ተርእዮ (የመታየት ጉጉት)
አሁን ለደረስንበት "ኹለንተናዊ ውድቀት" ተጠያቂው "ዘመኑ" ወይም ማኅበራዊ ሚዲያው አይደለም። ተጠያቂው "ዘመኑ" ሳይሆን እኛው ነን - በዘመኑ ውስጥ የምንሠራ ነንና። ሚዲያውም ቢሆን የኛን የልብ ጥመትና ክፋት ገለጠብን እንጂ በራሱ መጥፎ አይደለም። ከጥቂት ዓመታት በፊትና በአሁኑ ዘመን መካከል በተለይ በክርስቲያናዊ አኗኗር ላይ ብዙና ሰፊ ለውጦች የታዩ ይመስለኛል። ከሁሉ ከሁሉ ግን ዕለት ዕለት የሚገርመኝ የተርእዮ ፍላጎታችን መጋሸብ ነው። አሁን ላይ ግሽበት ለኢኮኖሚው መስክ ብቻ የሚነገር አይደለም። ከእርሱ ሌላ ኢጎ ("የእኔነትና - የለኔነት") ከፍተኛ ሁኔታ ጋሽቧል። የመታየት አምሮትም ከዚህ የሚለይ አይደለም። የአሁን ሰው ዛሬን መኖር ረስቷል። ዛሬን (አሁንን) ከመኖር ይልቅ ለትዝታ የሚሆነው ላይ ይታትራል። ቤተ ክርስቲያን (ንግሥ፣ ማኅሌት፣ ቅዳሴ ... ) በእግሩ መጥቶ፤ በልቡ ግን ከሥርዓተ አምልኮቱ ውጪ ይሆናል። ነገ ራሱና ሌሎች የሚያዩትን በፎቶና በቪዲዮ ለማስቀረት "ይተጋል"። በአምልኮቱ ጊዜ በልዩ ሁኔታ የተገኘውን ክርስቶስን (Divine Presence) ሳያገኝ፤ ሌሎች ለሚያዩት፣ በቲክቶክ ለሚለቀው ቪዲዮ ይደክማል።
በቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ አምልኮት ላይ ማን እንዴትና ለምን እንደሚገኝ የምናውቀው ይመስለናል እንጂ ፈጽሞ አላወቅነውም። ክርስቶስ እኛን ለማግኘት ይመጣል፤ እኛ በኢጎአችን ተመርተን የሠራነውን ለሌሎች Broadcast ለማድረግ እንፋጠናለን። ስለዚህም ጸጋ እግዚአብሔር ከብዙዎቻችን ጋር ሳይዋሐድ የሚመለስ ይመስለኛል። Divine Presence ሊዋሐደው የሚሻ እውነተኛ (ልባዊ) human presence ይፈልጋልና። እኛ ሰማያዊውን ለሰው መታያ አደረግነው። መዝሙሩ ብዙዎች የሚኩነሰነሱበት መታያ ሆነ፤ ትምህርቱም ብዙዎች የጸሎትና የቅዳሴ መንፈስ የራቀው፡ እርስ በእርስ መሸነጋገያ ሆነ። ምስጋና እና ክብርን መጠማት በዛ። "የራስ ሥራን" በሰው ክብር መሸጫ መለወጫ ገበያዎች ብዙ ሆኑ። "ሌላው ሰው" ለክርስትናችን አስፈላጊያችን መሆኑ ተረሳ። ዓለም እርሱን በእጁ ስለያዘው ገንዘብ ምክንያት እንደምትፈልገው፤ እንዲሁ እኛም እርሱን ለመውደድ በእርሱም ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘትን ሳይሆን ስለ ገንዘቡና ስለሚሰጠን attention ብቻ እንፈልገዋለን። ታዲያ ክርስትናውን መቼ መኖር እንጀምር ይሆን? መቼ ከራሳችን ጋር የእውነት እንተያይ? መቼ እውነተኛ ንስሐን እናግኝ? መቼ እግዚአብሔርን እና ሌላውን ሰው የእውነት እንወድ ይሆን?
"ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው ወልደ ማርያም ሥግው መሐረኒ!"
( ዲያቆን ሚክያስ አስረስ )
#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ