ወቅታዊ ጥያቄያችሁን ሰምተናል ፤ ከሚመለከተው አካል ምላሽ ይሰጥበታል " - የትግራይ የፀጥታ አካላት ከፍተኛ አመራሮች
ከመቐለ እና አከባቢዋ በተለያዩ አቅጣጫዎች የተሰባሰቡ በሺህ የሚሆኑ ወጣቶች የሚበዙባቸው ሰልፈኞች ዛሬ ከጥዋቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ ወደ ከተማዋ የከንቲባ አስተዳደር ፅህፈት ቤት ተሰባስበው ነበር።
የአስተዳደሩ ዋና በሮችና ዙሪያው የሚጠብቁ በርካታ ቁጥር ያላቸው ፓሊሶች በአከባቢው የነበሩ ሲሆን በባነር የተፃፉ መፈክሮች በመያዝና ድምፅ በማሰማት ወደ አስተዳደሩ ህንፃ በተለያዩ አቅጣጫ የተመሙ ሰልፈኞች አንድ ላይ አንዳይሰባሰቡ አድርገዋቸዋል።
በአንዱ አቅጣጫ የመጡ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰልፈኞች ከከንቲባው ህንፃ ዋና በር በቅርብ ርቀት በመሆን ፦
- ጊዚያዊ አስተዳደሩ አይፈርስም !
- በመንግስት ላይ እምቢታ ያወጁ ሃይሎች ላይ እርምጃ ይወሰድ !
- መንደርተኝነት እና ኋላቀርነት ይወገድ !
- ከፓርቲ መንግስት ይቀድማል !
- መንግስት ለማፍረስ የሚደረግ እንቅስቃሴ ይቁም !
- የህዝቦች አንድነት ለማፍረስ የሚደረገው እንቅስቃሴ በጥብቅ እንቃወማለን !
- እምባገነንነት ፣ጭቆናና አፈና አንቀበልም !
- መቐለ የልማት እንጂ የአመፅ መነሃሪያ አይደለችም !
- የጊዚያዊ አስተዳደሩ ውሳኔዎች በድማፃችን ይከበራሉ !
- የአመፅ መሪዎች ወደ ህግ ይቅረቡ !
- እውነተኛ የህዝብ ትግል አይቀለበስም !
- ህዝብ እና እውነት የያዘ ያሸንፋል !
- እናሸንፋለን ! ... የሚሉና ሌሎች መፈክሮች ከፍ ባለ ድምፅ አሰምተዋል።
የሰልፈኞቹ ጥያቄ ያዳመጡ በቦታው የተገኙ የክልሉ ከፍተኛ የፀጥታ አመራሮች " ወቅታዊ የሰልፈኞቹ ጥያቄ ከሚመለከተው አካል ምላሽ እንደሚሰጠው " በመንገር ሰልፈኞቹ ወደ መጠቡበት አከባቢ በሰላም እንዲመለሱ አድርገዋል።
በሰልፈኞቹ መካከል ይሁን ከፀጥታ አካላት ጋር የተፈጠረ ግርግር እና ግጭት እንደሌለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ቦታው ደረስ በአካል በመገኘት አረጋግጧል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በጊዚያዊ አስተዳደሩ የተሾሙ አዲሱ የመቐለ ከንቲባ ብርሃነ ገ/የሱስ በይፋዊ የማህበራዊ የትስስር ገፃቸው " የትግራይ ትንሳኤ እውን እንዲሆን እጅ ለእጅ ተያይዘን እንነሳ " የሚል ይዘት ያለው ፅሁፍ አጋርተዋል።
በተመሳሳይ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ እየመከረ ሲሆን ፤ በምክክሩ የዞን እና የክልሉ የፀጥታ አመራሮች ተሳታፊ እንደሆኑ የፕሬዜዳንት ፅህፈት ያወጣው መረጃ ያመለክታል።