ራሳችሁን ከልሉ!
ጤንነታችሁ ክፉኛ የሚያሳስባችሁ ከሆነ፣ የምርም የተረጋጋና ሰላማዊ ህይወትን መምራት የምትፈልጉ ከሆነ፣ የእውነት ንፁህና ነፃ ህይወትን መኖር የምትፈልጉ ከሆነ ለራሳችሁ አንድ ውለታ ዋሉ። እነርሱ ችግር እየፈጠሩባችሁ እናንተን እንደ ችግር ፈጣሪ፣ እየጎዷችሁ እነርሱ እንደተጎዱ፣ እያሳመሟችሁ እንዳሳመሟቻቸው ከሚያስቡ ሰዎች በፍጥነት ራቁ። ላለፈ የጋራ ታሪክ ብቻ ብላችሁ የዛሬና የወደፊት ህይወታችሁን አታበላሹ። ከሰው ጋር ስንኖር የሚሆነንና የሚበጀንን ሰው የመምረጥ ግዴታ አለብን። ካልሆነ ግን ራሳችንን ለብዙ ጥፋትና ቁስል አሳልፈን የምንሰጥ እንሆናለን። ችግር በማንም መቼም ሊፈጠር ይችላል፣ የሰው ልጅ አቅዶም ይሁን በአጋጣሚ ሊጎዳችሁ ይችላል ዋናው ቁብ ነገር ግን ለችግሩ ወይም ለጉዳቱ የምትሰጡት ምላሽ ነው። አንድ ወንዝ መፍሰሱን የሚያቆመው የተገደበ እንደሆነ ወይም የደረቀ እለት ብቻ ነው። እናንተም ችግሩን መፍታት የምትችሉት አንድም ከችግር ፈጣሪው ስትርቁ ወይም ዳግም ችግር እንዳይፈጥርባችሁ ስታሳስቡት ብቻ ነው።
አዎ! በፍቃዱ የሚጠቃ፣ ወዶ የሚጎዳ፣ አማራጭ አጥቶ ተጠቂ የሆነ ሰው አትሁኑ። ከጉዳት፣ ከበደል፣ ከጥፋት፣ ከከፋው ውድቀት ራሳችሁን ከልሉ፣ ራሳችሁን ጠብቁ። ህብረታችሁን በጥንቃቄ መርምሩ፣ ከማን ጋር ህይወታችሁን ለመምራት እንዳሰባችሁ በሚገባ እወቁት። ከማንም በላይ የሰውን ልጅ ሊያጠፋ የሚችለው ብቻኛ ፍጡር ራሱ የሰው ልጅ ነው። አብዛኛዎቹ የዓለም አሁናዊ ችግሮች የተፈጠሩት በሰው ልጆች ነው፤ ብዙ ሰው ለህመም፣ ለስቃይ፣ በቀላሉ ለማይሽር የልጅነት ጠባሳ የሚዳረገው፣ ገና እድሜው ሳይደርስ ብዙ ፈተናን ብዙ ውጣውረድን የሚያየው፣ ደጋግሞ ወድቆ የሚነሳው በሰው ምክንያት ነው። ስኬታችሁ እንደ እሾህ ከሚወጋው ሰው ጋር ሆናችሁ መቼም ስኬታማ ልትሆኑ አትችሉም፤ አላማችሁን ለመኖር መጣራችሁ ምቾት ከሚነሳው ሰው ጋር እየኖራችሁ መቼም ህልማችሁን ልትኖሩ አትችሉም። ከየትኛውም እርምጃችሁ ፊት የሚቀድመው አካባቢያችሁን ማፅዳትና ማስተካከል ነው። ወደ የትኛውም ከፍታ ለመውጣት የግድ ሸክም የሆኑ ክብደቶችን የመቀነስ ግዴታ ይኖርባችኋል።
አዎ! ጀግናዬ..! ራስህን መጠበቅህ፣ ዙሪያህን ማጠርህ፣ ራስህን መከለልህ ኩራት ወይም ንቀት አይደለም። ይልቅ እርሱ ራስን መውደድ፣ ራስን ማክበርና ራስን መግዛት ነው። የቅርብ ዘመዶችህ፣ ጓደኞችህ፣ የስራ ባልደረቦችሁ፣ ቤተሰቦችሁ ሊሆኑ ይችላሉ ነገር ግን ለእያንዳንዳቸው የራሳቸው ገደብና ልኬት ያስፈልጋቸዋል። ሰው ጎድቶህ እንደጎዳሀው የሚያስመስለው በፈቀድክለት ልክ ነው፣ ሰው አሰናክሎ ጥሎህ በራስህ ጥፋት እንደወደቅክ የሚነግርህ ማንነትህን ያወቀ እለት ነው። ከሰው ጋር በሰላምና በመከባበር መኖር ከፈለክ ሰውን አክብር አንተም የሚከበር ማንነትን ፍጠር። ሁሌም እየተጠቁና እየተጎዱ መኖር ትልቅ ረፍት አልባ ስቃይ ነው። አዳኝ ፈጣሪ ነው፣ ከአጣብቂኝ የሚያወጣ አምላክ ነው። ነገር ግን አንተም የራስህን ድርሻ መወጣት ካልቻልክ እርሱ ሊረዳህ አይችልም። የትኛውም ነፃነት ትግል አለው ይፈትናል፣ እንዲሁ ሰላማዊና የተረጋጋ ህይወት መኖር ዋጋ ያስከፍላል። እርሱን ለማድረግ አታመንታ፣ በፍቃድህ ለገዛ ሰላምህ ዘብ ቁም።