አንድ በሥራው ታታሪ የሆነ ዓሳ አጥማጅ ነበር።ይህ አጥማጅ በየቀኑ ዓሳ ያጠምድና አስከሚያልቅ ድረስ ይጠቀማል። ልክ ሲያልቅ ወደ ባህር ዳርቻ በመሄድ ሌላ ያጠምዳል።
ከእለታት አንድ ቀን የዓሳ አጥማጁ ሚስት ባሏ ያመጣላትን ዓሳ በመቆራረጥ ላይ ሳለች አሰገራሚ ነገር ታያለች። ይህች ሰው የተመለከተችው እጅግ የከበረ ሉል ነው ። በጣም እየተገረመች በዓሳ ሆድ ውስጥ ሉል ...? አያለች ባሌ... ባሌ... ባሌ... እያለች ባሏን መጥራት ጀመረች ከዚያም "ምን እንዳገኘሁ ተመልከት ሉል እኮ ነው!! ሉል ... ከዓሳው ሆድ ውስጥ " አለችው ።
እሱም " እንዴት አሰደሳች ሚስት ነሽ እስኪ አቅርቢው ለዛሬ ለቤት ቀለባችን መግዣ ትሆነናለች ..... ከዓሳ ሌላ ምግብ እንበላለን!!" አላት..... ይህ ዓሳ አጥማጅ ሉሉን በመያዝ ወደ ሉል ገዢና ሻጭ በመሄድ ያሳየዋል። ገዢውም "እኔ ይህንን ሉል የመግዛት አቅሙ የለኝም፤ ዋጋው ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ ይህንን ሱቄንና መኖሪያ ቤቴን ብሸጠው እንኳን ልገዛህ አልችልም። ይልቁንስ እከሌ የሚባል ሀብታም ነጋዴ አለ እርሱ ሊገዛህ ይችላልና ወደርሱ ሂድ። አለው ።
ዓሳ አጥማጁ ሉሉን በመያዝ ወደ ተባለው ሀብታም ሰው በመሄድ ጉዳዩን ነገረው። ይህ ታላቅ ነጋዴም "እኔ አልችልም ይህ የያዝከው ሉል በገንዘብ የሚተመን አይደለምና እኔ መፍትሔ ብዬ የማስበው ወደ ከተማው አስተዳዳሪ ሄደህ ብታሳየው ነው እንደዚህ አይነት ውድ ሉል ከርሱ ውጭ የመግዛት አቅም አለው ብዬ የማስበው ሰው የለም " አለው።
ጉዞውን ወደ ተባለው አስተዳዳሪ በማድረግ ቤቱ እንደደረሰ ወደ ህንፃው ለመግባት ፈቃድ እስኪያገኝ ድረስ መጠበቅ ጀመረ።
(እንደገባም) ለአስተዳዳሪው የያዘውን ሉል ሲያሳየው አጅግ ተገረመ። "እንደዚህ አይነት ሉል ስፈልገው የነበረ ነው…እንዴት ተመኑን እንደምከፍልህ አላውቅም… ነገር ግን ለየት ወዳለው ካዝናዬ እንድትገባ እፈቅድልሃለሁ። እዛ ውስጥም ለስድስት ሰዓታት በመቆየት የቻልከውንና የፈለከውን ንብረት ተሸክመህ መውጣት ትችላለህ። ይህ እንግዲህ የሉልህ ክፍያ ነው።" በማለት ወደ ካዝናው እንዲገባ ጋበዘው።
ዓሳ አጥማጁም "አለቃዬ ሆይ! ስድስት ሰዓት…!! እንደኔ ላለ ዓሳ አጥማጅ በጣም ብዙ ነው እንደው ሁለት ሰዓት ብታደርግልኝ " ሲል ጠየቀው። አስተዳዳሪውም "በጭራሽ አይሆንም ስድስት ሰዓት ሙሉ ከካዝናዬ የፈለከውንና የምትችለውን ያህል ይዘህ መውጣት አለብህ " አለው። ዓሳ አጥማጁ ወደ ካዝናው ሲገባ በጣም የሚያስደንቅ ሁኔታን ተመለከተ። በሦስት የተከፈለ ሰፊ ክፍል
☞ አንደኛው ክፍል በአልማዝ፣ በወርቅና በተለያዩ ጌጣጌጦች የተሞላ ክፍል ነው።
☞ሁለተኛው ክፍል ለመተኛት ምቹ የሆኑ ለየት ያሉ ፍራሾች ያሉበት ክፍል ነው።
☞ ሦስተኛው ክፍል አጠቃላይ በሚፈለጉና ውድ በሆኑ የምግብና የመጠጥ ዓይነቶች የተሞላ ነው።
ዓሳ አጥማጁ ከራሱ ጋር መነጋገር ጀመረ። "ስድስት ሰዓት!! እንደኔ ላለው ድሃ ዓሳ አጥማጅ በጣም ብዙ ነው በዚህ ስድስት ሰዓት ምን ማድረግ አለብኝ? ጥሩ! በሦስተኛው ክፍል ባሉት ምግብና መጠጥ መጀመር አለብኝ ምክንያቱም ብዙ ወርቅ ለመሸከም የሚያስችለኝን ኃይል አገኝበታለሁ። " በማለት ወደ ሦስተኛው ክፍል በመሄድ መብላት ጀመረ። ይበላል… ይበላል… ይጠጣል…
ከስድስቱ ሰዓታት በመብላት ሁለቱን ሰዓት ተጠቀመ። ልክ ሲጨርስ ወርቁንና ጌጣጌጡን ለመሸከም ወደ አንደኛው ክፍል በመሄድ ላይ ሳለ በሁለተኛው ክፍል ያለውን ያማረ ምቹ ፍራሽ ተመለከተና እራሱን ማናገር ጀመረ። "አሁን በጣም ጠግቤያለሁ ለምን ትንሽ በመተኛት በደንብ ለመሸከም የሚያስችለኝን እረፍት አልወስድም? ይህንን እድል ደግሜ አላገኘውምና ለምን
አበላሸዋለሁ?" በማለት ወደ ፍራሹ በመሄድ በጀርባው ተዘረጋ በጣም ጭልጥ ያለ እንቅልፍም ወሰደው።
ከተወሰነ ሰዓታት በኃላ "ተነስ ተነስ ቁም አንተ ጠባብ የሆንክ ዓሳ አጥማጅ ተነስ… ቁም...... ጊዜው አልቋል " አለው። ዓሳ አጥማጁም " እ እ እንዴ ምንድነው...?" አለ። ሰውዬውም " አዎ! ወደ ውጭ ውጣ " አለው። አጥማጁም "ኧረ ምንም በቂ ዕድል አላገኘሁም " አለ። ሰውዬውም "ስድስት ሰዓታት ሙሉ በዚህ ካዝና ውስጥ ሆነህ ጊዜህን ሳትጠቀም ቀርተህ አሁን ትባንናለህ? ከዚያም ሰዓት እንዲጨመርልህ ትጠይቃለህ? እነዚህን አልማዝና ወርቆች በፍጥነት ሰብስበህ በመውጣት የፈለከውን ምግብና መጠጥ እንዲሁም ያሰኘህን አይነት የመኝታ ፍራሽ መግዛት ትችል ነበር። ነገር ግን አንተ ዝንጉና ጠባብ በመሆንህ በዙሪያህ ያለውን እንጂ ሩቅ ያለውን ነገር አታስብም።" በማለት "ወደ ውጭ አስወጡት! " አለ።
አጥማጁም "ኧረ ባካችሁ!! ኧረ!… እባካችሁ አንድ እድል ይሠጠኝ " ቢልም ሊሆንለት አልቻለም።
ታሪካችን አለቀ በውስጡ ያለው ትምህርት ግን አላለቀም......
ልብ በሉ ይህ ሰውዬ እጅግ የከበረ ጸጋ ተሰጥቶት አልተጠቀመበትም ባለችው ጊዜያዊ ምግብና መኝታ ተታሎ እጅግ የበለጠ ጥቅሙን አጣ። የሰው ልጅ ህይወትም እንደዛ ነው። ፀልዩ፣ ንስሃ ግቡ፣ ቁረቡ፣ መንፈሳዊ ስራ ስሩ ስንባል ሁሌ ቀጠሮ። ሁሌ ረጅም ጊዜ ያለን ይመስለንና ቆይ ገና ነኝ እያልን ቀጠሮ እንይዛለን። የሚጠቅሙንን መንፈሳዊ ተግባራት ላይ አስቀድመን ከመሰማራት ይልቅ ሁሌ ስጋዊ ነገሮች ላይ አትኩሮት እየሰጠን የተሰጠን ጊዜ ያልቃል። መንፈሳዊ ተግባራትን እንደ ትርፍ ወይም ተጨማሪ ነገር አናያቸው። ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ከሆነ ሌላው ሁሉ ትርፍ ነው ይጨመርለታል። እግዚአብሔር ይሞላዋል።
እኛም ምድራዊ ነገር አታሎን ጥርስ ማፏጨትና ልቅሶ ወዳለበት ወደ ሲኦል እንዳንጣል በጊዜ ንስሐ ገብተን ተዘጋጅተን ልንኖር ግድ ነው።