እመን ታሸንፋለህ!
ውስጥህን አዘጋጅ፣ ለምታምነው አምላክ የልብህን በር ክፈት፣ እራስህን አረጋጋ፣ ምንም እንዳልተፈረም እያሰብክ የእምነት ደረጃህን መዝነው። በእርግጥ አማኝ ነኝ ብለህ ታስባለህ? አማኝ በእምነቱ አሸናፊ ነው። እናም አንድ ጥያቄ እራስህን ጠይቅ፦ የምርም ማሸነፍ የምፈልገው ነገር አለን? ተሻግረሀው ማለፍ የምትፈልገው፣ ጥለሀው መሔድ የምትፈልገው፣ ሸክሙን ማራገፍ፣ ከጭንቀቱም መገላገል የምትፈልገው ነገር አለህን? ከማንም ሰው የተለየህ አይደለህምና እንደ ማንኛውም ሰው የግል ጦርነት ይኖርብሃል፤ እለት እለት የሚያታግልህ፣ በነጋ ቁጥር ከፊቱ የምትቆመው፣ እንደ አዲስ የምትገዳደረው የህይወት ፈተና አለበህ። እንደምታሸንፈውም እርግጠኛ አይደለህም፤ ነገር ግን መጋፈጥ ስላለብህ ብቻ ትጋፈጠዋለህ፣ መታገል ስላለብህ ብቻ ትታገለዋለህ።
አዎ! ጀግናዬ..! እመን ታሸንፈለህ! በእግዚአብሔር አምላክህ ተማመን ጥለሀው ትሔዳለህ፤ ፈጣሪህን አስቀድመህ ተዋጋው ትማርከዋለህ። ሰውነትህ ደካማ ነው አብሮት ያለው ፈጣሪህ ግን ሃያል ነው፤ ሰውነትህ ተስፋ ይቆርጣል አብሮህ የሚሰራው አምላክህ ግን በእራሱ ተስፋ ነው፤ ፀጋ ነው፤ በረከት ነው፤ አሸናፊ ነው፣ ድል አድራጊ ነው። ለአማኝ ማሸነፍ ብርቁ አይደለም፤ እውነታን ለሚይዝ፣ ከእውነት ለሚጠጋ መሰናክልም ብርቁ አይደለም። ምክንያቱም የሚያምነው ሞትን ባሸነፈ አምላኩ ነውና ነው፤ ምክንያቱም እውነት በእራሱ ፈጣሪው ስለሆነ ነው። በህይወት እስካለን ድረስ የምድር ፈተና ማብቂያ የላትም። በተለይ በተንሹም በትልቁም የምንጨነቅና የምንሰበር ከሆንን ፈተናችን በእጥፍ ይጨምራል። እውቀታችን ውሱን ብትሆን እንኳን አምላክ በሚያድለን በረከትና ፀጋ ግን ለአሸናፊነት የሚያበቃንን፣ ከመዳረሻችን የሚያደርሰንን፣ ህልማችንን እውን የሚያደርግልንን ጥበብና ማስተዋልን እንወርሳለን፣ መንፈሳዊ ብለሃትንም እንላበሳለን።
አዎ! እምነት የጦር ጋሻችን ነው። ቃሉም እንደሚለው "ለሚያምን ሁሉ ይቻለዋል።" ማንን ማመን እንዳለብን ካወቅን ከልባችን የማመኑ ጉዳይ የእራሳችን ነው። እመን ታሸንፋለህ። የምታምነው በነፍስህ ነው፤ የምታምነው በጥልቁ ማንነትህ ነው። እምነትህን ሆነህ ማሳየት ይጠበቅብሃል፤ እምነትህን በየቀኑ እየኖርከው ልትገልፀው ይገባል። እምነታችን ስለጎደለ ብቻ የምንፈልገውን ብዙ ነገር አጥተናል፤ መድረስ ከሚገባን ደረጃ ቀርተናል። ያለችው ትንሿዋ እምነትህ በምንም በማንም እንድትሸረሸር አትፍቀድ፤ ማንም ተስፋህን እንዲቀማህ፣ በደስታህ እንዲቀልድና ሰውነትህን እንዲያሳንስ እድል አትስጠው። ከቃል በላይ በተግባር ስታምን ሁሉም የሚበጅህ ነገር እንደሚከናወንልህ አትጠራጠር።