ሻማ ለኩሼ ከተዘረጋው የመስመር ፣ ወረቀት ላይ ብእሬን እየኳልኩ ነው። የይቅርታ ደብዳቤ ይድረስ እያቀረብኩ ላራኩሽ ፣ እየወደድኩ እጥፉን ለጠላውሽ ፣ እያቀፍኩ ጀርባሽን ለወጋውሽ ፣ የቆምኩልሽ እየመሰልኩ በበዳይሽ ጎን ለተገኘውት ፣ ያለውልሽ መስዬ ለከዳውሽ ፣ ላንቺ....። ደብዳቤዬን ስታዪ ለይቅርታ መዘግየቴ እያብሰለሰለሽ በቅያሜ ሆነሽ እንዳታነቢው ቀድመሽ የርህራሄ ልብሽን ትሰጪኝ ዘንድ እማፀንሻለሁ...። ይቅርታ ዘመንሽን ሙሉ በቆሰለ ልምድሽ ላይ ቁስል ስጨምርብሽ ስለኖርኩ ፣ ይቅርታ ስላላዳንኩሽ ፣ ከሁሉ በላይ ይቅርታ ቦታ ስላልሰጠሁሽ ፣ ችላ ስላልኩሽ ፣ የራስሽን ስሜት አንድም ቀን እንድታደምጪ ስላልፈቀድኩልሽ ፣ ይቅርታ ለወጪ ወራጁ መረጋገጫ ስላደረኩሽ ፣ ይቅርታ የየሰዉን ንዴት ማብረጃ መቀለጃ ስላደረኩሽ ፣ ይቅርታ ስላልተማመንኩብሽ ፣ ብቁ እንዳልሆንሽ ስለነገርኩሽ ፣ ስትንገዳገጂ ስላልደገፍኩሽ አለው ስላላልኩሽ ፣ ይቅርታ ለበደለሽ ሁሉ ይቅርታ ጠያቂ ስላደረኩሽ ፣ ድምፅ ስላልሆንኩሽ ሰዎችን ሁሉ አባባይ ተለማማጭ ስላደረኩሽ ይቅርታ ፣ ስሜትሽን እንድትደብቂ ስለተጫንኩሽ ፣ የተሻለ ነገር ሁሉ አይገባሽም ስላልኩሽ ፣ እንደማይገባሽም ከልብ ስላሳመንኩሽ ይቅርታ ፣ ንፁህ ቅርርብ እንደሌለ ስላስተማርኩሽ ፣ ሌሎች እንደፈለጉት እንድትሆኚ ፣ ስላደረኩሽ እራስሽን ፣ ስላስካድኩሽ ፣ ይቅርታ ህመምሽን ስላላስታመምኩሽ ፣ ቁስልሽን ሰላላከምኩሽ ይቅርታ.....አንዱም አይገባሽም ነበር....🫴💔
ዮሀንስ...✍🤍 @Jo_21_19
🥀ᴊᴏɪɴ & ꜱʜᴀʀᴇ🥀
🔔@Kurach_kalat💭
📣@Kurach_kalat💬
ዮሀንስ...✍🤍 @Jo_21_19
🥀ᴊᴏɪɴ & ꜱʜᴀʀᴇ🥀
🔔@Kurach_kalat💭
📣@Kurach_kalat💬