ህንፃው ለምን ነጣ?
የጉስቁልና ደሴት ነዋሪዎች እድሳቱ ያለቀው ታላቁ የአፄ ፋሲል (ጎንደር) ቤተመንግስት በጣም “ነጣ” እያሉ ነው። አብዛኞቹ ለማልቀስ የተወለዱ ስለሆኑ ምንም ልንረዳቸው አንችልም። ለቅን ጠያቂዎች ግን ከባለሙያዎችና ከሰነዶች ያገኘነውን መረጃ ባጭሩ እናስቀምጥ ..
ሰነዶችና በዘርፉ ጥናት ያደረጉ ባለሙያዎች እንደሚያስረዱት ነገስታቱ በግንባታ ግዜ የተጠቀሙባቸው ግብአቶች እነዚህን ይመስላሉ፦
ብረት ፥ የጭቃ ጡብ ፥ እንጨት ፥ የተመረጡ ድንጋዮች ፥ የኖራ ጡቦች ፥ የኖራና የአሸዋ ድብልቅ ድንጋዮች ፥ ውሀ ፥ ወዘተ .. ናቸው።
ታላቁን ቤተመንግስት ለመገንባት ነገስታቱ የተጠቀሙት ከላይ የተዘረዘሩት ዘመኑ የፈቀደላቸውን ግብአት ከመሆኑም ባለፈ በግዜው ህንፃው ሲሰራ የነበረው ቀለም አሁን ከታደሰ በኋላ ያለውን መልክ እንደሚመስል ብዙ ባለሙያዎች ይስማማሉ። ህንፃውም ሲታደስ በውጭና በሐገር ውስጥ ባሉ ባለሙያዎች ለረጅም ግዜ ተጠንቶ የተሰራ እንጂ እንደተራ ነገር ዝም ብሎ የሆነ አይደለም።
አሁን በጣም የነጣ የመሰለን ህንፃው ለመቶ አመታት የቆየ ከመሆኑ አንፃር በግዜ ብዛት ፀሀይ ዝናብና ነፋስ ሲፈራረቅበት በመቆየቱና አቧራ በመልበሱ ቆሽሾ የወየበውን ህንፃ አይናችን ስለለመደው ብቻ ነው።
ለማንኛውም ያሰቡ፥ ያሰሩና የገነቡ ሁሉ ምስጋና ይግባቸው እንላለን።