ታዋቂው የፊልም ባለሙያ ቸርነት ፍቃዱ የ2.2ሚሊዮን ብር ክስ ቀረበበት!
ክስ የቀረበበትም 2.5 ሚሊዮን ብር ኪሳራ አድርሷል በሚል እንደሆነ በቀረበበት ክስ ዝርዝር ላይ ለመመልከት ተችሏል።
ከሳሽ አቶ ዩሀና ተወልደ የተባሉ በሆላንድ አመስተርዳም የሚኖሩ ሲሆነ ከወ/ሮ ሰመሀል ዩሀንስ ጋር በመሆን "ቀንጃ" በሚል መጠሪያ ፊልምን ተከሳሽ ቸርነት ፍቃዱ የፊልሙን ፅሑፍ ድርሰት ዝግጅትና በፊልሙ ላይ አንድ ገፀ ባህሪ ለመስራት መስከረም 26/2016 ዓ/ም ውል እንደተዋዋሉ ከሳሽ አቶ ዩሀና በክስ ዝርዝራቸው ገልፀዋል።
ተከሳሽ ከላይ ለተዘረዘረው የስራ ድርሻ ቅድመ ክፍያ 1 ሚሊዮን እንደተከፈለውና ከሆላንድ ለፊልም ቀረፃ የሚያግዘውን ካሜራ እንዳስመጡለት ይሁን እንጂ አርቲስቱ ፊልሙን በተባለው ጊዜና ሰዓት ባለማስረከቡ ወደ ክስ መግባታቸው አቶ ዩሃና በክስ ዝርዝራቸው ገልፀዋል።
ከሳሽ ለፍርድ ቤት ዳኝነት በጠየቁትም ተከሳሽ የተከፈለውን 1 ሚሊዮን ብር በተጨማሪም በውላቸው መሰረት ለውል ተዋዋዮቹ ሊከፈል የሚገባውን ኪሳራ የከሳሽን ድርሻ 1.2 ሚሊዮን ብር ውሉ ተፈፃሚ ከሚገባበት ጀምሮ የሚታሰብ ህጋዊ ወለድ ጋር እንዲከፍሉ እጠይቃለሁ ሲሉ ገልፀዋል።
ጉዳዩ የቀረበለት የፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ኮልፌ ምድብ 3ተኛ ልዩ ልዩ ፍትህ ብሔር ችሎት በተከሳሽ እና ከሳሽ ጉዳያቸውን በስምምነት እንዲጨርሱ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም ባለጉዳዮች በተሰጣቸው ቀጠሮ መስማማት ባለመቻላቸው ፍርድ ቤቱ ታህሳስ 3 ቀን 2017ዓ/ም ክሱን ለመስማት ተጨማሪ ቀጠሮ ሰጥቷል።
@MOVIE_NEWS12