ጌታችን ያለ ወንድ ዘር ስለምን ተወለደ ?
በዘር በሩካቤ መወለድ ኃጢአት ስለሆነ ይሆን ? አይደለም ! እኮ ስለምን እንልከሆነ ፦ በሴቶች የወንዶች ብድር ነበረባቸው ። ብድሩም አዳም ብቻውን ሴትን ሲያስገኝ ፥ ሴቶች ግን ወንድን አላስገኙም ነበር ። ይህን የሴቶች ብድር ሲያጠፍላቸው ከድንግል ማርያም በድንግልና ተወለደ ። ዮሐንስ አፈ ወርቅ ይህን ሲመሰክር ወበእንተዝንቱ ወለደት ድንግል ብእሴ እንበለ ዘርዐ ብእሲ ከመትፍድዮ ለብእሲ ዕዳሃ ለሔዋን ፣ ስለዚህም እመቤታችን ብእሲ ክርስቶስን ያለ ዘር አስገኘች። የሔዋንንም ብድራት ለአዳም ትከፍለው ዘንድ ብእሲ ክርስቶስን ያለ ዘር ወለደችው በማለት ይናገራል ሃይ.አበ.ም.፳፮፥፳፱። (ኦርያሬስ ገጽ-160 መምህር ሳሙኤል ሰሎሞን) ባለጠግነቱ ይህም አይደለም ታድያ ።
ሊቁ ቅዱስ ያሬድ እመቤታችንን "አንቀጸ ብርሃን" የብርሃን ደጅ በር እያለ ያመሰግናታል ሌሎች ደጆች ካልተከፈቱ አያስገቡም ካልተዘጉም አይከለክሉም መስታወት ተዘግቶም ሳለ ብርሃን ያሳልፍል ሌሎች ግዙፍን ፍጥረታትን ግን አያሳልፍም ሌሎች አናቅጽ የሌሎች ሴቶች ምሳሌ አነርሱ በድንግልና ፀንሰው በድንግልና መውለድ አልቻሉም እርሷ ግን በድንግልና ፀንሳ በድንግና ወልዳለች ያ ብርሃንን እያስገባ ሌሎቹን እንዲከለክል እመቤታችንም ጌታን በድንግልና ስትወልድ ልማደ አንስት ዘርዐ ወራዙት አላገኛትምና ከጌታችን በቀርም ልጅን አልወለደችም በዚህም አንቀጸ ብርሃን ተብላለች ። ( አንቀጸ ብርሃን አንድምታ ትርጓሜ ገጽ-35 መ/ር ኃይለ ማርያም ዘውዱ )
#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ