+ ከአሸናፈዎች እንበልጣለን +
ቅዱስ ጳውሎስ ኃጢአታችንን በደሙ ባጠበልን በእርሱ በተሰቀለው በልዑል ክርስቶስ ከአሸናፈዎች እንበልጣለን አለ ። እነርሱ የማይሰሩትን ስራ እኛ እንሰራለን ። ብዙ ታላላቅ ጦር ሜዳ ድል ያደረጉ ጀኔራሎች ( ታላላቅ የጦር ሰዎች ) ልባችንን ማሸነፍ አይችሉም ። ይኸው በቅዱስ ጊዮርጊስ ታውቋል። አንዱን ወጣት የሃይማኖት ገበሬ ቅዱስ ጊዮርጊስን ሰባው ነገስታት ከነሰራዊቶቻቸው ሊያሸንፍት አልቻሉምና ። እርሱ ድል አደረጋቸው እንጂ ፤ በእርሱ ጸሎት ሁሉንም እሳት በላቸው ፣ እርሱ ግን ማንም ድል ሊያደርገው ሊያሸንፈው አልቻለም ። ብዙ መከራ ቢያጸኑበትም ፤ ስጋውን አቃጥለው አመድ አድረገው ቢበትኑበትም ቅሉ ፤ ሃይማኖቱ አስነሳው ። መድኃኔ ዓለም ተገልጦ "ወዳጄ ጊዮርጊስ ሆይ ተነስ " አለው። ቅዱስ ጊዮርጊስ ድል ያደረገው በወደደው በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ነው ። ጠላቶቹ ገደልነው ፣ አሸነፍነው ፣ ቆራረጥነው ፣ በተንነው ፣ ጠብስነው ፣ አቃጠልነው ፣ ሲሉ በወደደው በፈጣሪው በኢየሱስ ኃይል ከሙታን ብድግ ይልና ፤ ከጫጉላ ቤት እንደ ወጣ ሰው ታድሶ ፣ ለምልሞ እንደገና ሄዶ ይገጥማቸዋል ። ሶስት ጊዜ ገደሉት ሶስት ጊዜ ተነሳ ፣ በአራተኛው በእግዚአብሔር ፍቃድ ነብሱ ከስጋው ተለየች ። ነገር ግን መጀመርያ አነርሱን አጥፋቶ ነው ፤ እሳት ከሰማይ ወርዶ ጠላቶቹን አጥፍቶ ሲያበቃ በሰይፍ ተሰየፈ ፤ ከአንገቱም ደም ፣ ውኃ ፣ ወተት ፈሰሰ። (ገድለ ጊዮርጊስ ) ስለዚህ በወደደን በእርሱ በኃያሉ በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ ከአሸናፈዎች እንበልጣለን ።
ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ በዕብራውያን መልእክቱ (በሃይማኖት የሚሰራ ታላላቅ ስራ) እንዳለ ነግሮናል ። እንግዲህ ምን እላለሁ ? ስለ ጌዴዎን ስለ ባርቅ ስለ ሶምሶን ስለ ዮፍታሔም ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም ስለ ነብያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛል ። እነርሱ በእምነት መንግስታትን ድል ነሱ።" ዕብ 11:32:33 (ኦርቶዶክስያ ገጽ -94 የመ/ር ግርማ ከበደ ትምህርታዊ ስብከቶች ስብስብ )
@mekra_abaw