የክለባችን የወደፊት እጣፋንታ የሚወሰንባት ወሳኟ እለተ ሰንበት!
ከወራት በፊት እንደተገለፀው የክለባችን ደጋፊዎች በግሌዘር ቤተሰቦች ተቃውሞ ዙሪያ በነገው ዕለት ከፍተኛ ንቅናቄ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
በነገው እለት ጨዋታው ከመደረጉ በፊት በኦልድትራፎርድ አካባቢና በተለያዩ አውራ-ጎዳናዎች ላይ በተጨማሪም...
ጨዋታው ከተጀመረ በኋላም ስታድየም ውስጥ ጥቁር ከመልበስ ጀምሮ የተለያዩ የተቃውሞ ባነሮችን በመያዝ ከፍተኛ የተቃውሞ ድምፅ የሚያሰሙ ይሆናል።
የክለባችን Ultra ደጋፊዎችም ከቢዝነስ ውጪ ሌላ ሀሳብ ለሌላቸው የክለባችን አመራሮች ከተቃውሞና አመፅ ውጪ ሌላ ምንም መፍትሔ እንደሌለው በማመን...
ኦልትራፎርድንና መላዋን ማንችስተር ድብልቅልቁን አውጥተው ክለቡን የሚታደጉበትን አንድ እርምጃ ወደፊት እንደሚያስኬዱ ተስፋ እናደርጋለን።
የትኬት ዋጋ መጨመርን ብቻ አስመልክቶ የሚደረግ የወረት ተቃውሞ የሚሆን ከሆነ ዘላቂ ለውጥ ይኖራል ብዬ ባላምንም
የግሌዘር ቤተሰብ ወጥቶ ሌላ ለክለቡ የሚያስብ ትክክለኛ አመራር እስካልመጣ ድረስ ካለበት ቀውስ ለመውጣት ከባድ ለሚሆንበት ክለባችን ግን የነገው የተቃውሞ ሰልፍ ክለቡን ለመታደግ ወደፊት የሚደረግ አንድ እርምጃ ሊሆን ይችላል።
@Man_United_Ethio_Fans@Man_United_Ethio_Fans