ጌታቸው ረዳ ገና አሁን ስራ ጀመረ‼️
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
በጌታቸው ረዳ የሚመራው የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ጊዜያዊ ምክር ቤት አቋቋመ‼️
የትግራይ ህዝብ ጥቅም የሚረጋገጠው በሰላማዊ ትግልና ውይይት እንጂ በጦርነትና የጦርነት ጉሰማ አይደለም ብሎ የሚያምነው በጌታቸው ረዳ የሚመራው የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ እስከ ቀጣዩ 14ኛው መደበኛ ጉባኤ ድረስ አመራር የሚሰጥ ጊዜያዊ ምክር ቤት አቋቋመ። የምክር ቤቱ አባላት ሁሉም ከኃላቀሩና ወንጀለኛው ቡድን ጎን አንሰለፍም ያሉት የህወሓት ማ/ኮሚቴ አባላትና የሁሉም ዞኖች አስተባባሪዎች፣ የክልል ስታፍ፣ የትእምትና የትግራይ ዩኒቨርስቲዎችን ያካተተ ነው። ምክር ቤቱ በጊዜያዊነት እንዲመሩት ሊቀ መንበርና ምክትሉን የሰየመ ሲሆን ከአባላቱም መካከል 7 አባላት የያዘ ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አቋቁሟል። አስተባባሪ ኮሚቴው ሊቀ መንበርና ም/ሊቀ መንበር የተሰየመለት ሲሆን የአባላቶቻችን ክትትል ስራ የሚከውኑ ዘርፎችም በግልፅ ተቀምጠዋል።
በተጨማሪም በዞን ሊቃነመናብርት የሚመሩ የዞን ኮሚቴዎችና የወቅቱ ትግላችንን ለማሳለጥ የሚያስችሉ ልዩ አደረጃጀቶችም እንዲቋቋሙ ተወስኗል። በወረዳዎችና ቀበሌዎችም በተመሳሳይ መልኩ እንዲፈፀም አቅጣጫ ያስቀመጠ ሲሆን የ3 ወራት ዕቅድም አፅድቋል።
04 ታህሳስ 2017 ዓ.ም