በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን እንደምን ቆያችሁ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
መልስና ጥያቄ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
1⃣,ቤተ ክርስቲ ያን ማለት ምን ማለት ነው??
መልስ፦ -ቤተ ክርስቲያን ማለት የክርስቲያኖች አንድነት ጉባኤ ወይም ማህበር ማለት ነው።
2⃣,መንፈሳዊ ተጋድሎ ማለት ምን ማለት ነው??
መልስ፦ ተጋድሎ ማለት አንድ ሰው የሚያምንበትን እምነት፣የሚመራበትን ሕግ፣ የሚያልመውን ተስፋ ተከትሎ ሀሳቡን ከግብ ለማድረስ ማድረግ የሚገባውን በማድርግ፣ማድረግ የማይገባውን ባለማድረግ በነጻ ፈቃዱ ወስኖ በሙሉ ልቦናው እና በሙሉ ኃይሉ የሚያደርገው የውስጥ እና የውጭ ጥረት ነው።
3⃣, ጸጋ እግዚአብሔር ለማግኘት ምን ማድረግ አለብን???
መልስ፦ ጸጋ ማለት እግዚአብሔር ለልጆቹ በነጻ የሚያድላቸው ስጦታ ማለት ነው። ይኸውም የሚገኘው በመንፈሳዊ ተጋድሎ ነው።
4⃣,የቅዱስ ጴጥሮስ አባት ማን ይባላል??
ነው
መልስ፦ ዮና ይባላል።
5⃣, ከአስራሁለቱ (፩፪) ሐዋርያት መካከል በመጀመርያ የሰማዕትነን አክሊል የተቀዳጀ ሰማዕትነቱ በሐዲስ ኪዳን መጽሐፍ የተጻፈለት ብቸኛ ሐዋርያ ማን ነው??
መልስ፦ ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ /ወልደ ዘብዴዎስ/ ነው።
የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ቁጥር ፩ ገጽ 48 ላይ ማንበብ ይቻላል።
6⃣, ገድላት በስን ይከፈላሉ??
መልስ፦ ገድላት በ3 ይከፈላሉ እነሱም፦ 1) ገድለ ሰማዕታይ፦ ለምሳሌ ገድለ ጊዮርጊስመከራ ገድለ ፋሲለደስ፤ ገድለ ኢየሉጣ
2) ገድለ ሐዋርያት፦ በአንድነት የተሰበሰቡ የሐዋርያት አገልግሌት ተአምራት የያዘ መጽሐፍት
3) ገድለ ጻድቃን፦ ገድለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ ገድለ ገብረ መንፈስ ቅዱስና የመሳሰሉት ናቸው።
7⃣, ህግ በስንት ይከፈላል??
መልስ ፦ በ3 ይከፈላል እነሱም
1ኛ ህግ ልቦና
2ኛ ህግ ኦሪት .
3ኛ ህግ ወንጌል ናቸው።
8⃣, መልአኩ ቅዱስ ገብሬኤል ለነብዩ ዳንኤል ስንት ሚስጥራት ገለጸለት??
//መልስ፦// 3 ሚስጥራትን ገልጾለታል 1ኛ የቤተ እስራኤልን ከ70 አመት በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም መመለስ።
2ኛ የክርስቶስ ሰው መሆንና መሞት ዘመን
3ኛ የኃሳዊ መሲህን በመጨረሻው መምጣት ነው።
9⃣, በ8ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ቤተ ክርስቲያን ታቃጥል የነበረች አይሁዳዊ ፈላሻ ማን ነበረች??
// መልስ// ዮዲት ጉዲት ነበረች።
የሚከተሉትን ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ ምረጥ/ጭ/
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
10, አዕማደ ሐዋርያት (የምሥጢር ሐዋርያት) ከሚባሉት ውስጥ የሆነው የትኛው ነው??
ሀ) ዮሐንስ ለ) ያዕቆብ መ) ጴጥሮስ ሠ) ሁሉም መልስ ነው??
//መልስ// ሠ, ሁሉም መልስ ነው።
11, ቆስጠንጢኖስ ለቤተ ክርስቲያን ከሰጣቸው መብቶች ውስጥ የትኞቹ ናቸው??
ሀ) ቤተ ክርስቲያን ከግብር ነጻ ናት።
ለ) ከመንግሥት ገቢ ለቤተ ክርስቲያን የተወሰነ ድርሻ አላት።
ሐ) ዕለተ እሑድ /ሰንበት/ በንጉሠ ነገሥቱ ግዛት ውስጥ ሥራ እንዳይሠራበት አወጀ።
መ) ከክርስቲያን ወገን በሕይወቱም ሆነ በሞቱ ንብረቱን ለቤተ ክርስቲያን አወርሳለሁ የሚል ምእመን ካለ ቤተ ክርስቲያን ኑዛዜ የመቀበል፤ ውርስ የመውረስ መብት አላት።
ሠ) በክርስቲያኖች መካከል ለሚፈጠሩ አንዳንድ አለመግባባቶች ቢኖሩ ለኤጲስ ቆጶሳት የዳኝነት ሥልጣን ሰጥቷል።
ረ) ሁሉም መልስ ነው።
የተጀመረው
//መልስ// ረ, ሁሉም መልስ ነው።
1⃣2⃣, ክህደት በ-----------------ነው
.ሀ) በሳጥናኤል/ዲያብሎስ
ለ) በአርዮስ
ሐ) በይሁዳ
መ) አይታወቅም
//መልስ//፦ ሀ) በሳጥናኤል /ዲያብሎስ
ውድ የተወደዳችሁና የተከበራችሁ ወንድም እህቶቼ ጠቅላላ መልስ ይህንን ይመስላል ስተት ከአለበት አርሙኝ ለመታረም ዝግጁ ነኝ። ወስብኃት ለእግዚአብሔር
ወለ ለወላዲቱ ድንግል
ወለ ለመስቀሉ ክቡር።
✝ኦርቶዶክስ ተዋህዶ✝
#መልካም_አዳር
https://t.me/OrtoPicturehttps://t.me/OrtoPicturehttps://t.me/OrtoPicture