ልዩ መለያ ኮድ (QR Cod) የተካተተበት የደረሰኝ ህትመት ጥያቄ የማቅረቢያ ቀነ ገደብ እስከ የካቲት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እንዲራዘም ተወሰነ
ጥር 30/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
ከዚህ ቀደም የደረሰኝ ህትመት ጥያቄ ማቅረብ የሚቻለው እስከ ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም ብቻ መሆኑ በተገለጸው መሰረት ቁጥራቸው 88,717 የሆኑ ግብር ከፋዮች የህትመት ጥያቄ ማቅረብ መቻላቸውን የገቢዎች ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሤ ከክልል እና ከተማ አስተዳደር የገቢ ዘርፍ አመራሮች ጋር በበይነ መረብ ባደረጉት ውይይት ገልጸዋል፡፡
ሆኖም በተለያዩ ምክንያቶች የህትመት ጥያቄያቸውን ያላቀረቡ ግብር ከፋዮች መኖራቸውና ይህን ታሳቢ በማድረግ የህትመት ጥያቄ ማቅረቢያ ቀነ ገደብ እስከ የካቲት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እንዲራዘም በውይይቱ ተወስኗል፡፡
እንደ ሀገር በገቢው ዘርፍ የሚሰተዋሉ ክፍተቶችን ለማረም በርካታ የሪፎርም ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ በውይይቱ የገለጹ ሲሆን በተለይም የማንዋል ደረሰኝ አጠቃቀም እና አስተዳደር ስርዓትን በማሻሻል የሚፈለገውን የገቢ ዕድገት ማስመዝገብ ያሰፈልጋል ብለዋል፡፡
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫ፡- https://shorturl.at/ZLOQR