የእስራኤልና ሀማስ የተኩስ ቀቁም ስምምነት
እስራኤልና ሀማስ ተኩስ ለማቆምና ታጋቾችን ለመልቀቅ መስማማታቸው የጦርነቱ ሰለባ ለነበሩት ፍልስጤማውያንንና እስራኤላውያን የመጀመሪያው የሰላም ተስፋ ምልክት ተደርጎ ተወስዷል። ለወራት በኳታር ግብጽ እና USA ሸምጋይነት የተሳካው ይኽው ስምምነት የእስራኤል ኃይሎች ቀስ በቀስ ከጋዛ ሰርጥ የሚወጡበትን የ6 ሳምንታት የመነሻ የተኩስ አቁም አካቷል። በዚህ ጊዜ ውስጥ ሀማስ ከያዛቸው ወደ 100 ከሚደርሱ ታጋቾች 33ቱ ሲለቀቁ በምትኩ እስራኤል ደግሞ ፍልስጤማውያን እስረኞችን ትፈታለች። የኳታር ጠ/ ሚ ሼክ መሀመድ ቢን አብዱልራህማን አል ታኒ ትናንት እንደተናገሩት ተኩስ አቁሙ ተግባራዊ የሚሆነው ከፊታችን እሁድ ጀምሮ ነው። ከሸምጋዮቹ አንዷ የሆነችው የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ስምምነቱ የጋዛውን ጦርነት ለማስቆም ፣ለሲቪል ፍልስጤማውያን እጅግ አስፈላጊ የሆነውን እርዳታ በብዛት ለማስገባት እና ከ15 ወራት በላይ የታገቱት ሰዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲገናኙ ለማድረግ እንደሚያስችል ተናግረዋል። እስራኤል ስምምነቱን በይፋ የምትቀበለው የሀገሪቱ የጸጥታ ካቢኔ እና መንግሥት ዛሬ በሚሰጡት ድምጽ ካጸደቁት በኋላ ነው። ምንም እንኳን በጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ነታንያሁ መንግስት ውስጥ ያሉት አክራሪዎቹ ቢቃወሙ ስምምነቱ ዛሬ ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተዘግቧል።
የሁለቱም አካባቢዎች ህዝብ በስምምነቱ የተሰማውን ደስታ ገልጾ ሳያበቃ ስምምነቱ ይፋ በተደረገ በሰዓታት ውስጥ የእስራኤል ጦር ኃይል ትናንት በጋዛ ጥቃት መፈጸሙን ነዋሪዎችና ባለሥልጣናት ተናግረዋል። እስራኤል እንዳለችው ደግሞ የጋዛ ሚሊሽያዎች ዛሬ ወደ እስራኤል ሮኬቶች ተኩሰዋል። የእስራኤል ሀማስ ስምምነት ለሁለቱ ወገኖች ሰላም ተስፋ ፈንጣቂ ቢባልም ጦርነቱ ሙሉ በሙሉ እንዲያበቃ ማድረጉ ግልጽ አይደለም።