ከ25 ቢሊየን ብር በላይ የግብር ታክስ ጉዳት ተከሳሽ በ10 ዓመት ጽኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጣ
ሕዳር 30/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
ከ25 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ የግብር ታክስ ጉዳት አድርሷል ተብሎ ክስ የቀረበበት በረከት አለኸኝ በ10 ዓመት ጽኑ እስራትና በገንዘብ እንዲቀጣ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሙስና ወንጀል ችሎት ወሰነ።
በተለይም በመስከረም 24 ቀን 2011 ዓ.ም እና በመስከረም 22 ቀን 2012 ዓ.ም ፍቃድ በማሳደስ የተመዘገበዉ በአስመጪነት ንግድ ስራ ዘርፍ ሆኖ ሳለ ምንም አይነት እቃ ከዉጭ ሀገር ሳያስገባ እና የሀገር ዉስጥ የዕቃ ግዥ ሳይፈጽም ከወሰደው የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ደረሰኞችን በማተም ለ339 ግብር ከፋዮች 1 ሺህ 663 ደረሰኞችን በማሰራጨት በ15 የገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ላይ 25 ቢሊየን 989 ሚሊየን 943 ሺህ 223 ብር ከ83 ሳንቲም የታክስ ማጭበርበር ጉዳት አድርሷል በማለት ዐቃቤ ሕግ ክስ ማቅረቡ ይተወሳል።
ዐቃቤ ህግ ያቀረበው የክስ ዝርዝር ለተከሳሽ ከደረሰው በኋላ ግለሰቡ የወንጀል ድርጊቱን አለመፈጸሙን ጠቅሶ የዕምነት ክህደት ቃሉን በመስጠቱ ዐቃቤ ህግ 13 የሰው ምስክሮችን እና 23 ገላጭና አስረጂ የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቧል።
ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ ያቀረበውን የመከላከያ ማስረጃ መርምሮና ከዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ጋር አመዛዝኖ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት መፈጸሙን በማረጋገጡ ተከሳሽን ጥፋተኛ ብሎታል።
ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ ቅጣት አስተያየት መርምሮ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ተከሳሹ ያቀረበውን 5 የቅጣት ማቅለያ በመያዝ በእርከን 29 መሰረት በ10 ዓመት ጽኑ እስራት እና በ3 ሚሊየን 8 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ተወስኗል::
ምንጭ፡- ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን