MIND MAP
አንድ ከ20+ ገጽ በላይ የሆነ ትልቅ Chapter ማንበብ ሲኖርብህ… ጫላን ነህ ወይስ ደበበን?
🔸 የጫላ መንገድ (Just Read)
ጫላ ከገጽ 1 ይጀምራል ➜ በደመነፍስ እያነበበ ይሄዳል ➜ ያነባል ➜ በመጨረሻም ገጹን ጨርሶ ደብተሩን ይዘጋል።
አንብቦ እንደጨረሰ ያነበበውን ለማስታወስ (Recall) ሲሞክር፦
መጀመሪያ አካባቢ ያነበበውን Main Topic ያስታውሳል፤ ወደ ውስጥ ገባ ሲል ግን የት እንደደረሰ አያቅም “ቆይ… ምን ነበር ያነበብኩት?” 😅 ፣ ምን እያነበበ እንደሆነ እና ጉዳዩ ከምን ጋር እንደሚገናኝ ራሱ ግራ ይገባዋል!
“የመጀመሪያውን ርዕስ አስታውሳለሁ… ከዛ በኋላ ግን የት እንደገባሁ፣ ምን እንዳነበብኩ ራሱ ጠፋብኝ!” ይላል ተበዳይ ጫላ😂
🔹 የደበበ መንገድ (Build Mind Map)
ደበበ አይቸኩልም። ወደ ዝርዝሩ ከመግባቱ በፊት የት እንደሚሄድ ካርታውን በዚህ way ያዘጋጃል፦
Quick Skim ➜ Chapterሩን በግርድፉ ገለጥ ገለጥ አድርጎ ያየዋል።
Find the Big Picture ➜ ዋናውን Main Topic ይለያል።
Spot Subtitles ➜ ቁልፍ Titles እና Subtitles ይመርጣል።
Connect the Dots ➜ ሃሳቦቹ እርስ በእርስ እንዴት እንደሚገናኙ የተለያዩ Diagram በመጠቀም ደብተሩ ጋ ያስቀምጣል።
ስዕሉ ፍጹም እና ውብ መሆን አይጠበቅበትም, ቀስቶች፣ ሳጥኖች ወይም ጥቂት Keywords ብቻ ለደበበ በቂ ናቸው።
ዋናው መርሁ፦
Build the map before exploring the territory.
(ወደ ጫካው ከመግባትህ በፊት መጀመሪያ ካርታህን ያዝ።)
ደበበ ካርታውን አንዴ ከያዘ በኋላ ማንበብ እና ማስታወስ ሲጀምር የት እንዳለ እና ከየት ወዴት እየሄደ እንደሆነ መቼም አይጠፋውም።
የሚፈልገውን ቁልፍ መረጃ ልክ እንደ ራዳር በቀላሉ ነቅሶ ያወጣል።
ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ብቻ ሙሉ ትኩረቱን ያደርጋል።
✦ ሁለቱም አንብበው እንደጨረሱ መጽሐፉን፣ ደብተሩን እና ስልካቸውን ዘግተው “ምን አጠናሁ?” ብለው ራሳቸውን ሲጠይቁ የሚፈጠረው ይህ ነው
የጫላ Recall (Just Reading):
ጭንቅላቱ ውስጥ ያለው መረጃ ልክ እንደተበታተነ ዕቃ ነው! የመጀመሪያውን ርዕስ ብቻ ያስታውሳል፤ የቀረው ግን ወዴት እንደሄደ፣ ከምን ጋር እንደሚገናኝ አያውቅም—የጠፋ ተጓዥ ሆኖ ይቀራል።
“ርዕሱን አውቀዋለሁ… ከዛ ወዲያ ግን ጭንቅላቴ ባዶ ነው!” 🤯
የደበበ Recall (Mind Map):
ጭንቅላቱ ውስጥ ግልጽ የሆነ GPS አለ! በሳለው ካርታ መሠረት በቀላሉ ይጓዛል፦
“ዋናው Topic እዚህ ይጀምራል ➜ ወደነዚህ 3 ቅርንጫፎች ይከፈላል ➜ እያንዳንዱ ስር እነዚህ ቁልፍ ዝርዝሮች አሉ!”
መንገዱም፣ መዳረሻውም፣ ዝርዝሩም በሙሉ በዓይነ-ሕሊናው ቁልጭ ብሎ ይታየዋል። 😎
✦So Study smarter, not just harder✦
Share
@MatricET