ማንም አይሰጣችሁም!
ያሳዝናል ነገር ግን እውነታው ይሔ ነው፣ ያበሳጫል ነገር ግን መሬት ላይ ያለው ሃቅ ይሔው ነው። ለምን የቅርብ ዘመዳችሁ አይሆንም፣ ለምን አባት እናታችሁ አይሆኑም፣ ለምን ከማንም በላይ የሚወዳችሁ ሰው አይሆንም ማንም ሽራፊ ሳንቲም አይሰጣችሁም፤ ማንም በምትፈልጉትና በምትጠብቁት ልክ ሊረዳችሁና ሊተባበራችሁ አይመጣም። የናንተ ህይወት የእናንተና የእናንተ ሃላፊነት ብቻ ነው አለቀ። ሞኝ አትሁኑ፣ በልክ አልባ የዋህነት ጣሪያ አትንኩ። አስቡት እሱ ምናችሁም ሊሆን ይችላል ለዓመታት ለፍቶ፣ ደክሞ፣ ወጥቶ ወርዶ፣ ተጋግጦ ብዙ ዋጋ ከፍሎ ካፈራው ንብረት ቆርሶ ለምን ይሰጣችኋል? ለምን በምላሹ ምንም ሳያገኝ አንስቶ ይሰጣችኋል? ስለሚወዳችሁ ወይስ ስለማይፈልገው? ውለታችሁ ስላለበት ወይስ ስለተበደራችሁ? አትሸወዱ እንኳን በቅርብ ጊዜ ያወቃችሁት ሰው ይቅርና እድሜ ልካችሁን የምታውቁት የቅርብ ዘመዳችሁ እንኳን ምንም ነገር አንስቶ ያለምክንያት አይሰጣችሁም። ምናልባት ዛሬ ላይ "እኔ በእርሱ ቦታ ብሆን እሰጣለሁ" ትሉ ይሆናል። ነገር ግን ስሜቱን የእርሱ ቦታ እስካልሆናችሁ ድረስ ልታውቁት አትችሉም።
አዎ! ራሳችሁን ቻሉ፣ በራሳችሁ ተመፅዋችነት የምታዝኑ ሰው አትሁኑ። በሙሉ ጤንነት ሆኖ መለመን እውቀትም ጥበብም አይደለም። መስራት ያለባችሁን ሰርታችሁ ህይወታችሁን ቀይሩ። ጓደኛ ከድህነት አያወጣችሁም፣ ሀብታሙ አጎታችሁ ህይወታችሁን አይቀይረውም፣ ቤተሰብ የምትፈልጉትን ሁሉ አይሰጣችሁም። የማታገኙትን ነገር ከሰው አትጠብቁ፣ በሰው እጅ ያለን ወርቅ አትናፍቁ። ምንም ነገር የእናንተ የሚሆነው ራሳችሁ ሰርታችሁ ያገኛችሁት እለት ብቻ ነው። በበዛው የዋህነታችሁ አስቂኝ ሰው አትሁኑ። አትልፋ ማንም አይሰጣችሁም፣ እንዲሁ በባዶ አትድከሙ ማንም ለእናንተ ብሎ ዋጋ የሚከፍል የለም። አንዳንድ ሰው ሌላው ሰው "ለምን አላሰበልኝም? ለምን የምፈልገውን ነገር አስቦ አይሰጠኝም? ለምን የጠየኩትን ሁሉ ነገር አያሟላልኝም?" ብሎ በሰውዬው ይበሳጫል። መስጠት ቢኖርበት እንኳን ስንት ሊሰጠው የሚገባ ምስኪን ህዝብ እያለ፣ ስንተ የፅቅን በር ሊያስከፍት የሚችል በጎ ስራ እያለ ለምን ላንተ ይሰጥሃል? ምን ለማግኘት ሰርተህ መቀር የምትችልን ሰነፍ ሰው ሊደጉም ይችላል?
አዎ! ጀግናዬ..! ራስህን አትግደል፣ በሀሳብ አንሰህ ራስህን አታሳንስ፣ የመስራት አቅሙ እየለህ፣ ከራስህ በላይ ለሰው መትረፍ እየቻልክ ዕድሜህን በሙሉ ፍርፋሪ እየለቃቀምክ አትኑር። ከሰው መጠብቅ ቀስ በቀስ ይገልሃል፣ ሰውን ደጅ መጥናት እያደር ዋጋህን እያሳነሰ የተናቅክ ሰው ያደርግሃል፣ ሰውን መለማመጥ በሂደት ፈሪና በራስ መተማመን የሌለው ልፍስፍስ ያደርግሃል። በጊዜ መረዳት ካለብህ ተረዳ ወደፊት ከሚገፋህና ከሚረዳህ በላይ ወደኋላ የሚጎትትህና ከጉዞህ የሚያደናቅፍህ ሰው ይበዛል። በድህነቱ ከሚመፃደቅ ምስኪን ሰው ጋር ህብረት አትፍጠር፣ በሀብቱም ከልክ በላይ ከሚመካ ሰው ጋር የጠለቀ ግንኙነት አይኑርህ። ሁለቱም ባላሰብከው መንገድ አስተሳሰብህን እየሸረሸሩት ዋንኛ ተከታያቸው ያድርጉሃል። የደሃ ቅንጡ በድህነትህ እንድትኩራራ ያደርግሃል፣ የሀብታም ኩሩም ሁሌም አገልጋዩ እንድትሆን ያደርግሃል። ዛፍ በእድሜው እንደሚያጎበድድ ሁሉ አንተም በጊዜህ ሳታጎበድድ በፍጥነት ራስህን ቻል፣ የራስህን የተለየ ማንነት ፍጠር፣ እውቀትና አቅምህ የሚታይበትን ተግባር ፈፅመህ ተገኝ።