Posts filter


Forward from: Nejashi Printing Press
ሸዕባን 8
ማስታወሻ
****
ከረመዷን ወር በፊት መግቢያ በር ብቻ አይደለም ።

፨ ኸይር ከሚመረትበት የበለጠ ኸይር ወደሚመረትበት መሸጋገሪያ ድልድይ ነው።

፨ ከፊት ለፊታችን ትልቅ ወር እየመጣ እንደሆኑ ማብሰሪያ ፊሽካ የተዘጋጁ ደወል ነው።

፨ ከረመዷን በፊት በቀሩት ጥቂት ቀናት ነፍስን ማዘጋጃና መለማመጃ መድረክ ነው።

፨ ከብዙ ዝንጋቴ በኋላ ወደ አላህ የመመለሻ ወር ነው።

፨ ከኖርማልና ከተለመደው የዒባዳ ሁኔታችን ወጥተን ለተሻለ መታዘዝ መስፈንጠሪያ ቦርድ ነው።

ረመዷን ያለአንዳች መንፈሳዊ ዝግጅት ዝምተብሎ የሚገባበት ወር አይደለም ።

፨ ከማንኛውም ወር በበለጠ መልኩ ሸዕባን ውስጥ ረሱላችን ፆም ያበዙ ነበር።

፨ ይኸውም ነፍስ ጠርታ፣ ለስልሳ፣ ገርታ፣ በአላህ ፍራቻ ተሞልታ ረመዷንን እንድትቀበል ነው ብለዋል ዑለሞች።

፨ የረመዷንን ለዛና ጥፍጥና ማጣጣም የፈለገ ከወዲሁ ሸዕባን ላይ ነፍሱን በፆም፣ በቁርአን ፣ በዚክር፣ በሰደቃ፣ በመልካም ሥራ ያለስልስ።

፨ ሸዕባን ሥራዎች ወደ አላህ ከፍ የሚሉበት/ የሚቀርቡበት ወር ነው። ፆመኛ ሆናችሁ ሥራችሁ አላህ ይቀርብ ዘንድ አትወዱም ወይ?

፨ በውስጡ ኢስቲግፋር፣ ዱዓና ዚክር አብዙ፣ ቁርአን አብዝታችሁ ቅሩ፣ የበደላችሁትን ካሱ፣ ለበደላችሁ ይቅር በሉ፣ የወሰዳችሁት የሰው ሐቅ ካለ መልሱ።

አላህ ሆይ ፅናትን ለግን። ሸዕባንን ባርክልን። ለረመዷን ደርሰው፣ ፆመውት፣ ፆማቸውም ተቀባይነት ከሚያገኙት አድርገን።

https://t.me/NejashiPP


Video is unavailable for watching
Show in Telegram




ረመዷን ቁርአን በብዛት የሚቀራበት ወር ነው። ቁርአን ገዝቼ ለመስጊድ ወቅፍ ማድረግ እፈልጋለሁ የሚል ካለ በውስጥ ያናግረኝ አማናውን አድራሽ ነኝ።
ከታች ያለው ከአንድ መንደር የተላከልኝ የቁርአን አስገዛልን ጥሪ ነው።

https://t.me/MuhammedSeidAbx




ብዙ አትሳቁ እስቲ ይህ መንግሥት ኑሮ የተመቸን ይመስለውና ይናደዳል ።

https://t.me/MuhammedSeidAbx


ሻሸመኔና አካባቢው ያላችሁ ከዚያም ርቃችሁ የምትገኙ ሁሉ።

ይህች ሙሽሪት ☝️ ቆንጆ ቆንጆ ጂልባቦችንና ኒቃቦችን ታቀርብላችኋለች።
አጋሩላት።
እዘዟት።

በዚህ ቁጥርና የቴሌግራም አድራሻ

0986535321

@Muslimahe1


https://t.me/MuhammedSeidAbx




አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏህ።

ረመዳንን  በጂልባብና ኒቃበ ፏ ማለት ለምትፈልጉ order በመቀበል ላይ እንገኛለን። ይዘዙ። ምርጫችሁ ስላደረጋችሁንም እናመሰግናለን🥰

0986535321
@Muslimahe1

https://t.me/MuhammedSeidAbx


የሆነ የመረረ ቀን ደስ የማይላችሁ አስደንጋጭ መልስ ሊመለስላችሁ ይችላል ። በሰው ሞራል፣ በሰው ክብር ፣ በሰው ስሜት አትቀልዱ።

https://t.me/MuhammedSeidAbx


በተቀሩት ጥቂት የሸዕባን ቀናት ለረመዷን አዲስ መጅሊስ አያስፈልጋችሁም ወይ።

ማሠራት የምትፈልጉ በሩቅም በቅርብም እዘዙኝ ልታዘዛችሁ። ጥሩ ዕቃ ከጥሩ ዋጋ ጋር ።

ማሂር ዐረብያን መጅሊስ

ስልክ ፡
+251922487331

https://t.me/MuhammedSeidAbx


ዛሬም አልናደድም፣ ዛሬም አይገርመኝም ፣ ዛሬም ተስፋ አልቆርጥም፣ ዛሬም በአላህ ላይ ያለኝ እምነት ያው ነው፣ አልሐምዱ ሊላህ።
ከዚህ በላይ ደግሞ በዚህች እጅግ ፈተና በበዛባት ዓለም ውስጥ፣ ዱላና መከራዋን ችዬ፣ ሳላብድ፣ ጨርቄን ሳልጥል፣ ብቻዬን ሳላወራ ... በጤናማ አዕምሮ ቆሜ እየሄድኩ ነው።
እና ይሄ ስኬት አይደለም ወይ።


https://t.me/MuhammedSeidAbx


ፃፍ ቢባል ሰው ሁሉ ደራሲ እኮ ነው።
**
የሆነ ሰው፣ የሆነ ሰው የፃፈለትን ልኮልኝ። እስቲ እንዴት አያችሁት ....

***

ዛሬ ማለት ነው የሚያምር መነፈሻ ውስጥ ቸቀምጠን ጉልበትህ ላይ ትኝት ብዬ እስኪ ደስ ያለሽን አንድ አያ ቅሪልኝ ብለከኝ ያ-አዩሀለዚነ አመኑ እስተዒኑ ቢሶብሪ ወሶላህ ኢነሏሀ መዓ ሷቢሪን የሚለውን ሳነብ ....
እኔም በተራየ አንተም ቅራልኝ ስልህ ሳቢቁ ኢላ መግፊረቲን ሚረበኩም ወጀነቲን አርዱሃ ከአርዲ ሰማኢ ወል አርድ የሚለውን ስታነብ በደስታ ስፍከነከን በሀይ ይሁን በህልም ተደናብሬ ተነሳሁ ይሄው ከነጋ ጆሮዬ ላይ ድምጽህ እያቃጨለ ግማሽ ሰራየን አጠናቀቅኩ። ኢትዮ መምጣት ናፈቅኩ በርሬ ሌምጣ እንዴ ...


ሸይጧንን አትርዱበት
****
በጠዋት ተነስቼ ከዛሬ ዓመት፣ ሁለት ዓመትና ከዚያም በላይ እዚሁ አካባቢ ባጠፉት ጥፋት ምክንያት ሲዘመትባቸው የነበሩ ሰዎችን እየቆጠርኩ ነው። የት ደርሰው ይሆን ብዬ ፈተሽኩ። ብዙዎቹ ይበልጥ ታዋቂ ሆነዋል፣ በተከታይ ከብረዋል።

እዚህ አካባቢ አንድ ሰው ሲያጠፋ የሚደረጉ ዘመቻዎች ብዙዎቹ የሚጠናቀቁት ሰውዬውን ገፍቶ ከበር በማስወጣት ነው፡፡ ያው የወከባ ሽኝት በሉት፡፡ ያለን ሰው ይበቃናል አታስፈልገንም ዓይነት መግፋት። ከዚያም ደቦ የወጣው ሰው ሁሉ ጉዳዩን ትቶ ወደቤቱ ይመለሳል፡፡ ሰውዬውንም አጀንዳውንም ይረሳል፡፡

ታዲያ የብዙ ዘመቻዎቻችንና ጩኸታችን ውጤት ሸኝቶ መመለስ ከሆነ፤ በዚህም የተሻለ ዲናዊ ትርፍ የማናገኝበት ከሆነ ለምንድነው በሚሻለው መልኩ ዲናችንን የማንጠቅመው የሚል ሀሳብ አለኝ፡፡ በኢስላም የአንድ ሰው መጉደል ቀላል እንዳይመስላችሁ፤ የብዙ ሰው መጉደል ነው፡፡

ሰውን ከአንድ እና ሁለት ጊዜ በላይ መምከርም ሆነ መውቀስ ማሠልቸት፣ ማስጠላትም ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ብዙ ሰው የሚሠራውን ጠንቅቆ ያውቃልና፡፡ አጥፊን ሰው ከመምከርና ከማሳየት በዘለለ በደቦ ፍርድ ይወገር ይሰቀል እያሉ ማሳደድ የበለጠ ሸይጧንን በርሱ ላይ መርዳት ነው የሚሆነው፡፡ እኛ ይወገር ብለን ብናባርረው ከነጥፋቱ ና እናስጠጋህ የሚል የጥፋት ጭፍራ አያጣም፡፡ ለዚህም ነው በግርግር፣ በርብርብ፣ በሥም ማጥፋት፣ በውግዘት፣ በሰበራ፣ በወቀጣ፣ በቅልጠማ … የበለጠ ጉዳት እንጂ የተሻለ ጥቅም አናገኝም እንረጋጋ ብዬ የምሞግተው።
ወዳጄ የዛሬ ሰው ብሶተኛ ነው መሠለኝ፣ እንኳንስ ወርደህበት እንዲሁ አልቅስ አልቅስ ይለዋል፡፡ ይበልጥ ለማጥፋት ሰበብ የሚፈልግ ነው ማለቴ ነው፡፡
ጥፋት ላይ ያለን ሰው የባሰ እንደያጠፋ ቀስ ብለህ ጠጋ ብለህ ትነግረዋለህ፣ ታርመዋለህ፣ ታባብለዋለህ እንጂ አትወርድበትም፡፡ አንዳንዴ ደግሞ ለሰው ማዘንም ተገቢ ነው፡፡ አንዳንድ የተጮኸባቸውንና ከመጠን በላይ ድንበር የታለፈባቸውን ሰዎች ሳይ ሶብራቸው ሁሉ ይገርመኛል፡፡ እንደው ግን ይህን ሁሉ አጥፍተዋል ግን እላለሁ፡፡ ከተጮኸም በልክ ይሁን እሺ፡፡

ሌላው ደግሞ አንድ ሰው ብቻ የሰማውን በሆነ ሚዲያ ላይ የሰማውን ወሬ እዚህ አምጥቶ ለሰፊው ጀማ ማስጣትም ሆነ ተብሎ አጥፊንና ጥፋቱን ከማስተዋወቅ አይተናነስም፡፡

ወዳጆቼ! የታየኝ የግድ ይታያችሁ ብዬ ድርቅ አልልም፡፡ ሀሳቤ ግን ይህን ይመስላል፡፡

ሶባሐል ኸይር


https://t.me/MuhammedSeidAbx


አብዛኛው የፌስቡክ ተጠቃሚ ሙስሊሞች ይመስሉኛል አልኩት ለአንድ ወዳጄ ። ባለፈው በቤጃይ ውድድር ጊዜ ከስድስቱ አሸናፊዎች አምስቱ ሙስሊም መሆናቸውን ሳይ ግምቴን ነበር ያወራሁት ። በርግጥ ፌስቡክን ለመልካም ነገር ስንጠቀም ውጤቱም ደስ ይላል። እንዲያም ሆኖ ግን በዚህ አካባቢ የሚጠፋው ሳያሳስበኝ አልቀረም። ጭራሽ ልጁ ደግሞ ጨመረልኝ -

ቲክቶክ አካባቢም የሚበዙት የኛው ልጆች ናቸው።
ፊልም ቤትም፣ ኳስ ቤትም፣ ቲያትር ቤትም የኛው ልጆች የሚበዙ ይመስለኛል አለኝ።
ሃይስኩል፣ ዩኒቨርስቲ፣ ላይብረሪ፣ ቢሮ፣ ፖለቲካ አካባቢ ግን ብዙ የሉም ።
ወጣቶች የት እንዳሉ ካወቅን እንደ ማኅበረሰብ የት እንዳለን ማወቅ አይከብደንም።
እስቲ ውሎአችን የላቀ ይሁን፣
ጊዜአችን ዕድሜአችን ነውና ይበልጥ ለተሻለ ነገር እናውል፣
በትላልቅ ነገሮች ላይ ተሳትፎአችን ይጨምር፣
ሂማችን ከፍ ይበል። ሂማ ማለት ዓላማ ማለት ነው።

ሶባሐል ኸይር

https://t.me/MuhammedSeidAbx


መልካም ሪዝቅ
መልካም ውሎ
መልካም ሥራ
መልካም ቀደር

ተወፍቃችሁ ዋሉ ወዳጆቼ።

https://t.me/MuhammedSeidAbx


Forward from: Nejashi Printing Press
የሸዕባን ዝግጅት
****

አነስ ረዐ እንዳሉት " የሸዕባን ወር ሲገባ ሙስሊሞች ቁርአን ላይ ተደፍተው ያነባሉ። ደካሞችና ድሆች በረመዷን ፆም ላይ ይበረቱ ዘንድ ዘካቸውን ያወጣሉ።"

ኢማም ኢብኑ ረጀብ እንዳሉት ሸዕባን የረመዷን መግቢያ ነው። ፆምም ሆነ ቁርአን መቅራት በረመዷን ውስጥ የሚወደዱ ተግባራት ሁሉ በሱ ውስጥም ይወደዳሉ። ነፍስ የረመዷን ዒባዳ እንዳይከብዳት ከወዲሁ መዘጋጀት ማለማመድና ማለስለስ ያስፈልጋል ።

የአላህ መልዕክተኛ ሰ.ዐ.ወ.
" ሸዕባን ብዙ ሰዎች የሚዘናጉበት በረጀብ እና በረመዷን መካከል የሚገኝ ወር ነው። በዚህ ወር ውስጥ ሥራዎች ወደ ዓለማት ጌታ ይቀርባሉ ። ፆመኛ ሆኜ ሥራዬ እንዲቀርብ እወዳለሁ ።"

ዓኢሻ (ረ.ዐ.)
" ከሸዕባን የበለጠ የትኛውንም ወር በብዛት ሲፆሙ አይቼ አላውቅም ።" ብላለች።

ደጋጎች ሸዕባንን የቁርአን ወዳጆች ወር ይሉ ነበር። በብዛትም ያነቡታል።

አላህ ሆይ ሸዕባንን ባርክልን። ረመዷንን ደርሰው ፆመው፣ በፆማቸውም ተቀባይነት ከሚያገኙት አድርገን።

https://t.me/NejashiPP


አንድ ሰው በዚህች ምድር ላይ ሲኖር ሞዴሌ ብሎ የሚይዘው ሰው ይኖራል፡፡ የኔ ሞዴል ረሱሉ ሰልለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ናቸው፡፡ ከዚያ በታች ደጋግ የአላህ ሰዎች ይኖራሉ፡፡ ከዚያም በዘመንህ ያለን ሰው ቀልብህ ወዶ፣ ስሜትህ ፈቅዶ፣ መንፈስህ አፍቅሮት ልትከተለው ትችላለህ፡፡

እኔ ወድጄ የምከተላቸው፣ አዘውትሬ የምሰማቸው ባሮቹ… ለጊዜያቸው በእጅጉ የሚሳሱ፣ በሁኔታቸው ሁሉ ቁጥብ የሆኑ፣ በትርፍ ነገር የማይደክሙ፣ ትርፍ ንግግር የማይናገሩ፣ ከትርፍ ክርክር የራቁ፣ ትርፍ መቀማመጥ የማይቀመጡ፣ በራሣቸው ጉዳይ ቢዚ የሆኑ፣ ጠፋሁ ጠፋሁ እያሉ የሚሰጉ፣ ነፍሲ ነፍሲ ማለትን የሚያወትሩ፣ ስለ ሰው ጉዳይ የማያነሱ፣ ቢነሳባቸውም እባክህን ወዲያልኝ የሚሉ ናቸው፡፡

ራሣቸውን ማንሳት፣ ራሣቸውን ማብቃት፣ ራሣቸውን ማሻሻል፣ ራሣቸውን ማሳደግ፣ ራሣቸውን ከፍ ማድረግ ነው ሁሌም ሀሳባቸው፡፡ በዚህ በኩል በራሣቸው ላይ ይሠራሉ፡፡ በዚያ ደግሞ ስለ ኡማው ይጨነቃሉ፡፡ የራሣቸውን አሻራ ይጥላሉ፡፡ ቁጭብለው አይረፍድባቸውም፣ ያለ አስተዋጽኦ አይመሽባቸውም፡፡

አንድ ቀን እንዲህ አሉኝ፡- ሰው በራሱ ላይ ሳይሠራ ሰውን መሥራት አይችልም፡፡ ራሱን ሳያስተካክል ሌላውን አያስተካክልም፡፡ አንተ ከተስተካከልክ መምከርም መናገርም ላይጠበቅብህ ሁሉ ይችላል፡፡ ምክንያቱም ተግባርህ ከቃል በላይ ተናጋሪና ተጣሪ ነውና፡፡

ሶበሓል ኸይር

https://t.me/MuhammedSeidAbx


አንዳንዴ እኮ አንዳንድ ጊዜ ሐጃዎችንን፣ ችግሮቻችንን፣ ድካሞቻችንን፣ ህመሞቻችንን ... ሌላው ቀርቶ ደስታዎቻችን ጭምር የማንናገርበት ጊዜ አለ።

ወዳጆቻችን ሆይ ደብቀን ወይም ለናንተ ቦታ አጥተን ሳይሆን እናንተኑ ላለማስቸገር ብለን ነው። እንዴት ሳይነግረን፣ እንዴት ሳንሰማ፣ እንዴት ሳይጠራን፣ እንዴት ሳናውቅ ... ብላችሁ ብትወቅሱ በርግጥ እውነት አላችሁ ። በዚያው ግን መልካም ጠርጥሩ።

ዱንያ የብዙዎችን ዐቅል ይዛለች። ብዙዎችን በውክቢያ ዓለም ውስጥ ከታለች። ለሐዘኑም፣ ለሰርጉም፣ ለዐቂቃውም፣ ለምርቃቱም፣ ለማግባቱም፣ ለህመሙም፣ ለችግሩም ... ሰውን ማስቸገር ደግም አይደል የሚል ሀሳብ አለን።

በረካ ሁኑልን።

መሳአል ኸይር

https://t.me/MuhammedSeidAbx


Video is unavailable for watching
Show in Telegram

20 last posts shown.