እርሱን ታምኜ እወጣለሁ!
ከራስ ጋር ንግግር፦ " አዎ! እርሱን ታምኜ፣ እርሱን አምኜ፣ በእርሱ ተደግፌ አወጣለሁ እገባለሁ፣ አምላኬን ይዤ ባህሩን እሻገራለሁ፣ አውሎ ንፋሱን አልፈዋለሁ፣ ፈተናዬን እፈትነዋለሁ፣ ችግሬን አስቸግረዋለሁ። እንደማንኛውም የሰው ልጅ ትልቅ ራሃብ አለብኝ፣ እንደ ማንኛውም ሰው ይጠማኛል። መንፈሴ ይራባል፣ ነፍሴ ትጠማለች። መንፈሴም የሚጠግበው፣ ነፍሴም የምትረካው አምላኳን ያገኘች እለት ነው፣ በእርሱ ጥላ ስር የተከለለች እለት ነው፣ ከስጋዋ በላይ ሆና ለእርሱ የተገዛች እለት ነው። ትናንተ ስታገል ነበር፣ ዛሬም እየታገልኩ ነው፣ ነገም እንዲሁ ትግሌ ይቀጥላል። ሲሆን ሲሆን ግን ያለፈው ትግሌ በዓለም ለመድመቅ፣ ስጋዬን ለማድመቅ፣ ክብሬንም ለመጨመር ቢሆንም ከአሁን ቦሃላ ግን ድካሜ ሁሉን ነፍሴን ለማጉላት፣ መንፈሴን ለማርካት፣ አምላኬንም ለማስደሰት እንዲሆን እፈልጋለሁ። ባልናገረውም ነፍሴ ግን እሱን ታምናለች፣ እንዲህ በቃላት ባልዘረዝረው ውስጤ ግን በእርሱ ፍቅር ተማርኳል። እርሱን አምኜ ወጥቼ አፍሬ አላውቅም፣ እርሱን ተማምኜ ወጥቼ አንገት ደፍቼ አላውቅም። እርሱን ሳስብ ልቤ ትልቅ ነው፣ ፍቅሩን ለመለካት ስሞክር መለኪያ አላገኝለትም።
አዎ! እርሱን ታምኜ እወጣለሁ፣ አምላኬን ታምኜ እገባለሁ። መውጫና መግቢያዬን የሚጠብቅልኝ ድንቅ መካር ሃያል ጌታ አለኝ። ብዙ ክፉ ነገር ሲናገር ያላፈረው አንደበቴ የአምላኩን ድንቅ ስራ መናገር ክብሩ እንጂ እፍረቱ አይደለም። ኬት አንስቶ የት እንዳደረሰኝ፣ ከምንአይነት ማንነት እንደቀየረኝ፣ እንዴት አድርጎ ዳግም እንዳበጃጀኝ እኔና እርሱ ብቻ እናውቃለን። ለዘመናት ያደረገልኝን ሳልመሰክር ቆይቼያለሁ፣ ለዓመታት የሚሰጠኝን ሁሉ እንደ ግዴታ ስቆጥርበት ሰንብቼያለሁ። ከረፈደም ቢሆን አሁን ፍቅሩ ገብቶኛል፣ ጊዜው ከሔደም ቢሆን ማዳኑን ተመልክቼያለሁ። በስኬቴ ውስጥ ፍቅሩ አብሮኝ ነበር፣ በውድቀቴ ውስጥም እንዲሁ ፍቅሩ ነበር። "አሁን ተሳክቶለታል፣ ነገሮች ሁሉ ሆኖለታል የእኔ እርዳታ አያስፈልገውም በራሱ መንገድ ይሒድ" ብሎ ትቶኝ አያውቅም። "አሁን ወድቆል፣ የዲያብሎስ መጫወቻ ሆኗል፣ ኀጢአት ሰልጥኖበታል፣ አይነ ልቦናው በፍቅረ ነዋይ ታውሯል፣ ራሱን ለዓል ሰጥቷል" ብሎ በእኔ ተስፋ ቆርጦ ረስቶኝ አያውቅም። የዘላለም አባቴ ነውና እርሱ እንደ አባት ይጠብቀኛል፣ እኔም ልጁ ነኝና እንደ ልጁ እታዘዝለትና በሚመራኝ መንገድ እጓዝ ዘንድ እንደሚያበረታኝ አምናለሁ፣ አምኜም በእርሱ ፊት እመላለሳለሁ።"
አዎ! ጀግናዬ..! አንድ ሁለቴ ሳይሆን በጣም ብዙ ጊዜ እምነትህ ይፈተናል፣ አንድ ሁለቴ ሳይሆን በጣም ብዙ ጊዜ ለአምላክህ ያለህ ፍቅር ይፈተናል። ነገር ግን ፈተና ሁሉ ሊጥልህ እንደማይመጣ አስተውል። አብዛኛው ፈተናህ ለቀጣይ ጉዞህ መንገድ ከፋች ነው። እምነትና ፍቅር የሚፀኑት በከባባድ ፈተናዎች ወቅት ነው። ፅናት የሌለው እምነት እምነት አይደለም፣ በትዕግስት የማይመራ ፍቅር ፍቅር አይደለም። የአምላክን አሰራር ብዙ ለመመርመር አትሞክር። ዝም ብለህ ራስህን እየተመለከትክ እመን፣ እንዲሁ ላንተ ያደረገልህን እያስታወስክ አመስግነው። "ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ? ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ? ወደ ሰማይ ብወጣ አንተ በዚያ ነህ ወደ ሲኦልም ብወርድ በዚያ አለህ።" እንዳለ ቅዱስ ዳዊት አምላክህን አትሽሽ፣ ከእርሱም ተሰውረህ ለማጥፋት አትሞክር። የትም ሒድ እርሱ እዛ አብሮህ አለ፣ ምን አድርግ እርሱ እያንዳንዱን ድርጊትህን ያያል። ከማታመልጠው አባትህ ስር ለማምለጥ አትሩጥ፣ ይልቅ በእርሱ አምነህ ውጣ፣ በእርሱ ተማምነህ ግባ፣ የዓለምህም ገዢ፣ የምድራዊ መርከብህም ካፒቴን ሁን።