ጨለማው አብቅቷል!
፨፨፨፨/////////፨፨፨፨
አዎ! ጠለማው አብቅቷል እናም ድጋሜ አይመለስም፣ አሳፋሪው ወቅት፣ አስፈሪው ጊዜ አልፏል እናም ድጋሜ አትመለከተውም። ከልክ በላይ ማሰብ፣ ለሚሆነውም ለማይሆነውም መጨነቅ፣ በየትኛውም ስፍራ አቀርቅሮ መጓዝ፣ ለከባዱ የህይወት አጋጣሚ አስቀድሞ መንበርከክ፣ ሰዎች ባስቀመጡት ክብ ደጋግሞ መመላለስ፣ በራስ አለመተማመን፣ በራስ ማፈር፣ እራስን ማሸማቀቅና ማጎሳቆል ሁሉ አብቅቷል። ለእራስህ የምትኖርበት ጊዜ መጥቷል፣ እራስህን የምታኮራበት፣ ከጨለማው አስተሳሰብ፣ ከውድቀት አቋም እራስህን ነፃ የምታወጣበት ጊዜ አሁን ነው። ብዙዎች ስለወደፊት ያወራሉ፣ ብዙዎች በትናንትናቸው ታስረዋል አንተ ግን ዛሬ አሁን የውሳኔ ሰው ሆነህ ተገኝ፣ ዛሬውኑ ህይወትህን ወደመቀየር ተሸጋገር። ለራስህ የገባሃቸው መሰረተ ቢስ ቃላቶች፣ የሚገባህን ህይወት መኖር ያልቻልክበት ጊዜ እንዲያበቃ አድርግ።
አዎ! ጀግናዬ..! ጨለማው አብቅቷል፣ የብረሃን መንገድ ተጀምሯል፤ የኋሊቱ ጉዞ ቆሟል ወደፊት መራመድ ጀምረሃል፤ በራስ ማዘን አብቅቷል በማንነት መኩራት ተጀምሯል። ማስመሳል፣ እራስን ማታለል፣ ለታይታ መኖር ለእይታ መመላለስ፣ እራስን በየአቅጣጫው ማድከም፣ ህይወትን ማክበድ ቀርቷል። ብዙዎች እውነታን መጋፈጥ ይፈራሉ፣ ብዙዎች ሪስክ መውሰድ ይፈራሉ፣ ብዙዎች በስንፍና ታስረዋል፣ በእምነት ማጣት በጥርጣሬያቸው እየተበዘበዙ ነው፣ ብዙዎች ከተግባር በራቀ ሃሳብ፣ እርምጃ ባልተወሰደበት ህልም፣ ከዛሬ ነገ ተንከባሎ በመጣ እቅድ በጭንቀት ይኖራሉ። ከብዙዎቹ አንዱ እንደሆንክ ከተሰማህ እርምጃ የምትወስደው እንደለመድከው በሃሳብ ወይም በእቅድ ወይም በወሬ ሳይሆን በተግባር እንደሆነ አስታውስ።
አዎ! ህይወት ለማን ቀላል ሆና ታውቃለች? ኑሮ ለማን አልጋባልጋ ሆኖ ያውቃል? ለማንም። ማንም ህይወቱን ወዶ ተመችቶት ለመኖር የግድ ማድረግ ያለበት ነገር ይኖራል። በተመሳሳይ የለውጥ አመለካከት፣ በተለመደው የህይወት መረዳት፣ በአንዳይነት የግል አቋም አንዳች የሚፈጠር ነገር የለም። የጨለማው ዘመን ያበቃ ዘንድ ህልምህን መሞከር ይኖርብሃል፣ ከቀደመው ችግር ለመውጣት አዲስ አደጋን መጋፈጥ የግድ ነው፣ ትናንትህን ለማደስ ዛሬ እንቅስቃሴ መጀመር ይጠበቅብሃል። ያለ ተግባር የሚገፈፍ ጨለማ፣ ያለጥረትም የሚመጣ ለውጥ የለም። የምርም ህይወትህን ከወደድከው ይበልጥ ትደሰትበት ዘንድ በምትፈልገው መንገድ መቀየር ይኖርብሃል። ቀስበቀስ ነገር ግን በእርግጥም ነገሮችን ትቀይራለህ፣ በሂደት ነገር ግን የምርም የምትመኘውን ህይወት መኖር ትጀምራለህ። በተስፋህ ተማመን በከባዱ መንገድም ህይወትህን አሻሽል።