ጥላቻውን አታቆመውም!
እብደትህ እስከቀጠለ ጥላቻው አያቆምም፤ ልዩነት መፍጠር እስካላቆምክ ትቺቱ አያቆምም፤ ማስመሳል እስካልቻልክ ወቀሳው አይቀርም፤ ማጨብጨብ እስካልጀመርክ መነቀፍህ አያቆምም፤ መንጋውን እስካልተቀላቀልክ አጀንዳ መሆንህ አይቆምም፤ ተስፋ እስካልቆረስክ ጣት የሚቀስርብህ አታጣም። እራስህን መሆን ካላቆምክ በአንድ ፅንፍ የሚያንቋሽሽህ፣ የሚያወራብህ፣ የሚተችህ፣ የሚሰድብህ አይጠፋም። መረዳት የማይፈልግን ሰው ፈትፍተህ ብታጎርሰውም ሊቀበልህ አይችልም። ያንተ ሃሳብ ጤና ቢስ ሆኖ ሳይሆን ውስጡ የተፈጠርው ፈር አልባ ጥላቻና የበታችነት ስሜት ስለሚያንጨረጭረው ነው። እውነቱን ሲነጓሯት የኮረኮሯት መሰላት እንደሚለው አባባሉ፤ የሚመለከተው ጉዳይ ሲነሳ ያዙኝ ልቀቁኝ ማለቱ የማይቀር ጉዳይ ነው።
አዎ! ጀግናዬ..! ጥላቻውን አታቆመውም! መገፋቱን አታስቀረውም፤ ትቺቱ ሁሌም ይኖራል። በተመሳሳይ የህይወት አዙሪት የተጠመደ ሰው አልተረዳኝም ብለህ አንገትህን አትድፋ፤ በፍረሃት ሰነሰለት የታሰረ ሰው ጠላኝ ብለህ ሆድ አይባስህ። የምታደርገው ነገር ስሜት ካልሰጠው ዝም ማለት ቢችልም መፍጨርጨሩን ከመረጥ እርሱ ያንተ ጉዳይ ሳይሆን የእራሱ ጉዳይ ነው። እውነት እያደር ይጠራል፤ የሚገባውም በጊዜው ይገባዋል። የመጣህበትን መንገድ የማያውቅ ሁሉ ለመፍረድ መቸኮሉ እጅግ ያስገርማል። ነገር ግን ይህ ይሆን ዘንድ የግድ ነው። ማሰብ እንደሚችል ስትነገረው አለመቻሉን ካረጋገጠለህ ያንተ እንዲረዳህ መጠበቅ ከንቱ ድካም ነው። ህይወቱን ይውደደው አይውደደው ያንተ ጉዳይ ባይሆንም በምትችለው መንገድ ማስረዳትህን ግን እንዳታቆም። አሉታዊ ሰዎች ባሉበት አለም ከአስደናቂ ተዓምር ውስጥ እንኳን ህፀፅና ክፍተት መታየቱ አይቀርም። አብዛኛው ሰው የሚፈልገውን እንጂ የሚያስፈልገውን አያይም። በኡሉታዊነቱም ፍላጎቱ አሉታዊና መጥፎ ሃሳብ ነውና የፈለገውን ነቅሶ ለማውጣት ዘወትር ይተጋል።
አዎ! በመደበኛው ክልል ተከልለህ፣ በጊዜያዊ ሁካታ ተከበህ፣ ማንም የሚያደርገውን እያደረክ፣ መንጋውን እየመራህ አንዳች ነገር ጠብ እንዳላለልህ ካንተ በላይ ምስክር የለም። የተለየ ነገር መፍጠር ከፈለክ ለእራስህ ጤነኛና የመልካም ስሜት ባለቤት ብትሆንም በብዙዎች ግን እብድ መባል ይኖርብሃል። በሁለት መልኩ እብድ ልትባል ትችላለህ፤ አንድም በሃሳብህ፣ ሌላም በተግባርህ። የተለየ ነገር ለማሰብ ተጠንቅቀህ፣ አዲስ ድርጊት ለመፈፀም የሰውን ምላስ ጠብቀህ እስከ መቼ ትዘልቀዋለህ? ስታስብለት የማይገባው ቢገጥምህም እንዳልገባው ለመረዳት መጣርህን ትተህ እስኪገባው መወትወትህን ቀጥል። አንዳንዴ በቀጥታ የተነገረለት ሰው ባይጠቀመውም በተዘዋዋሪ የሚጠቀመው ሰው ይኖራል። አላማህ መቀየር፣ ማደግ፣ ለሰዎች መትረፍ፣ ህይወትን በሙላት መኖር ከሆነ ምንህንም ለማያውቅ ሰው ብለህ ወደኋላ አትመለስ፤ በእራስህ አትዘን፣ ተስፋ አትቁረጥ፤ አላማህን አትዘንጋ። በሚያዋጣህ መንገድ ጉዞህን ቀጥል፤ ያመንክበትን ማድረግህን ግፋበት፤ ከግብህ የሚያደርስህ እንደብረት የጠነከረ ፅኑ አቅም ይኑርህ።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊 💪