በእድልህ አትተማመን!
መዳረሻህ በእድልህ አይወሰንም፤ ስኬትህ በአጋጣሚ አይመጣም፤ ልዕልና እንዲሁ ከአየር ላይ የሚታፈስ አይደለም። በውሳኔህ ልክ ህይወት የምትሰጥህ ስጦታ አለ፤ በምርጫህ አኳሃን የምትደርስበት ስፍራ ይኖራል። በእድል የሚያምን ስኬት የተባለውን አስደሳችና ትርጉም ሰጪ ህይወት ሊያገኝ አይችልም። በአጋጣሚ ነገሮች ሊመቻቹልህ ይችላሉ፤ እንደ እድል ከቤተሰብህ ባገኘሀው ንብረት ልትከብር ትችላለህ፤ ሎተሪም ሊደርስህ ይችላል። ነገር ግን ያ ሁሉ በአጋጣሚ የመጣው ነገር በአጋጣሚ ቢጠፋ ዳግም የምታገኝበት እድልህ እጅጉን ያነሰ ነው። መርጠህ የመጣህበት ስትመለስ ሊጠፋብህ አይችልም። በአጋጣሚ የገባህበት ስፍራ ግን መውጫውም አዳጋች ነው። ምርጫህ ውጤት እስኪያመጣ ድረስ ከባዱ መንገድ ነው፤ እድል ግን ከውጤቱ ቦሃላም ሆነ በፊት ከባድ ሁኔታ መፍጠሩ አይቀርም።
አዎ! ጀግናዬ..! በእድልህ አትተማመን፤ አጋጣሚ ላይ አትደገፍ። በምትኩ ለምርጫህ ትኩረት ስጥ፤ በውሳኔህ ተማመን፤ ለፍላጎትህ የምትከፍለውን መሱዓትነት በሚገባ ጠንቅቀህ እወቀው። ለፍተው፣ ደክመው፣ ጥረው ግረው በተቀየሩ ሰዎች አትቅና። ከቻልክ የእነርሱን መንገድ ምረጥ፤ ካልሆነ ግን ስለ እድለኝነታቸው ደጋግመህ አታውራ። ታሪክ የሚፃፈው በእድልህ ሳይሆን በመረጥከው ምርጫ ነው። እድል ላይቀናህ ይችላል፣ የሚልቀው ምርጫህ ግን ሁሌም በእጅህ፣ ሁሌም በቅርብህ ነው። የያዝከውን ይዞ መቀመጥ ምርጫ ነው፤ ገና ለገና የሚመጣውን መጠባበቅ የአጋጣሚ ምርኮኛ፣ የእድል ተጧሪ መሆን ነው። ገና ለገና እንደሚፈጠር በሚታሰብ መላምት ህይወትህ ወደፊት ሊራመድ አይችልም። ምርጫህን በጊዜ ካልተጠቀምክ ኪሳራህ በየጊዜው እየጨመረ ይሔዳል።
አዎ! ገበሬ አምኖ ዘሩን ይዘራል፣ ፍሬውንም ያጭዳል። ያለመዝራትና መንግስት እንደሚረዳው የመጠበቅ ምርጫ ግን ነበረው። ይህ ግን የሚሆነው እድለኛ ከሆነ ብቻ ነው፤ ካልሆነ ግን እድሉን እያማረረ ለመኖር እራሱ ላይ መፍረዱ የግድ ነው። "እድሌ ጠማማ ነው፤ እኔ የነካውት ነገር አይበረክትም፤ እድለኛ አይደለሁም።" እያልክ እጅህን አጣጥፈህ የመቀመጥ ሙሉ ምርጫ አለህ፤ በዛው ልክ ጠማማውን እድልህን ለማቃናትም በድፍረት ወደ ተግባር የመግባት ምርጫ አለህ። እድልህን እርሳውና በምርጫህ ላይ ህይወትህን ገንባ፤ አጋጣሚዎችን መጠባበቅ አቁምና በውሳኔዎችህ አጋጣሚዎችን መፍጠር ጀምር። አብዝተህ ስለጠበከው የሚመጣው አጋጣሚ ሳይሆን ያንተ ብክነት እንደሆነ ተረዳ። በምጫህ ማንነትህን አስከብር፤ በውሳኔህ የወሳኝ አጋጣሚዎች ባለቤት ሁን።