በቀላችሁን መልሱ!
ብትፈልጉም ባትፈልጉም ማንም ቆሞ አይጠብቃችሁም፣ ተመኛችሁም አልተመኛችሁም ምንም ነገር በነበር አይቀጥልም። ያለፈው አልፏል፣ የሆነው ሆኗል፣ የሚሆነውም ወደፊት ይሆናል። በእናንተ ምርጫ ሳይሆን መሆን ስላለበት ይሆናል። በገዛ ፍቃዳችሁ ዓለም እንድትገፋችሁ፣ በምርጫችሁ ምድር ፊቷን እንድታዞርባችሁ፣ ሰዎችም እንዲርቋችሁ አታድርጉ። ህይወትን እንድ ህይወት ኑሯት፣ የግል ዓለማችሁን ሰፋ አድርጋችሁ ተመልከቷት፣ ያመለጣችሁን የተሻለ ኑሮ የመኖር እድል አሁን መበቀል ጀምሩ። ነገሮችን ሁሉ ግላዊ እያደረጋችሁ ራሳችሁን አታሰቃዩ። ከዚህ ቀደም የማትፈልጉትን ህይወት ስትኖሩ የነበራችሁት እናንተ ብቻ አይደላችሁም። ከዛ ህይወት ግን እናንተ ብቻ መውጣት ትችላላችሁ፣ ያንን ህይወት ግን እናንተ ብቻ ልትቋጩት ትችላላችሁ። በእርግጥ የሰው ህይወት አይመለከታችሁም ነገር ግን ውድቀትና ችግራችሁን ግላዊ ካደረጋችሁ በደምብ ይመለከታችኋል። በምንም ጉዳይ ከልክ በላይ ማዘን፣ መሳቀቅ፣ መጨነቅ አያስፈልግም። ከእናንተ አቅም በላይ የሆነን ነገር አምናችሁ ተቀበሉት፣ የእናንተ ጉዳይ ያልሆነን ነገር ተውት። ብዙ ጥላችሁ ልታልፉት የሚገቡ የህይወት ፈተናዎች እያሉባችሁ ከሰው ጋር ተጨማሪ ግግብግብ ውስጥ አትግቡ።
አዎ! የሰው ሳይሆን በሙላት የመኖር በቀላችሁን መልሱ፣ የክህደት ወይም የመገፋት ሳይሆን ከፍ ብሎ የመኖር በቀላችሁን፣ በስኬት መንገድ የመመላለስ አምሮታችሁን፣ ተርፎ ተትረፍርፎ የመኖር ምኞታችሁን መልሱ። ሰው መጣ ሰው ሄደ፣ አንዱ ጠቀማችሁ አንዱ ጎዳችሁ፣ በአንዱ አተረፋችሁ በአንዱ ከሰራችሁ፣ አንዱ አስደሰታችሁ አንዱ አሳዘናችሁ። ህይወት ግን በዚህ ነገር አትቆምም። ፈጣሪ የፈቀደው መሆኑ ላይቀር የሰውን በደልና ክፋት እየቆጠራችሁ ልባችሁን አታስጨንቁት፣ ከሆነላችሁ መልካም ነገር በላይ የሆነባችሁን መጥፎ ነገር አትቁጠሩ። ሰው እያሳደዳችሁ ህይወታችሁን በሚገባ ሳትኖሩ እንዳታልፉ፣ እድሜ ልካችሁን ስለሰው ጉዳይ እየተጨነቃችሁ የራሳችሁን ህይወት ባዶ አታድርጉት። መበቀል ካለባችሁ ሰውን ሳይሆን ራሳችሁን ተበቀሉ፣ መናደድ ካለባችሁ በሰው ሳይሆን በራሳችሁ ጥፋት ተናደዱ። ሰው ላይ ጣት መጠቆም እናንተን ጠንካራ ወይም ፃድቅ አያደርጋችሁም፣ የሆነ አካል መርጣችሁ መውቀስ ለእናንተ የሚያመጣላችሁ የተለየ ነገር የለም። ትርፍ ያለው ህይወት መኖር ከፈለጋችሁ፣ ትርጉም በሚሰጣችሁ መንገድ መመላለስ ካሰባችሁ እለት እለት ራሳችሁን ውቀሱ፣ ከባዶ ወቀሳም በላይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ራሳችሁን አስጨንቃችሁ ፍሬ አፍሩ።
አዎ! ጀግናዬ..! ፍፁም ነፃ አውጪው በቀል በሰው ላይ የምትወጣው በቀል ሳይሆን ራስህ ላይ የምትወጣው በቀል ነው። ማንኛውንም የጎዳህን ሰው ዳግም ብትጎዳው በሰውዬው ጉዳት የምታገኘው አንዳች ትርፍ የለም። ይልቅ የራስህን የቀደመ ጥፋትና በደል ሽረህ ራስህን በተሻለ መንገድ ብትበቀል ከአንተ በላይ የሚጠቀም አካል የለም። በቀል ሁሌም አሉታዊ ተግባር አይደለም፣ በቀል ሁሌም ጥፋት አይደለም። ራስህን ተበቀልክ ማለት ያመለጡህን ጥሩ የህይወት አጋጣሚዎች ተበቀልክ ማለት ነው። ባለፈ ጊዜ ላይ ቆመህ መጪውን ጊዜ ማስተካከል አትችልም። የትኛውም ስህተትም ሆነ ጥፋት የሚታረመው ከአሁን ጀምሮ ባለው መጪ ጊዜ ነው። ፊት ኋላህን አስተውል፣ ግራ ቀኝህን ተመልከት፣ መጣል መነሳት ያሉባቸውን ነገሮች ለይ፣ ቀና ብለህም አዋጩን ትክክለኛ መንገድ ተከተል። በተበዳይነት እሳቤ ራስህን እየወቀስክ አትኑር። ለራስህ ክብርና ዋጋ ስትል በፍፁም የጎዱህ ፊት ዝቅ አትበል፣ ከእነርሱ በላይ ራሳን ከፍ የማድረግ ትልቅ አጀንዳ እንዳለህ በተግባር አሳይ።