Forward from: "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
☞ ወር በገባ በ 24 ቀን የሙሴ ጸሌም ወርሐዊ መታሰቢያ ነው፡፡☞ብዙ መነኮሳት ወደ አቡነ ሙሴ እየመጡ የሕይወት ትምህርትን ይማሩ ነበር፡ ከነዚህ የሕይወት ትምሕርታቸው መካከል በጥቂቱ እንመልከት፡፡
☞1ኛ☞አባ ሙሴ በገዳመ አስቄጠስ እያለ ከገዳማውያን አንዱ ጥፋት ሠራና
ማኅበሩ ለፍርድ ተሰበሰበ፡፡ አባ ሙሴ ግን በጉባኤ ላይ አልነበረም፡፡ ስለዚህ
ካህኑ ተልኮ ና ሁላችንም አንተን እየጠበቅን ነው አለወ፡፡ አባ ሙሴም በሚያፈስስ
ከረጢት አሸዋ ሞልቶ ያንንም በጀርባው ተሸክሞ ከኀላው እያፈሰሰ ወደ ጉባኤው
አመራ፡፡ ጉባኤተኞቹ ተገርመው ለምን እንደዚህ እንዳደረገ ጠየቁት፡፡ እርሱም
የእኔ ኃጢአቶች በኀላዬ እንደዚህ አሸዋ በዝተው ይፈሳሉ ነገር ግን ላያቸው
አልቻልኩም ዛሬ ግን በሌላው ላይ ለመፍረድ መጥቻለሁ አላቸው፡፡ ይህን ሲሰሙ
ዝም አሉ፡፡ ያን ወንድምም በይቅርታ አለፋት፡፡
☞2ኛ☞በሌላ ጊዜ በገዳመ አስቄጠስ ያሉ መነኮሳት ተሰብስበው የአባ ሙሴን
ትዕግሥት ለመፈተን ሲሉ ይህ ጥቁር መነኩሴ ለምን እዚህ መጣ ብለው
ተናገሩት፡፡ እርሱም ዝም አለ፡፡ ጉባኤው ሲበተን አባ ክፋ ስንናገርህ ምንም ሐዘን
አልተሰማህም ነበርን? ሱሉ ጠየቁት፡፡ እሱም ተሰምቶኝ ነበር ግን እንዳልናገረው
አንደበቴን ተቆጣጠርኩት አላቸው፡፡
☞3ኛ☞አንድ ጊዜ የአካባቢው ገዥ ሰለ አባ ሙሴ ዝና ሰምቶ ያየው ዘንድ ወደ
ገዳመአስቄጠስ መጣ፡፡ ይህን የሰማው አባ ሙሴ ሸሽቶ ወደ ጫካ ገባ፡፡
በመንገድም ላይ የገዥው መልእክተኞች አገኙትና እባክህን አባ ሙሴ የት
እንዳለ በኣቱን አሳየን አሉት፡፡ ከርሱ ምን ትሻላችሁ እርሱ ኮ ቂላቅል ነው
አላቸው፡፡
☞ይህን የሰማው የአካባቢው ገዥ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ መጣና የሆነውን ሁሉ
ለአገልጋዮቹ ነገራቸው፡፡ ብዙ ሰዎች ስለ አባ ሙሴ ሲያወሩ ሰምቼ ለማግኘት
መጥቼ ነበር በመንገድ ላይ ያገኘነው አንድ አረጋዊ ሰው ግን የአባ ሙሴ በኣት
የት እንደሆነ ስንጠይቀው ከእርሱ ምን ትሻለችሁ እርሱ ኮ ቂላቅል ነው አለን
ብለው ነገራቸው፡፡
☞አገልጋዮቹም በጣም ተናደዱና ምን ዓይነት ሰው ነው ስለ ቅዱሱ ይህን
የሚናገር ብለው ጠየቁት፡፡
☞ትልቅ ጠቆር ያለ አሮጌ ልብስ የለበሰ ነው፡፡ አላቸው፡፡ አገልጋዮቹም
ተገርመው ይህማ ራሱ አባ ሙሴ ነው ይህን ያለህ ሊያገኝህ ስላልፈለገ ነው
አሉት፡፡ የአካባቢው ገዥም ከአባ ሙሴ ሁኔታ ከንቱ ውዳሴን ስለ መሸሽ ትልቅ
ትምህርት ተምር ተመለሰ፡፡
☞4ኛአባ ሙሴ በኣት ሠርቶ ወደ ጴጥራ ሲሔድ በአካባቢው ውኃ ሰላልነበረ
ተጨንቆ ነበር፡፡ አንድ ድምፅ ሒድ ስለምን ነገር አትጨነቅ አለው፡፡ ሰለዚህም
በዚያ መኖር ጀመረ፡፡ አንድ ቀን በጴጥራ እያለ አበው ሊጎበኙት መጡ
የነበራቸውን ውኃ ጥቂት ነበረችና በርሷ ምግባቸውን አበሰለ፡፡ የሚያጠጣቸው
ግን አላገኘም፡፡ ስለዚህ ወደ ውጭ እየወጣ ውኃ ይሰጠው ዘንድ እግዚአብሔርን
ይለምን ነበር፡፡ በመጨረሻም ዝናብ ዘነበና የውኃ ማጠራቀሚያዎቹን ሁሉ ሞላ፡፡
☞እነዚያም አባቶች ትወጣና ትገባ የነበረው ለምን እንደሆነ እባክህ ንገረን
አሉት፡፡ እናንተ በእግድነት ስትመጡ ውኃ አልነበረኝም ስለዚህ ያንተን አገልጋዮች
ወደ እኔ ልከሃቸዋል ነገር ግን ውኃ የለኝም ስለዚህ እባክህ ውኃ ስጠኝ እያልኩ
እግዚአብሔርን ለመለመን ነበር አላቸው፡፡
☞5ኛ☞በአንድ ወቅት በገዳመ አስቄጠስ ጾም ታወጀ፡፡ በዚያም ሳምንት አባ
ሙሴን ለማየት ከግብፅ ወንድሞቹ መጡ፡፡ አባ ሙሴም በእንግድነት
ተቀበላቸውና ምግብ ያበስልላቸው ጀመር፡፡ የእሳቱን ጢስ የተመለከቱ ጉረቤቶቹ
አባ ሙሴ ትእዛዝ አፍርሶ ምግብ ያበስላል ብለው ለገዳሙ ሓላፊዎች ተናገሩት፡፡
ሓላፊዎችም አሁን ተውት ሲመጣ እኛው ራሳችን እናናግረዋለን አሏቸው፡፡
☞ሓላፊዎችም አባ ሙሴን ጠርተው ለምን ምግብን እንዳበሰለ ተረዱ፡፡
በቀዳሚ ሰንበት ማኅበሩ ሁሉ ወደ ቤተክርስቲያን ሲጣ በዐደባባይ አባ ሙሴ
ሆይ የሰውን ትእዛዝ አልጠበቅም የእግዚአብሔር ትእዛዝ /እንግዳ ሆኜ መጥቼ
ተቀብላችሁኛል የሚለውን ግን ጠብቀሃል ብለው አመሰገኑት፡፡
☞የጻድቁ አባታችን የአቡነ ሙሴ ጸሊም የሕይወት ትምህርቶች ከብዙ በጥቂቱ
በእኔ በሀጥያተኛው ለበረከት ያክል ይቺን ጻፍኩላችሁ፡፡
☞የጹሁፍ ምንጭ(በዲያቆን ዳንኤል ክብረት ከተጻፈው "በበረሓ ጉያ
ውስጥ"ከተሰኘው መጽሐፍ የተወሰደ)
☞ከጻድቁ አባታችን ከአባ ሙሴ ጸሊም የሕይወት ትምህርት ተምረን ፍሬ
ለማፍራት ፈጣሪ ማስተዋሉን ያድለን፡፡
☞የጻድቁ አባ ሙሴ ጸሊም በረከታቸው ይደርብን፡፡
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ
☞