ሉሲ ወይም ድንቅ ነሽ እና ሰላም የተባሉት ዕድሜ ጠገቦቹ የሰው ልጆች ቅሪተ አካላት በቼክ ሪፐብሊክ ብሔራዊ ሙዚዬም ለዕይታ ሊቀርቡ መሆኑን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ሉሲ እና ሰላም ከፈረንጆቹ ነሐሴ 25 ቀን 2025 ጀምሮ ነው የባህል ማዕከል በሆነችው የቼክ ሪፐብሊክ መዲና ፕራግ ለተመልካች ክፍት የሚሆኑት፡፡
“የሰው ልጅ አመጣጥና ቅሪተ አካል” በሚል መሪ ቃል የሚከፈተው ይህ አውደ ርዕይ ለጎብኚዎችና ተመራማሪዎች ልዩ አጋጣሚ እንደሚፈጥር የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ጉዳዩን አስመልክተው በፕራግ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።
ከዚህ ባለፈም ኢትዮጵያ ለምን “ምድረ ቀደምት” እንደተባለች ለጎብኚዎች የተሻለ ግንዛቤ መፍጠር ያስችላል ነው ያሉት፡፡
አውደ ርዕዩ ሉሲ በአፋር ክልል ሃዳር በተባለ ቦታ የተገኘችበትን 50ኛ ዓመት ተከትሎ የሚዘጋጅ ሲሆን÷ለሁለት ወራት እንደሚቆይ ተመላክቷል፡፡
ይህ ታሪካዊ ሁነት የኢትዮጵያ እና ቼክ ሪፐብሊክን የሁለትዮሽ ግንኙነት ወደ አዲስ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለማሸጋገር የተደረሰው ስምምነት አካል መሆኑን ሚኒስትሯ ጠቁመዋል፡፡
አውደ ርዕዩ ከሳይንሳዊ ሁነትነቱ ባሻገር የኢትዮጵያን የበለጸገ ታሪክ፣ ባህላዊ ሃብቶችና አስደናቂ መልክዓ ምድሮች ለማስተዋወቅና ከመላው አውሮፓ የሚመጡ ጎብኚዎችን በመጋበዝ የሰው ልጅ መገኛ ምድረ ቀደምትነቷን ለማስረዳት እድል ይፈጥራል ተብሏል።