ምዕራፍ 3 የደዕዋ ግልፅ መውጣት
ክፍል 21 ዳሩል አርቀም
የመጀመሪያው እርምጃ የአርቀም ቢን አቡል አርቀም አልመኽዙሚን ቤት(ዳሩል አርቀም)የዳዕዋ፣የኢባዳና የተርቢያ(ሥልጠና) ማዕከል ማድረጋቸው ነበር።ይህ ቦታ የተመረጠበት ምክንያት በአል-ሰፋ ተራራ ስር ስለሚገኝና ከአመፀኞችና ከድንበር አላፊዎች እይታ ራቅ ያለ ስለነበር ነው።ከሰሃቦቻቸው ጋር በምስጢር እዚያ ይሰበሰባሉ።እዚያ የቁርኣን አንቀፆችን ያነቡላቸዋል፤ ከሽርክ ያጠሩዋቸዋል፤ መጽሐፍን(ቁርኣንን) እና ጥበብን ያስተምሩዋቸዋል። በግልፅና በገሃድ ከሰሃቦቻቸው ጋር ቢሰበሰቡ ኖሮ ሊደርሱ ይችሉ ከነበሩ ብዙ ችግሮች በዚህ ዘዴ ሰሃቦቻቸውን ከአደጋዎችና ችግሮች ታግደዋቸዋል።እርሳቸው ግን በሙሽሪኮች መሀል አላህን ይገዛሉ፤ወደ አላህ በግልጽ ይጣራሉም።የሚደርስባቸው በደልም ሆነ ድንበር ማለፍ ማላገጥም ሆነ መሳለቅ ከተግባራቸው ወደ ኋላ ለሰዎች በአላህ ላይ መከራከሪያ ነጥብ እንዳይኖራቸው የተደረገ የአላህ ጥበብ ነው። ይህም ማለት በ"ቂያማ" ቀን አብሳሪም ሆነ አስጠንቃቂ አልመጣልንም እንዳይሉ ነው።
ወደ ሐበሻ ስደት-ሂጅራ
ሁለተኛው እርምጃ ነጃሺ ማንም ሰው በርሱ ዘንድ የማይበደል ፍትሃው ንጉስ መሆኑን ካረጋገጡ በኋላ ሙስሊሞች ወደ ሃበሻ እንዲሰደዱ አመላከቱዋቸው። ከነቢይነት(ኑቡዋ)አምስተኛ አመት ላይ በረጃብ ወር የመጀመሪያው ቡድን ወደ ሀበሻ ተሰደደ።አስራ ሁለት ወንዶችና አራት ሴቶች ነበሩ።ኋላፊያቸው ዑስማን ቢን ዐፋን አል ኡመዊ (ረ.ዐ)ሲሆኑ ከሳቸው ጋር ባለቤታቸው ሩቅያ ቢንት ረሱሊላህ(ﷺ) ነበሩ።ከነቢዩሏህ ኢብራሂምና ከነቢዩላህ ሉጥ (ዐ.ሰ) ቀጥሎ በአላህ መንገድ ከቤተሰብ ጋር ለመሰደድ ዑስማን የመጀመሪያው ሰው ናቸው።
እነዚህ ሰሃቦች በሌሊት ጨለማ በምስጢር ወጥተው ከጂዳ በስተደቡብ ወደሚገኘው ሸዒባ ወደሚባለው ወደብ አመሩ። የአላህ "ቀደር" ሆነና ሁለት የንግድ ጀልባዎችን አግኝተው በመሳፈር ሀበሻ ገቡ። ቁረይሾች ግን መውጣታቸውን ሲሰሙ በጣም ተቆጡ። ይዘዋቸው ወደ መካ በመመለስ መቅጣቱንና ማሰቃየቱን በመቀጠል ከአላህ ሃይማኖት ሊመልሷቸው ፈልገው የወጡትን ሰሃቦች ፈለጎቻቸውን በመከተል በፍጥነት ወደ ባህር አመሩ።ሙስሊሞቹ ግን ተሳፍረው አመለጡ። ቁረይሾች የባህር ጠረፍ ከደረሱ በኋላ አፍረው ተመለሱ።
ይቀጥላል.......
https://t.me/Menhaj_Asselefiya