Forward from: Semir Jemal
የሱንናው አንበሳ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ (ረሂመሁላህ) ለሱንና ብለው የታሰሩባቸው የእስራት እርከን:
"""""""""""""
የመጀመሪያው እስራት: በሀገረ ደማስቆ
በ693 ዓመተ ሂጅራ፣ አንድ ክሪስቲያን (ነሷራ) መልእክተኛውን (ﷺ) በመተቸቱና በመስደቡ...ይህን ተከትሎ ሸይኹ ምላሽ በመስጠታቸው ለተወሰነ ጊዜ ታስረዋል።
ሁለተኛው እስራት: በሀገረ ግብፅ ታስረዋል፣የዚህ እስራት ዋናው ምክንያት ደግሞ፣የአላህ ስሞችና ባህሪያት፣የዐርሽን ጉዳይ በተመለከተ እንዲሁም አላህ ወደ ቅርቢቷ ሰማይ ይወርዳል በሚሉ ነጥቦች ላይ ነበር ለእስር የዳረጋቸው። በዚህ በሁለተኛው እስራት በሀገረ ግብፅ፣አንድ አመት ከ-ስድሥት ወራት ያክል ታስረዋል።
ሶሥተኛው እስራት: ይሄኛውም እስር የተካሄደው እዛው በሀገረ ገብፅ ላይ ነበር፤ ምክንያቱም ከፍጡር እገዛን እንዲሁም ምልጃን መጠየቅ አይቻልም በማለታቸውና እንዲሁም "በኢብኑል ዐረቢ አስ-ሱፊ" ላይ ረድ በማድረጋቸው ለእስር ተዳርገዋል። ፕሮፓጋንዳ አስነስተው ያሳሰሯቸውም እራሳቸው ሱፊዮች ነበሩ።
አራተኛው እስራት: በዛው በሀገረ ግብፅ ከሶስተኛው እስራት ተራዝሞ ለሁለት ወራት ያክል ታስረዋል።
አምስተኛው እስራት: ይሄም የተከሰተው በሀገረ ግብፅ ከአራተኛው እስራት በኃላ ተራዝሞ፣ ልዩ ቦታው "አሌክሳንድሪያ" በተሰኘ ስፍራ ለ-7 ወር ከ-28 ቀናቶች ያክል በእስር አሳልፈዋል።
ስድስተኛው እስራት: ይሄኛው እስራት ደግሞ የተካሄደው በሀገረ ደማስቆ ልክ እንደ አምስተኛው እስራት ለ-7 ወር ከ-28 ቀናቶች ያክል በእስር አሳልፈዋል።
ሰባተኛው እስራት (የመጨረሻው እስራት): የመጨረሻው እስራት የተካሄደው በሀገረ ደማስቆ ነበር፤ምክንያቱም ቁብሪዮችን፣ ሙብተዲኦችን አበክረው በመቃወማቸው የተነሳ ነበር። ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ (ረሂመሁላህ) በዚህ በመጨረሻው እስራቸው ላይ ለእስር የተዳረጉት ሁለት አመታት ከ-ሶሥት ወር እና ከ አስራ አራት (14) ቀናት ያክል ነበር። ሸይኹ አላህ ይዘንላቸውና ሕይወታቸውም ያለፈው በዚሁ እስር በሀገረ ደማስቆ በ-20 ዙል-ቀዕዳ 728 በሂጅራው ቀመር አቆጣጠር ላይ ነበር።
✍ Shaykh Hassan As-Somali
📝 Translated by:Abu Hafsah
@semirEnglish

#Reference: Summarized from the book of al-Jāmi li-Sirah Shaykhul Islam Ibnu Taymiyah, P. 32-36
✍ Shaykh Hassan As-Somali
📝 Translated by:Abu Hafsah
@semirEnglish