ከዓለም ተላቀቅ!
፨፨፨////////፨፨፨
መለየት ደስ ይላል፣ በታሪክ ውስጥ ማለፍ፣ የእራስን አሻራ ማሳረፍ፣ ሆነም ቀረም የሚያኮራን ተግባር መፈፀም የተለየ ስሜትን ይፈጥራል። ዓለም ሁሌም ስጋን መማረክ ትፈልጋለች፣ ምድር በየቀኑ የጥፋትን በር ከፍታ ትጠባበቃለች። ትኩረት በየሔድንበት ሁሉ በሚታደንበት ዓለም እየኖርን ትኩረትን ሰብስቦ፣ እራስን ገዝቶ፣ ምግባርን አስቀድሞ፣ በአምላክ እየተመሩ መኖር እጅግ ከባድ ነው። ህያዊት ነፍስ የተጠማችው መንፈሳዊውን ስራ እንጂ ምድራዊውን ፌሽታ አይደለም። ለነፍሳችሁ ስትታዘዙ የዓለም አብረቅራቂ ጊጣጌጥ ሁሉ የማይረባ ኮተት እንደሆነ ይገባችኋል። ነፍስ ምንምእንኳን በስጋ ብትጨቆንም የዘወትር ፍላጎቷና አምሮቷ ግን ለአምላኳ መገዛትና በህግጋቱ መመራት ብቻ ነው።
አዎ! ጀግናዬ..! ከዓለም ተላቀቅ፣ ገደብ ከሌለው ስጋዊ ፍቃድ እራስህን ጠብቅ፣ ሰዶ ማሳደድ ውስጥ አትግባ፣ ከዓለም ለማትረፍ አትሽቀዳደም፣ ክብርን ለማግኘት በጥፋት መንገድ አትጓዝ። የዓለም መድሃኒት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን አለ፦ "ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።" ለገንዘብ የሚገዛ እግዚአብሔርን ሊያከብር አይችልም፤ እግዚአብሔር አምላኩንም ያከበረ እንዲሁ በምድራዊ ንብረትና ዝና አይሰናከልም፣ ለእርሱም ብሎ እራሱን አያጣም፣ ነፍሱንም አያረክስም። የዓለምን ሃብት በሙሉ በእጅ ብታስገባና የእግዚአብሔርን ፍቅር ብታጣ ትርፍህ ምንድነው?
አዎ! ትርፍ ለሌለው ድካም እራስህን አታጋልጥ፣ ለማታርፍበት፣ ውስጥህን ለማታረጋጋበት፣ ሰላምህን ለማታረጋግጥበት ነገር ዋጋ ከመክፈል ተቆጠብ። እራስን መግዛት ተለማመድ ከዛም በላይ እራስህን ለእግዚአብሔር ለማስገዛት የምትፋጠን ሁን። በአምላኩ የሚታመን፣ ለፈጣሪው እራሱን የሰጠ፣ መንፈሱን ለጌታው ያስገዛ ሰው ሁሌም ህይወቱ የተረጋጋችና በሃሴት የተሞላች ነች። በዓላትን አስታኮ ስጋን ብቻ ለማስደሰት መሽቀዳደም፣ መንፈሳዊነትን ረስቶ በዓለም ዳንኪራ ለመሳተፍ መፋጠን፣ እድሜን ጨምሮ፣ ጤናን ሰጥቶ፣ ባርኮና ጠብቆ ለዚ ያደረሰን ፈጣሪ ዘንግቶ የስጋን ፍቃድ ብቻ ለመፈፀም መቻኮል አግባብ አይደለም። በደስታህም ሆነ በሃዘንህ ወቅት የፈጣሪህን አብሮነት አስብ። በደስታህ አመስግነው በሃዘንህም ተማፀነው። በምንም ሁኔታ ውስጥ ብትሆንም በቻልከው መጠን ለነፍስህ የሚበጃትን የአምላክህን ፍቃድ መጠበቅህን አንዳትዘናጋ።