ሸይጧንን አትርዱበት
****
በጠዋት ተነስቼ ከዛሬ ዓመት፣ ሁለት ዓመትና ከዚያም በላይ እዚሁ አካባቢ ባጠፉት ጥፋት ምክንያት ሲዘመትባቸው የነበሩ ሰዎችን እየቆጠርኩ ነው። የት ደርሰው ይሆን ብዬ ፈተሽኩ። ብዙዎቹ ይበልጥ ታዋቂ ሆነዋል፣ በተከታይ ከብረዋል።
እዚህ አካባቢ አንድ ሰው ሲያጠፋ የሚደረጉ ዘመቻዎች ብዙዎቹ የሚጠናቀቁት ሰውዬውን ገፍቶ ከበር በማስወጣት ነው፡፡ ያው የወከባ ሽኝት በሉት፡፡ ያለን ሰው ይበቃናል አታስፈልገንም ዓይነት መግፋት። ከዚያም ደቦ የወጣው ሰው ሁሉ ጉዳዩን ትቶ ወደቤቱ ይመለሳል፡፡ ሰውዬውንም አጀንዳውንም ይረሳል፡፡
ታዲያ የብዙ ዘመቻዎቻችንና ጩኸታችን ውጤት ሸኝቶ መመለስ ከሆነ፤ በዚህም የተሻለ ዲናዊ ትርፍ የማናገኝበት ከሆነ ለምንድነው በሚሻለው መልኩ ዲናችንን የማንጠቅመው የሚል ሀሳብ አለኝ፡፡ በኢስላም የአንድ ሰው መጉደል ቀላል እንዳይመስላችሁ፤ የብዙ ሰው መጉደል ነው፡፡
ሰውን ከአንድ እና ሁለት ጊዜ በላይ መምከርም ሆነ መውቀስ ማሠልቸት፣ ማስጠላትም ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ብዙ ሰው የሚሠራውን ጠንቅቆ ያውቃልና፡፡ አጥፊን ሰው ከመምከርና ከማሳየት በዘለለ በደቦ ፍርድ ይወገር ይሰቀል እያሉ ማሳደድ የበለጠ ሸይጧንን በርሱ ላይ መርዳት ነው የሚሆነው፡፡ እኛ ይወገር ብለን ብናባርረው ከነጥፋቱ ና እናስጠጋህ የሚል የጥፋት ጭፍራ አያጣም፡፡ ለዚህም ነው በግርግር፣ በርብርብ፣ በሥም ማጥፋት፣ በውግዘት፣ በሰበራ፣ በወቀጣ፣ በቅልጠማ … የበለጠ ጉዳት እንጂ የተሻለ ጥቅም አናገኝም እንረጋጋ ብዬ የምሞግተው።
ወዳጄ የዛሬ ሰው ብሶተኛ ነው መሠለኝ፣ እንኳንስ ወርደህበት እንዲሁ አልቅስ አልቅስ ይለዋል፡፡ ይበልጥ ለማጥፋት ሰበብ የሚፈልግ ነው ማለቴ ነው፡፡
ጥፋት ላይ ያለን ሰው የባሰ እንደያጠፋ ቀስ ብለህ ጠጋ ብለህ ትነግረዋለህ፣ ታርመዋለህ፣ ታባብለዋለህ እንጂ አትወርድበትም፡፡ አንዳንዴ ደግሞ ለሰው ማዘንም ተገቢ ነው፡፡ አንዳንድ የተጮኸባቸውንና ከመጠን በላይ ድንበር የታለፈባቸውን ሰዎች ሳይ ሶብራቸው ሁሉ ይገርመኛል፡፡ እንደው ግን ይህን ሁሉ አጥፍተዋል ግን እላለሁ፡፡ ከተጮኸም በልክ ይሁን እሺ፡፡
ሌላው ደግሞ አንድ ሰው ብቻ የሰማውን በሆነ ሚዲያ ላይ የሰማውን ወሬ እዚህ አምጥቶ ለሰፊው ጀማ ማስጣትም ሆነ ተብሎ አጥፊንና ጥፋቱን ከማስተዋወቅ አይተናነስም፡፡
ወዳጆቼ! የታየኝ የግድ ይታያችሁ ብዬ ድርቅ አልልም፡፡ ሀሳቤ ግን ይህን ይመስላል፡፡
ሶባሐል ኸይር
https://t.me/MuhammedSeidAbx