ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ተስማሙ
ኤርዶጋን ማምሻውን በኤክስ ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በአንካራ ለሰዓታት የቆየ ውይይቶችን ማድረጋቸውን ተከትሎ፤ በሀገራቸው አደራዳሪነት "ከ8 ወራት በፊት የተጀመረ የአንካራ ሂደት ዛሬ አመሻሽ ላይ ትልቅ ደረጃ ላይ ደርሷል" ብለዋል።
"የሁለቱን ሀገራት ሉዓላዊነት፣ አንድነት እና የግዛት አንድነትን ለማረጋገጥ ያለመ በመርህ ላይ የተመሰረተ ስምምነት ላይ መደረሱንም ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጋራ መግለጫው ላይ፤ የኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት ጉዳይ ከህልውናዋ ጋር የተያያዘ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ "የዛሬው ውይይት ወደ ጓደኝነት መልሶናል" ሲሉ ተናግረዋል።
የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ በበኩላቸው፤ ስምምነቱ የሁለቱን ሀገራት መካከል የነበረውን "ልዩነት ያስቆመ ነው" ብለዋል።
ቱርክ ከፈረንጆቹ ሀምሌ ወር ጀምሮ ሁለቱን ወገኖች በማደራደር ልዩነቶቻቸውን ለመፍታት ያለመ ውይይቶችን እየመራች ቢሆንም፣ በአንካራ ቀደም ብለው የተካሄዱት ሁለት ድርድሮች ምንም አይነት ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ሳይችሉ መቅረታቸው ተገልጿል።
ነገር ግን በዚህ ሦስተኛ ዙር ድርድር ሁለቱ ሀገራት መካከል ከስምምነት መደረሱ የተገለጸ ሲሆን፤ ይህንንም ስምምነት ለማስፈጸም ይረዳ ዘንድ የስምምነት ሰነድ ተዘጋጅቷል።
በዚህ ሰነድ ላይም ኢትዮጵያ በሶማሊያ የባሕር ዳርቻ በኩል ዘላቂ እና ደኅንነቱ የተጠበቀ የወደብ አማራጭ በምታገኝበት አማራጭ ላይ የቴክኒክ ውይይቶችን ለመጀመር ሁለቱ ሀገራት መስማማታቸው ተገልጿል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ አስተማማኝ፣ ደህንነቱ የተጠበቀና እና ቀጣይነት ያለው የባህር በር መዳረሻ ተጠቃሚነት እንዲኖራት ስምምነት ላይ የተደረሰ ሲሆን፤ ይህም በሶማሊያ መንግሥት ስልጣን ሥር የሚተገበር መሆኑ ተገልጿል።