ለታክስ አከፋፈል የሚቀርብ ዋስትና
ባለስልጣኑ የመንግስትን ገቢ ለመጠበቅ አስፈላጊ መስሎ ሲታየው አስፈላጊ ነው በሚለው መጠንና አኳኋን ታክስ ከፋዩ ዋስትና እንዲያቀርብ ሊያስገድደው ይችላል፡፡
ታክስ ከፋዩ ዋስትና እንዲያቀርብ የሚጠየቀውም፡-
1. የመክፈያ ጊዜው ለደረሰ ወይም የመክፈያ ጊዜው ለሚደርስ ታክስ መክፈያ፤ ወይም
2. በታክስ ሕግ መሰረት ተመላሽ ለሚጠይቅ ታክስ ከፋይ ቅድመ ሁኔታ ይሆናል፡፡
የሚሰጠው ዋስትና ባለስልጣኑ የሚጠይቃቸው ተገቢ ቅድመ ሁኔታዎች እንደተጠበቁ ሆነው በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ ዋስትና ሊሰጥ ይችላል፡፡
ታክስ ከፋዩ ዋስትና ማቅረብ ግዴታ የሚኖርበት ባለስልጣኑ፡-
1. የሚፈልገው የዋስትና መጠን፣
2. ዋስትናው የሚቀርብበት አኳኋን፣ እና
3. ዋስትናው የሚቀርብበትን ቀን የሚገልጽ የጽሑፍ ማስታወቂያ ለታክስ ከፋዩ የሰጠ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡
ታክስ ከፋዩ ያቀረበው የዋስትና መጠን የታክስ ከፋዩ ያልተከፈለ ታክስ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡