አቶ ሰርፀ ፍሬስብሀት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በፃፉት ደብዳቤ ከስራቸው ተሰናበቱ
(መሠረት ሚድያ)- የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የባህል፣ ኪነጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ የኪነጥበብ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሀላፊ ሆነው ላለፉት ስድስት አመታት ያገለገሉትን አቶ ሰርፀ ፍሬስብሀትን ከስራቸው ማሰናበታቸውን መሠረት ሚድያ የደረሰው መረጃ ያሳያል።
አቶ ሰርፀ ከስራቸው የተነሱት በከንቲባዋ ህዳር 23/2017 ዓ/ም በተፃፈ ደብዳቤ ሲሆን ምክንያቱ ግን በደብዳቤ ላይ አልተገለፀም።
ይሁንና ሚድያችን ከውስጥ አዋቂዎች የደረሰው ተከታታይ ጥቆማ እንደሚያሳየው ጉዳዩ በከተማ አስተዳደሩ ሊደረግ ከታሰበው የሰራተኛ ቅነሳ ጋር የተያያዘ ነው።
በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ባህልና ቱሪዝም ስር በሚገኙት 4 ቴአትር ቤቶች ማለትም የአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ፣ አገር ፍቅር፣ ራስ ቴአትር እና ሕጻናትና ወጣቶች ቴአትር በስራቸው 800 ሰራተኞች አሉ።
ከእነዚህ ሰራተኞች 50 ከመቶው እንዲቀነሱ እንደተወሰነ የደረሰን መረጃ የሚጠቁም ሲሆን በምትካቸው ማለትም 50 ከመቶ የሚሆኑ ከተለያዩ የክልል አካባቢዎች በመጡ ሰዎች በቴአትር ቤቶቹ ምደባ ተከናውኗል ተብሏል።
ይህን ውሳኔ ያልተቀበሉ ላይ ወይም ተቃውሞ ያሰሙ ሰዎች ላይ ከስራ የማንሳት እርምጃ እየተወሰደ እንደሆነ የታወቀ ሲሆን የአቶ ሰርፀ ጉዳይም ከዚህ ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል።
ሚድያችን ከሰሞኑ በተደጋጋሚ በሰራዎች ዘገባዎቹ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የመንግስት ሰራተኞች በቅርቡ ከስራ ሊቀነሱ እንደሆነ መዘገቡ ይታወሳል።
መረጃን ከመሠረት!