በርታ በል!
፨፨////፨፨
መድሃኒት ቀማሚው ለመድሃኒትነት የሚያገለግሉትን ግብዓቶች ፍለጋ ወደ ጫካ ይገባል፤ አትክልቶችንም ያስሳል። አሰሳው መድሃኒት ለመቀመምና ታካሚውን ከህመሙ ለማዳን እንዲሁም ለማሳረፍ ነው። ጥረቱ ግን አልጋ በአልጋ አልነበረም፤ የሚያገኛቸው ቅጠሎች ሁሉ ለፈለገው መድሃኒት የሚሆኑ አልነበሩም ነገር ግን ትከክለኛውን ቅጠልና ሌሎች ግብዓቶችን ፍለጋ ማሰሱን አላቆመም። ጥረቱም መና እንዳይቀር፣ ታካሚውም እንዲፈወስ የሚጠበቅበትን ሁሉ ለማድረግ እራሱን በይበልጥ አዘጋጅቶ ጥረቱን ቀጥሏል። በእርሱ ድካም ታካሚው ቢያመልጠው ቁጪትና ፀፀቱ የህይወት ዘመን ቁስሉ ነው። ነገር ግን ስለበረታ የታካሚውን ህይወት መታደግ ቻለ። አንተም ሁሌም ደስተኛ ላትሆን ትችላለህ፣ ህይወት ፊቷን ልታዞርብህ እድልም ጀርባ ልትሰጥህ ትችላለች፣ ቀኑ ሰጨልምብህ ተስፋ ለመቁረጥ ልታቀርብህም ትችላለች። ነገር ግን ካደረካቸው በላይ ባላደረካቸው እየተቆጨህና እየታመምክ ከምትኖር አሁን በርታ በል። የምታየው ሁሉ የሚያነቃህ፣ የምትሰማው ሁሉ የሚያበረታታህ፣ የምትሰራው ሁሉ ለውጤት የሚያበቃህ ላይሆን ይችላል። አንተ በፈለከው ጉጉት ልክ ብዙዎች አይሳኩም፤ መንገድህ አይቀናም፤ ሃሳብህ አይሞላም። ካልጠነከርክ ግን ሁሉም ያበቃል።
አዎ! ጀግናዬ..! በርታ በል! በመኖርህ የምታዝን ሳትሆን ስላለህ ብቻ፣ አምላክህ ፊት በመቆምህ ብቻ ህያዊት ነፍስህን በተስፋ የምትሞላ ሁን። ጠንካራ ነህና ቀላል ነገር አይሰብርህም፤ ብርቱ ነህና በጥቃቅን ክፍተት ተስፋ አትቆርጥም። ከባዱ ሊሰብርህ ቢመጣም እንዳትበገር፤ እጅህን ለመስጠት አትፋጠን። ተስፋህ ውስጥ ገና ያልኖርከው፣ ያላጣጣምከው፣ ያልተነካ ሙሉ ህይወት አለ። በእራሰህ አዝነህ ተስፋ ስላጣህ ከምንም የከፋውን ምንም ሳታገኝ ምንም ታጣለህ፤ እራስህን ትጥላለህ፤ በእራስህ ትከፋለህ፤ መልካሟን የህይወት ገፅም ወደ ክፉ፣ አስደሳቿንም ወደ አሳዛኝ ትቀይራታለህ። ያለፈው ጊዜ ቢያሳምምህ፣ ቢያሰቃይህ፣ ቢያቆስልህም ከበረታህ ከአሁን ጀምሮ ያለው ጊዜ ግን ይጠግንሃል፤ ያክምሃል፤ ያሳርፍሃል።
አዎ! ደጋግመህ በእራስህ ከማዘን ተቆጠብ፤ በእራስህ ከመጨከን ተመለስ። የማይደክም፣ የማይዝል፣ የማይታመም ሰው የለም። ሲስቅ የምታየው ሁሉ የሚያለቅስበት ጊዜ ነበር፤ ሲደሰት የተመለከትከው ሁሉ በህይወት አጋጣሚ ለአሳዛኝ ክስተት የሚጋለጥበት ጊዜ ይኖረዋል። ኑሮ ስለከበደህ ህይወትህን እንደ እርግማን አትቁጠራት፤ ችግር ስለተደራረበብህ በብሶት አንገትህን አትድፋ። የጨለመችው ጀንበር ጎህ ለምትቀደው ብረሃን ቦታ የምትለቅበት ጊዜ ይመጣል፤ መቼም ጨልሞ አይቀርም። የምታምነው አምላክ ሁሌም ከጎንህ ነውና መቼም ብቻህን እንደሆንክ አይሰማህ። ከተሰባሪው ሰው በላይ በማይበገረው ፅኑ ድጋፍህ በሆነው በፈጣሪህ ተማመን። በምክንያት የሆኑት ሁሉ በምክንያት ያልፋሉ፤ ያስደመመህን ለውጥ በሰዎች ላይ እንዳየሀው አትቀርም፤ ከበረታህ፣ በተስፋ ከተሞላህ፣ ካመንክ፣ በእምነትህ ልክ ከጣርክ ያለጥርጥር ያንን ለውጥ በአንተም ህይወት ሲከሰት ትመለከተዋለህ።