የሴራሊዮን ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት እና የጊኒ ጠቅላይ ሚኒስትር የመከላከያ ተቋማትን ጎበኙ።
የሴራሊዮን ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ጁሊየስ ማዳ እና የጊኒ ጠቅላይ ሚኒስትር አማዶ ኡሪ ባህ የኢፌዴሪ አየር ሀይልን እና የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽንን ጎብኝተዋል። የሁለቱም ሀገራት መሪዎች በጉብኝቱ ሥለተደረገላቸው አቀባበል እና ገለፃ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንት ጁሊየስ ማዳ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ እንደመሆኗ መጠን በዛሬው ጉብኝትም ይህንን ክብር የሚመጥን ተግባራት እያከናወነች መሆኑን ለማረጋገጥ ችለናል በጋራ በመስራታችንም ኩራት ይሰማናል ብለዋል።
የኢፊዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ አየር ሃይልም ሆነ የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለተቋሙ አባል ብቻ ሳይሆን ለመላው ኢትዮጵያዊም ጭምር አኩሪ ተግባር የሚያከናውኑ የኩራት ምንጭ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ተቋማቱ ለጎረቤት ሀገራት በራቸውን ክፍት አድርገው እየሰሩ መሆናቸውን ያስረዱት ሚኒስትሯ በሁለትዮሽ ግንኙነታቸው ደስተኞች መሆናቸውን ጎብኝዎቹ እና ሌሎችም ጎረቤት ሀገራት እየነገሯቸው መሆናቸውን ገልፀዋል።
የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ሉአላዊነት በማስጠበቅ በከተማ ግብርና በምግብ ራስን ለመቻል እና በፀጥታው ዘርፍም ኢትዮጵያ የራሷን እና የጎረቤት ሀገራትን ሰላም ለማስፈን ጠንክራ አየሰራች መሆኗን ኢንጂነር አይሻ አስረድተዋል።
በጉብኝቱ የኢፌዴሪ አየር ሀይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ እና የግብርና ሚኒስትሩ ዶክተር ግርማ አመንቴን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።