በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሰዎች ለቅሶ እና ገበያ ሲሔዱ ጭምር እየታገቱ እንደሚገኙ ነዋሪዎች ተናገሩ
ከአንድ ሳምንት በፊት ከደብረልባኖስ አከባቢ ወደ ያያ ጉሌሌ ለገቢያ ሲጓዙ የነበሩ አንድ ተሽከርካሪ ሙሉ 50 ሰዎች ግድም የሚሆኑ ነጋዴዎች ሳዲኒ ብዮ በሚባል የያያ ጉሉለ ወረዳ ታፍነው እንደተወሰዱ እስካሁን አለመመለሳቸውን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
በተለያዩ ጊዜያት አደባባይ ወጥተው ተፋላሚዎች ሰላም እንዲያወርዱ በአከባቢቸው ህዝቡ መማጸኑን የሚስታውሱት ነዋሪ አሁን ላይ ያ ሁሉ ተማጽኖ መና ቀርቶ አስገድዶ ስወራ እና እገታዎች በታጠቁ አካላት ስለሚፈጸሙ የአከባቢው ነዋሪዎች ገቢያ እና ለቅሰው ለመውጣት የሚሰጉበት አስቸጋሪ ያሉት ሁኔታ መፈጠሩን አስረድተዋል፡፡
“ታጣቂዎች በየቦታው ሰው ይወስዳሉ” የሚሉት አስተያየት ሰጪዋ በተለይም ሰው ገቢያም ሆነ ለቅሶ እንኳ ለመሄድ ስጋት እንደሚገባው አስረድተዋል፡፡
አንድ የአከባቢው ነዋሪ በዚህን ወቅት ከከተማ በመራቅ መንቀሳቀሱ ስጋት እንደሚፈጥር አስረድተው ማህበረሰቡ እለት በእለት ስጋት ወሮት እንደሚኖርም መግለጻቸውን የጀርመን ድምጽ አስደምጧል።
“በገጠር እውነት ለመናገር እንጀራ እንኳ መሶቡ ውስጥ የሚያድርለት ሰው ማግኘት ይከብዳል፤ የትኛውም ጉልበተኛ ይገባል በልቶ ይወጣል፤ ጋግሮ ልጆቹን እንዳይመግብ ሌማቱን ገልብጦ ባዶ የሚያስቀረው አካል ስላለ ይህን ሁሉ ስቃይ ህዝቡ የሚናገርበት መድረክም ሆነ ቦታ የለውም” ሲሉ ሌላኛው አስተያየት ሰጪ መናገራቸውንም ዘገባው አካቷል።
በመንግስት የጸጥታ ሃይልም ሆነ በአከባቢው በሚንቀሳቀሱ ታጣቂው ሃይሎች ስልክ ስለሚለቀም ስልክ ይዞ የሚንቀሳቀስ ሰው በገጠር አይገኝም ያሉት አስተያየት ሰጪው መረጃ እንኳ መለዋወጥ አዳጋች ሆኖ ህዝቡ ከዚህ በፊት ሲኖር ከነበረው ሃምሳ ኣመት ወደ ኋላ ተመልሶ እየኖረ ነው ብለዋል፡፡