ብርቱዎች ብቻ ይበረታሉ!
፨፨፨፨፨//////////፨፨፨፨፨
ጥሩ በሚባሉት ጊዜያት ማንኛውም ሰው ጥሩ ነው፤ በመልካሙ ጊዜ ብዙ ሰው ሰዎችን ለመርዳት አይቸገርም፣ እንዲሁም ጎበዝ ነው፤ ጠንካራ ነው፣ ማድረግ የሚፈልገውን ያደርጋል፣ በፈለገው ቦታ ይገኛል፣ የተመኘውን ያገኛል፣ የሃሳቡን ይሞላል፣ ውጥኑን ያሳካል፣ መርዳት ያለበትን ይረዳል። ነገር ግን ጊዜያትና ሁኔታዎች ሁሌም በጥሩነታቸው ላይቀጥሉ ይችላሉ። በእኛም ይሁን በሌሎች ምክንያት፣ መልካም የተባሉት ሁነቶች ወደ አስከፊና ወደማይመቹ አጋጣሚዎች ይቀየራሉ። ይህም ሁኔታ በሰዎች መሃል ትልቁን የህይወትና የማንነት ልዩነት ይፈጥራል። ወንፊት ስንዴውን ከእንክርዳዱ እንደሚለየው ሁሉ ይህም ወቅት ጠንካሮችንና ደካሞችን፣ ብርቱዎችንና ሰነፎችን የሚለይ ሁነኛ ወቀት ነው።
አዎ! ጀግናዬ..! ብርቱዎች ብቻ ይበረታሉ! መጥፎ በሚባሉት ጊዜያት ጠንካሮች ብቻ ይጎብዛሉ፤ አስከፊ በተባለ ጊዜ ብርቱዎች ብቻ ይበረታሉ፤ ጀግኖች ብቻ ይጀግናሉ፣ ይጋፈጣሉ፤ ይታገለሉ። ለጋሶች ብቻ ይለግሳሉ፤ መልካሞች ብቻ በጎ ያደርጋሉ፤ ቅኖች ብቻ ቀና ይሆናሉ። የእያንዳንዱ ሰው ጥንካሬ በማይቹ ሁነቶች ውስጥ የተመቻቸ ስፍራን በመፍጠር ይለካል። ፅናትህን የሚፈትን ትንሽ ነገር ሲገጥምህ ከተሰበርክ ምንም ከሌላው የሚለይህ ነገር የለም። እንደማንኛውም ሰው ፈተናዎች ሲመጡ ታቆማለህ፣ ወደ ኋላ ትመለሳለህ፤ እጅህን ትሰጣለህ፣ ትሰበራለህ፤ ትሸነፋለህ። ነገር ግን ከሽንፈትህ ማግስት ለአሸናፊነት እራስህን አዘጋጅ።
አዎ! ጥላቻህ ለብክነት ያጋልጥሃልና፤ ማድረግ ከምትችለው ይከለክልሃልና፤ አምኖ ከመቀበል ዘወትር በምሬት እንድትኖር ያደርግሃልና ደጋግ ጊዜያትን እንደምትወደው ሁሉ ክፉና መጥፎ ጊዜያትንም አምርረህ አትጥላ። በተመቻቸ ጊዜ ስታደርገው የነበረው ባልተመቸህ ሰዓት ለማድረግ ቀላል አለመሆኑ ግልፅ ነው። በብዙ የምትፈተነውም በዛን ሰዓት ነው።
ይብዛም ይነስም በሰውነቱ የችግርን ገፈት ያልቀመሰ፣ በፈተና ውስጥ ያላለፈ ሰው አይኖርም። አንተም የእኔ በምትለው መንገድ የሚመጥንህ ፈተናና ችግር ይገጥምሃልና እራስህን ይበልጥ አጠንክር፤ ሁሌም ነገሮችን እንዳመጣጣቸው ለመመለስ ተዘጋጅ። አንተን ብሎ መምጣቱ ስለሚያስፈልግህ ነውና "ለምን እኔን?" ለማለት አትቸኩል።