፍ ያልተኛች በሚመስል መልኩ ለሽሽሽ ብላለች፡፡ ቢኒም ቶሎ እንደማትነሳ
ስለተረዳ ቁርሷን ከአጠገቧ አስቀምጦ በብጣሽ ወረቀት "የኔ ቆንጆ አፈቅርሻለሁ!፡፡ ፈጣሪ
ይጠብቅሽ" የሚል ፅሁፍ አኑሮ ከመዉጣቱ... በሩ ፊት ለፊት ረዲኤትን አያት፡፡
ከግቢ የመዉጫዉን በር ተወና ወደ ረዲኤት ጠጋ ብሎ "ደህና አደርሽ " ሲላት ረዲኤት
አላየችዉም ነበርና ከየት የመጣ የቢኒ ድምፅ ነዉ ብላ ዘወር ስትል በህልሟም በእዉኗም
የምታስበዉ ቢኒ አጠገቧ ቁሞላታል፡፡
እንደመሽኮርመም እያደረጋት "ደህና አደርክ ቢኒ እንዴት አደርክ አለችዉ፡፡
ቢኒም "ትናንት ደዉዬልሽ ባትሪ ዘጋብሽ መሰለኝ..." ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ....
"ቢኒ ምን እንደምልህ አላዉቅም..... " እያለች ስታወራዉ፡፡
እማማ በለጡ የቤቱን መስኮት ገርበብ አድርገዉ ንግግራቸዉን እያዳመጡ ነበር፡፡
#ክፍል 10 ይቀጥላል... LIKE ❤️ & Share✅ በማድረግ ታሪኮቹን በፍጥነት ያግኙ።
ዮሀንስ...🤌🤍 @Jo_21_19
🥀ᴊᴏɪɴ & ꜱʜᴀʀᴇ🥀
🔔@Kurach_kalat💭
📣@Kurach_kalat💬