#መድኃኔዓለም
~~~~
✍️ " #እኛም_አይተናል_አባትም_ልጁን_የዓለም #መድኃኒት_ሊሆን_እንደ_ላከው_እንመሰክራለን።" ፩ኛ ዮሐ ፬፥፲፬
✝️እውነት ነው አይተናል አምስት ቀን ተኩል በእግረ አጋንንት በኃጢያት ወድቀን፤ ከክብር ተዋርደን በለስን በልተን ሞትን ሸምተን ቆይተናል ነገር ግን ሞታችን በሞት የሚሽረው የአብ ልጅ ክርስቶስ ለእኛ መድኃኒት እንዲሆን አብ እንደላከው እንመሰክራለን።
✝️ አዎ ከእቅፉ ሸሽተን በነበረበት በዚያ ወቅት ዘጠና ዘጠኙን በጎች ትቶ አንዱ ነገደ አዳምን ሽቶ ከእመቤታችን የተወለደው በቤተልሔም በከብቶች ግርግም የተኛው የዓለሙ መድኃኒት መሆኑን እንመሰክራለን።
✝️ ሄሮድስ በቅናት ንግስናውን የሚወስድበት መስሎት ሊገድለው የፈለገው፤ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋር ወደ ግብጽ የተሰደደው መድኃኒታችን ነው።
✝️እርጥብ መስቀል ተሸከም ቀራንዮ የዘለቀው ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ የሕይወት ምግብ የሕይወት መጠጥ ይሆነን ዘንድ የሰጠን እርሱ ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት ነው። ይኸውም መድኃኒትነቱ ከሞት የሚታደግ ኢየሱስ ክርስቶስ የተቤዠን መድኃኒታችን ነው።
✝️ ሳዶር፣ አላዶር፣ ዳናት፣ አዴራ ፣ ሮዳስ በተባሉ አምስት ቅንዋት የተቸነከረው በችንካራቱም፤ በመስቀሉም ብርሃን የሆነን አማኑኤል ከእኛ ጋር የሆነው የዓለም መድኃኒት ነው።
✝️ ለሚገድሉት ምህረትን የሚለምን ቸር አምላክ፤ መቃብር ክፈቱልኝ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ከሙታን ተለይቶ የተነሳ እርሱ ክርስቶስ የዓለም መድኀኒት ነው
በቸርነቱ ይማረን!🙏
@Orthodox_Tewahedo23