ተነሱና ስሩ!
አጭር ነው፣ ግልፅ ነው፣ አሁን መደረግ የሚችል ነው፣ በትንሹ የሚጀመር ነው። አሁን ምንም ስራ ከሌላችሁ፣ ምንምአይነት የገቢ ምንጭ ከሌላችሁ ስራ መናቅ አቁሙና ምንም ይሁን ምን ተነሱና ስሩ፣ ተነሱና ወደ ተግባር ግቡ። ገቢ አስጋስገኘ ድረስ ከባህል ከእሴታችን፣ ከሀይማኖት ከትውፊታችን እስካልወጣ ድረስ ምንም የወረደ ስራ የለም። ስራ እየናቀ ህይወቱን የቀየረ ሰው የለም፣ ስራ እየመረጠ የከበረ ሰው የለም። በቀኝም ዞራችሁ በግራ ስራ የማትሰሩ ከሆነ ማንም የሚሰራው ላይ የመፍረድና ጣት የመቀሰር መብቱ የላችሁም። ቁጭ ብላችሁ ብዙ ገንዘብ ታገኙ ይሆናል፣ ከቤተሰብ ከወዳጅ ከዘመድ የወጪ ታገኙ ይሆናል ነገር ግን ከሰው የሚመጣ ነገር ሁሌም የእናንተ ሊሆን እንደማይችል እወቁ። እድሜያችሁ ለስራ ደርሶ፣ አቅማችሁ ጎልብቶ፣ ገንዘብ አስፈልጓችሁ ቁጭ ብላችሁ ሰውን መለመን ልማዳችሁ ካደረጋችሁ አሁኑኑ ብትነቁ ይሻላችኋል። ምንም ስራ ሳይኖራቸው ስራን የሚንቁ፣ ምንም የሚያስገቡት ገቢ ሳይኖር ትንሽ ገንዘብ የሚንቁ ሰዎች በገዛ እጃቸው ለውድቀት ራሳቸውን የሚያመቻቹ ሰዎች ናቸው። የሚሰራን እየናቃችሁ ህይወታችሁ እንዲቀየር አትፈልጉ።
አዎ! ተነሱና ስሩ! ወስኑና እርምጃ ጀምሩ። ሳይሰሩ፣ አንዳች የወደቀ ነገር ሳያነሱ፣ ምንም እንቅስቃሴ ሳያደርጉ እንዲሁ ራስን ጠብቆ ፅድት ንፅት ብሎ መውጣት እውቀትም ጥበብም አይደለም። መስራት እየቻለ ሳይሰራ የሚበላ፣ ህይወቱን የመቀየር አቅም እያለው ከሰው የሚጠብቅ፣ ራሱን መቻል ሲኖርበት ለዓመታት ሰውን የሚያስቸግር እርሱ የመጨረሻ ሰነፍና የወደቀ ሰው ነው። የማይገባችሁን ቦታ ለራሳችሁ አትስጡ፣ ከአቅማችሁ በላይ ለመኖር አትሞክሩ፣ ሰው እንዲያዝንላችሁ ራሳችሁን አቅመቢስ ደካማ አታድርጉት። ሁሌም ቢሆን ባለው ያምርበታል፣ የሰራ፣ የለፋ፣ የሞከረ ህይወቱን ያሸንፋል። ጥሮ፣ ግሮ፣ ለፍቶ ሞክሮ ያልተሳካለትና እንዲሁ ቁጭ ብሎ የሰው እጅ የሚጠብቅ መሃል ያለው ልዩነት እጅግ ሰፊ ነው። ስለሰራችሁ ብቻ በአንዴ ያልፍላችኋል ማለት አይደለም፣ ምንም ካልሰራችሁ ግን መቼም አያልፍላችሁም። ያ ሞክሮ የተሳሳተው፣ የሚችለውን አድርጎ ያልተሳካለት ሰው የጊዜ ጉዳይ እንጂ ሙከራውን እስካላቆመና ጥረቱን እስከቀጠለ ድረስ አንድ ቀን የፈለገበት መድረሱ አይቀርም። ነገር ግን ምንም የማይሞክረው፣ ምንም ጥረት የማያደርገው ሰው መቼም ስኬታማ እንደማይሆን እርግጠኛ መሆን ይችላል።
አዎ! ጀግናዬ..! አራዳ ሁን። ባለው አየር ተንቀሳቅሰህ ህይወትህን ወደፊት ፈቀቅ አድርገው፣ ያገኘሀውን እየሰራህ ቀስ ብለህ እደግ። ድህነት ቤት እስኪሰራብህ አትጠብቅ። ትንሽም ብትሆን ሰርተህ የምታገኛት ጥሪት ነፃነትን ትሰጥሃለች፣ በራስመተማመንን ታጎናፅፍሃለች፣ በራስህ እንድትኮራ ታደርጋለች። ስራም ሆነ ገንዘብ፣ ሰራተኛም ሆነ ለፍቶ አዳሪ አትናቅ። የወጣት ተጧሪ ከመሆን ምንም ስራ ሳይመርጡ መስራት እጅጉን ያስከብራል። ዘመኑ እንኳን ሳይሰራ ተሰርቶም ከባድ ሆኗል፣ ጊዜው እንኳን እጅ አጣጥፎ ተቀመጦ ቀን ከሌሊት ተለፍቶም አልሸነፍ ብሏል። በፍፁም ማንም የሚበጅህን እንዲነግርህ አትፈልግ፣ በፍፁም ማንም እስኪጎተጉትህ አትጠብቅ። ራስህን ግፋው፣ ራስህን ስቃይ ውስጥ ክተተው፣ ራስህን ከመቾት ውስጥ አስወጣው። ጥረህ ግረህ፣ ለፍተህ ደክመህ በላብህ የራስህንም በዙሪያህ ያሉ ወዳጆችህንም ህይወት ቀይር። ጊዜው ጥሎህ እየሔደ አንተ ወደኋላ አታፈግፍግ። ከጊዜ እኩል ተራመድ፣ ለነፃነትህ የሚጠበቅብህን መሱዓትነት ሁሉ ክፈል።