አዳም ክፉን እና መልካሙን ከሚያስታውቀው ዛፍ እንዳይበላ የታዘዘበት ምክንያት ፈጣሪውን ምን ያክል እንደሚወድና ምንያክል እንደሚታመንለት ለማሳየት ምልክት ነበር ምክንያቱም አዳም ስለእግዚአብሔር ፍቅር ብሎ ከተከለከለው ዛፍ መብላትን እንዲተው ነበር የተፈለገው ። ነገር ግን አዳም ከእግዚአብሔር ፍቅር ይልቅ የራሱ ፍላጎት አሸንፎት ሕጉን ተላልፍ ዕፀ በለስን ቀጥፎ እምነቱን አጎደለ ፈጣሪውን በደለ ።
ስለዚህ ጾም አንድ ሰው አንድን ነገር ለማድረግ መብትና ሥልጣን እያለው ኾኖ ከዚያ በላይ የፈጣሪውን ቃል አስቦ ሊያደርገው ያሰበውን ነገር በመተው ከፈቃዱ ላይ መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ማቅረብ ማለት ነው ።
( ኆኅተ ስብከት ዘቅዱስ ያሬድ ቅጽ-፪ )
#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ
ስለዚህ ጾም አንድ ሰው አንድን ነገር ለማድረግ መብትና ሥልጣን እያለው ኾኖ ከዚያ በላይ የፈጣሪውን ቃል አስቦ ሊያደርገው ያሰበውን ነገር በመተው ከፈቃዱ ላይ መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ማቅረብ ማለት ነው ።
( ኆኅተ ስብከት ዘቅዱስ ያሬድ ቅጽ-፪ )
#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ