ጉዞ ላይ ናችሁ!
ያላችሁበት ሁኔታና ቦታ የማይመች፣ አሰልቺ፣ ለእናንተ የማይመጥንና “ራሴን እዚህ ቦታ አገኘዋለሁ ብዬ አላስብም ነበር” የሚያሰኝ ቢሆንም፣ “እንኳን በዚያ ሁኔታ አለፍኩ” የምትሉበትን ሁኔታ መፍጠር ትችላላችሁ፡፡ ያንን ለመፍጠር ግን በጉዞ ላይ መሆን አለባችሁ፡፡
1. ትምህርት፡- ካላችሁበት ሁኔታና ቦታ የምታገኙትን ሁሉ ትምህርት ውሰዱ፡፡ አንዳንድ የሕይወት ትምህርቶች በሁኔታው ካላለፋችሁ በስተቀር በፍጹም አትማሯቸውም፡፡ አንድ ልምምድ ጎጂን የባከነ የሚሆነው ትምህርት ካልተገኘበት ብቻ ነው፡፡
2. ውሳኔ፡- ካላችሁበት ሁኔታና ቦታ ለመውጣት ተገቢውን ውሳኔ አድርጉ፡፡ ዋናው ነገር የላችሁበት ሁኔታ ሳይሆን በዚያ ላለመቆየት ያላችሁ ምርጫና ውሳኔ ጉዳይ ነው፡፡
3. እቅድ፡- ካላችሁበት ሁኔታና ቦታ የምትወጡበትን ተገቢውን እቅድ አቅዱ፡፡ ካላችሁበት ሁኔታ ለመውጣት መወሰን ለብቻው በቂ አይደለም፡፡ በሚገባ የታሰበበትና ተግባራዊ ሊሆን የሚችልን እቅድ ከጊዜ ገደብ ጋር ማስቀመጥ የግድ ነው፡፡
4. እንቅስቃሴ፡- ካላችሁበት ሁኔታና ቦታ ለመውጣ ተገቢውን እቅስቃሴ አድርጉ፡፡ ከትምህርቱ፣ ከውሳኔውና ከእቅዱ በኋላ፣ ባቀዳችሁት መሰረት ወቅቱን ጠብቃችሁ መንቀሳቀስ ከቻላችሁ የላቀ ማንነት ይዛችሁ መውጣታችሁ አይቀርም፡፡
ከላይ የተጠቀሱትን ተግባራዊ እውነታዎች ከተለማመዳችሁ ያላችሁበት ቦታ በእርግጥም የምትማሩበት፣ የምታድጉበትና ለነጋችሁ በስላች የምትወጡበት ትክክለኛ ሁኔታና ቦታ ይሆንላችኋል፡፡