(ዘ-ሐበሻ ዜና) የትግራይ ሰራዊት(ቲዲኤፍ) አመራሮች ከመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አደረጉ፡፡ የህወሀት ዋና ፅህፈት ቤት በሚገኝበት ሰማእታት ሀውልት አዳራሽ በተደረገው በዚህ ውይይት ላይ ከፍተኛ የሰራዊቱ አዛዦች መገኘታቸው ተገልጿል፡፡ የሰራዊቱን አዛዦች በመወከል መድረኩን የመሩት ጄኔራል ዮሀንስ ወልደጊዮርጊው ወይንም መዲድ ናቸው፡፡
በስብሰባው ላይ ከሁሉም መቀሌ ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ወጣቶች የተገኙ ሲሆን የሚሰማቸውን ጥያቄዎች አቅርበው መልስ ተሰጥቷቸዋል፡፡ የዛሬው ውይይት ሊካሄድ የነበረው ሮብ እለት ቢሆንም የሰራዊቱ አዛዦች ባለመገኘታቸው ለዛሬ መቀጠሩ ይታወቃል፡፡ የዛሬውን ውይይት ለየት የሚያደርገው የሰራዊቱ አዛዦች መገኘታቸው ብቻም ሳይሆን በስብሰባው መክፈቻ ላይ የተገኙት የክልሉ ሚዲያዎች ልክ ስብሰባው ሲጀመር እንዲወጡ መደረጋቸው ነው፡፡
በመክፈቻው ወቅት ፎቶ ግራፍ ማንሳት የተፈቀደላቸው ጋዜጠኞቹ ሙሉ ውይይቱን እንዳያዳምጡ ከአዳራሹ መባረራቸውን ከስፍራው የተሰራጩ መረጃዎች አስረድተዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ትላንት የከተማውን ወጣቶች ማነጋገራቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡
🔴 በስብሰው ላይ ጄነራሉ ስላነሷቸውና ሌሎችም ተጨማሪ ጉዳዮች አሁን የተለቀቀው መረጃችንን ከዩቱብ ገጻችን ይመልከቱ።