ትራምኘ እና የስደተኞች ጉዳይ
ፕሬዝዳንት ትረምፕ ከመመረጡ ቀናቶች በፊት፤ ትረምፕ ሊመረጥ እንደሚችል እና የኢምግሬሽን ጉዳዮችን አስመልክቶ በጣም ጥብቅ እርምጃዎችን እንደሚወስድ፤ በዚህም ኢትዮጵያኖች ጭምር ተጠቂ እንደሚሆኑ ገልጬ ነበር።
ፕሬዝዳት ትረምፕ ቶም ሆማንን በኢምግሬሽን እና ቦርደር ጉዳዮች በመሾም የዲፖርቴሽን እቅዱ ሲሪየስ እንደሆነ አሳይቷል። ቶም ሆማን በመጀመሪያዎቹ 90 ቀናት ውስጥ ብቻ ብዙ ሚሊዮን ሰዎችን ዲፖርት ማድረግ እንደሚቻል እና ያንንም ለመፈጸም ሚሊተሪውን ጭምር እንደሚጠቀም ገልጿል። ይሄም ማለት በየሆቴሎቹ የICE ኦፊሰሮች በድንገት እየገቡ መፈተሽ፣ ሕዝብ በተሰበሰበበት ቦታዎች ድንገተኛ ፍተሻ እና ማጣራቶችን በማድረግ፤ የቪዛ ጊዜያቸውን የተላለፉ ሰዎችን ጨምሮ ዶክመንት የሌላቸውን ሰዎች በማሰር ዲፖርት ማድረግ የቶም ሆም ተልዕኮ ይሆናል።
ኢትዮጵያኖች ምን ያድርጉ፤
1) በተለይ የቪዛ ጊዜያችሁን ተላልፋችሁ በአሜሪካ ያላችሁ ሰዎች በፍጥነት ወደ ሕጋዊ ስታተስ ራሳችሁን መቀየር። ለምሳሌ አሳይለም ፋይል ካላደረጋችሁ ፥ ፋይል ማድረግ፤
2) የአሳይለም ሂደታችሁ በፍርድ ቤት እየተከታተላችሁ ያላችሁ ፥ የፍርድ ቤት ቀጠሮአችሁን በአግባቡ መከታተል። ከጠበቆቻችሁ ጋር በቅርበት መስራት፤
3) ያለሥራ ፈቃድ በካሽ የምትሠሩ ሰዎች ይሄ ከፍተኛ አደጋ ሊጥልባችሁ እንደሚችል ማወቅ እና ጥንቃቄ ማድረግ፤
4) በመጨረሻም ሁልጊዜ ዜናዎችን፣ በኢምግሬሽን ጉዳዮች ያሉ መረጃዎችን መከታተል እና ማድረግ የሚገቡንን ጥንቃቄዎች ዘወትር ማድረግ።
ሙሉአለም ጌታቸው
@MeribahTimes