አትነካካ!
ለምን ከብዙዎች መሐል ተመራጭ እንዳልሆንክ ታውቃለህ? ለምን በብዙዎች ዘንድ ተፈላጊ እንዳልሆንክ ታውቃለህ? ለምን ስምህ በጉልህ እንዳልተጠራ፣ ስኬት እንደራቀህ፣ ዋጋህ እንዳነሰ ታውቃለህ? ሰነፍ ስለሆንክ አይደለም፤ ስለማትሞክር አይደለም፤ አላዋቂ ስለሆንክ አይደለም፤ የመሆን አቅሙ ስለሌለህም አይደለም። ምክንያቱ ብዙ ስለምታውቅ ነው፤ ምክንያቱ ብዙ ነገር ስለምትሞክር ነው፤ ምክንያቱ ብዙ ጅምሮች፣ ብዙ ያላለቁ የቤት ስራዎች ስላሉብህ ነው። ብዙ ነገር ታውቃለህ ነገር ግን በአንደኛውም እውቀትህ ጠለቅ ያለ ማብራሪያ መስጠት አትችልም፤ ብዙ ትሞክራለህ ነገር ግን በአንደኛውም ረጅም ርቀት ተጉዘህ አታውቅም፤ ብዙ ትጀምራለህ ነገር ግን ምንም የጨረስከው ነገር የለም። ጀምረህ የተውካቸው የቤት ስራዎችህ ከመብዛታቸው የተነሳ መጀመርህንም ልትረሳቸው ትችላለህ።
አዎ! ጀግናዬ..! አትነካካ፤ እዚም እዛም አትበል፤ እራስህን አትበትን፤ እራስህን አታባክን። አንዱ ላይ እስከመጨረሻው አድፍጥ። የያዝከውን የመጨረስ ልማድ ይኑርህ። በመረጥከው ምርጫ፣ በወሰንከው ውሳኔ ላይ ፅናት ይኑርህ። ያማረህን ሁሉ እየሰራህ፣ የተባልከውን ሁሉ እያመንክ፣ ያየሀውን ሁሉ ለመጀመር እየተንደረደርክ በፍፁም ተመራጭና ስኬታማ ልትሆን አትችልም። ለጊዜው ያንተ የሆነው አንድና አንድ ነገር ብቻ ነው። አውቃለሁ ብለህ ያገኘሀውን አትቀላቅል፤ ገብቶኛል ብለህ በየቦታው በተንታኝነት አትሰየም፤ በምሁርነት ስም ሀገርን አታፍርስ። ሁሉም ዘርፍ የእራሱ ምሁር አለው፤ የእራሱ መምህር፣ የእራሱ ተንታኝ አለው። ተመራጭነት በሰው ሙያ ሳይሆን በእራስ ሙያ ነው፤ አንቱታ የሚገኘው፣ ተቀባይነቱ የሚመጣው፣ ስምና ዝናውም የሚገነባው በጥራትና በጥልቀት በሚሰራ ስራ ነው። ነካክቶ በማለፍ ከመካከለኝነት አይወጣም፤ በየቦታው እጅን በማስገባት ተፅዕኖ ፈጣሪነት አይመጣም።
አዎ! ነገሮችን በእራስህ ላይ አታክብድ። በቅድሚያ የዘራሀው ዘር ፍሬ እስኪያፈራ፣ የተከልከው ተክልም ለጥላነት እስኪበቃ ጠብቅ። በአንዴ አስር ተክል ተክለህ አትሰቃይ፤ በአንዴ በየዘርፉ ስኬታማ ካልሆንኩ እያልክ እራስህን አታባክን። የጀማሪ አቅሙ ለጊዜው አንድ ነገር ብቻ ነውና ስትጀምር አንድ ይበቃሃል፤ በሂደት ግን በየዘርፉ ማደግ ትችላለህ። ሁሉም ነገር ላይ ተሳታፊ የመሆን፣ ሁሉንም ነገር የማወቅ፣ ሁሉንም ነገር የመሞከር ግዴታ እንዳለብህ አታስብ። ሁላችንም የምንችለውና የሚገባን ዘርፍ ይኖረናል። በእርሱ ላይ ሃላፊነታችን በመወጣት የቀረውን ለባለቤቱ የመተው ልማድ ያስፈልገናል። እራስህን ከዚህም ከዛም ጋር አታነካካ፤ ስትጠየቅ "እኔም ጀምሬው ትቼው ነው።" የማለትን ልማድ አስወግድ። ጅማሬህ ካልጀመሩት የተሻልክ ያደርግህ ይሆናል እንጂ በፍፁም ለሚገባህ የከፍታ ደረጃ እንደማያበቃህ እውቅ።