በአርቲስቶች የተጥለቀለቀው የፌዴሬሽኑ ምርጫ
አርቲስት ማስተዋል ወንደሰን የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌደሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ሆና ተመርጣለች
የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ የፕሬዝዳንትና ስራ አስፈፃሚ ምርጫ አካሂዷል።
ኢ/ር ሃይለእየሱስ ፍስሀ የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት ሆነው ሲመረጡ፤ አርቲስት ማስተዋል ወንደሰን የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌደሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ሆና ተመርጣለች።
ፌዴሬሽን አመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በጊዮን ሆቴል ሲያካሂድ ለቀጣይ አራት አመታት የሚመሩትን ፕሬዝዳንትና ስራ አስፈፃሚዎችንም መርጧል።
አንጋፋዋ አርቲስት ሀረገወይን አሰፋ ፣አቶ ሲሳይ ዳኜ ፣ደ/ር ወገኔ ዋልተንጉስ ፣አቶ ኢሳያስ ታፈሰ ፣አቶ ሸሀመለ በቀለ፣አቶ በለጠ ወልዴ፣ ወ/ሮ አሰፋሽን ስራ አስፈፃሚ ውስጥ ተካተዋል።
ፌዴሬሽኑ አለብኝ የሚለውን የገንዘብ እጥረት ለመቅረፍ አርቲስቶችን ወደ ስራ አስፈፃሚ በማምጣት የማርኬቲንግ ስራዎችን ለመስራት እንዳሰበ ለማወቅ ተችሏል።
ቀደም ተብሎ በፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ላይ አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ ፕሬዚዳንት እንዲሆን ግብዣ ቀርቦለት ሳይቀበለው እንደቀረም ከታማኝ ምንጭ ለመረዳት ተችሏል።
በቀጣይ ተመራጮችን በባላገሩ ሜዳ ፕሮግራም ላይ ይዘን እንቀርባለን።
Via:- ባላገሩ ስፖርት